You are currently viewing የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ሰባኪያን፡ ማህበራት እና ምዕመናን እራሳችሁን ከ33 አመታት በላይ ማታለሉ አይበቃችሁም? ====== ሸንቁጥ አየለ ======= ወያኔ የተባለ መርዛማ እባብ ተዋህዶ…

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ሰባኪያን፡ ማህበራት እና ምዕመናን እራሳችሁን ከ33 አመታት በላይ ማታለሉ አይበቃችሁም? ====== ሸንቁጥ አየለ ======= ወያኔ የተባለ መርዛማ እባብ ተዋህዶ…

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ሰባኪያን፡ ማህበራት እና ምዕመናን እራሳችሁን ከ33 አመታት በላይ ማታለሉ አይበቃችሁም? ====== ሸንቁጥ አየለ ======= ወያኔ የተባለ መርዛማ እባብ ተዋህዶን አጠፋለሁ ብሎ ማኒፌስቶ ጽፎ ተዋህዶን በሚዲያ እያዋረድ ጸረ ተዋህዶ ሀይላትን ጉልበታቸዉን በኢኮኖሚና በስነልቦና እንዲሁም በተቋማዊ ኔትወርክ ሲገነባ የተባበሩት እና በዋናነት ግቡን ያስፈጸሙለት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ሰባኪያን፡ ማህበራት እና ምዕመናን ነበሩ።ከጳጳሱ እስከ ሰባኪና ካህኑ ፡ ከማህበራት እስከ ጽዋ ማህበራት። በምን አገባኝ፡ በግዴለሽነት : በልኑርበት፡ በዘረኝነት ፡ በድንቁርና እና በወንዘኝነት ጭምር የሆነዉ ሁሉ ሆኗል።ያለፈ ዘመን እንደ ፈሰሰ ዉሃ ነዉ። አሁን ግን የመንቂያ ዘመን ነዉ። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ሰባኪያን፡ ማህበራት እና ምዕመናን ዘር መቋጠሩን ትታችሁ ( ቢያንስ ኦነግ/ኦህዴድ ወይም ህዉሃት ያልማረካችሁ) ምን አገባኝን ትታችሁ ኢትዮጵያ የምትድንበትን መንገድ ምከሩ። ኢትዮጵያ ሳትድን ተዋህዶ አትድንም። የኢትዮጵያን ጉዳይ ወደ ጎን ገፍቶ ዳር ዳሩን መዞር ግን አሁንም ቀልድ ነዉ።ኢትዮጵያን ሳያድኑ ተዋህዶን ከሚያጠፋት አቢይ አህመድ ጋር መደራደር ዝም ብሎ ለ33 ዓም እንደሆነዉ ግዴለሽነትን እና ምን አገባኝነትን መድገም ነዉ። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ሰባኪያን፡ ማህበራት እና ምዕመናን ከሁሉም በፊት የአቢይ አህመድ መንግስት ተለዉጦ በምትኩ ኢትዮጵያን የሚያድን መንግስት እንዴት ሊመጣ ይችላል ብሎ መምከር አለበት።መምከር ብቻ ሳይሆን ለዚህ ነገር እዉን መሆንም አስተዋጽኦ ማድረግም ወሳኝ ነዉ። ኢትዮጵያ ሳትድን የሚድን ነገድ ወይም የሚድን እምነት አይኖርም።ይሄን ለ27 አመታት ጽፌዋለሁ።ወያኔ አልሰማም።ወያኔ ያሸነፈ መስሎት 27 አመት በዬመጠጥ ቤቱ የዉስኪ ጠርሙስ እየጎተተ ቢያንዛርጥም :በእብሪት ታዉሮ ቢያሽካካና ቢያናፋም ወያኔ ተሸንፎ መኖበሩን ሲለቅ ግን ሁለት አመት ባልሞላ ጦርነት ብቻ 1፡2 ሚሊዮን የትግራይ ህዝብን ነዉ ያስጨረሰዉ። ወያኔ ኢትዮጵያ ጠፍታ እርሱ የኔ የሚለዉ ነገድ የሚድን መስሎት ጸረ ተዋህዶ የሆነዉን ኦነግ/ኦህዴድን እየኮተኮተ ያፋፋዉ ኢትዮጵያ ስትጠፋ እና ኦርቶዶክስ ሲጠፋ ጥፋቱ ወደ ትግራይ የማይዘምት መስሎት ነበር። ኢትዮጵያ ስትጠፋ ሁሉ እንደሚጠፋ አሁንም ብዙዉ የኢትዮጵያ ነገድ እንደ ወያኔ በእብሪት ታዉሮ ባይሆንም በምን አገባኝ ስሜት ዉስጥ ሆኖ ግን ዳር ቆሞ እያዬ ነዉ።ሀገር ሲነድ ምን አገባኝ ከማለት የከፋ ወንጀል በምድሪቱ ላይ ይኖር ይሆን? ኢትዮጵያ ሳትድን የሚድን አይኖርም የምለዉ ዝም ብዬ ለማለት አይደለም።ብቸኛ እና ብቸኛዉ የሁሉም እምነት እና ነገድ መዳኛዉ ኢትዮጵያኖ ማዳን ብቻ መሆኑን ከብዙ ትንታኔ ብኋላ ስለደረስኩበት እንጂ። አሁንም አባቶች ማህበራት እና ሰባኪያን ብሎም ምእመናን ሀይማኖት ስለ ሀገር ይጸልያል እንጂ ስለ ሀገር አያገባዉም በሚለዉ የድንዛዜ ብርድልብስ ተጠቅለዉ ተኝተዋል። ሀገረ ኢትዮጵያንም ከማዳን ይልቅ ኦርቶዶክስ ብቻዋን ትድን ይመስል ኦርቶዶክስን እና ኢትዮጵያን ከሚያጠፋዉ አቢይ ጋር ድርድርና ምክክር ይዘዋል። እናም ጥያቄዉ ፥- የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ሰባኪያን፡ ማህበራት እና ምዕመናን እራሳችሁን ከ33 አመታት በላይ ማታለሉ አይበቃችሁም? የሚል ነዉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply