You are currently viewing #የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አከርካዋን ሰብረዋል ያለው  ወያኔ/ኢህድግ ሙቶ እንኳን መንፈሱ  ሀገር እያወከ ይገኛል‼ ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የወያኔ  ተወላጅ…

#የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አከርካዋን ሰብረዋል ያለው ወያኔ/ኢህድግ ሙቶ እንኳን መንፈሱ ሀገር እያወከ ይገኛል‼ ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የወያኔ ተወላጅ…

#የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አከርካዋን ሰብረዋል ያለው ወያኔ/ኢህድግ ሙቶ እንኳን መንፈሱ ሀገር እያወከ ይገኛል‼ ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የወያኔ ተወላጅ የሆነው ብልፅግና ከኢህደግ ስብራት የተረፈችውን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር ንቅልፍ አጥቶ እየሰራ ይገኛል። #ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሀገረ ኢትዮጵያን መሪ እንዳታጣ መሪዎቿን በቀለምና በስነ ምግባር በጥበብ በሞገስ አስተምራ ፣ አሳድጋ ፣ ቅባ ሜሮን ቀብታ ፣አንግሳ፣ያጠፉትን ነገስታት እየገሰፀች ኢትዮጵያን ያቆየች የሀገር ባለውለታ ነበረች። #ቅድስት ቤተክርስቲያ ቁርበት እየፋቀች ቀለም እየበበጠች ከፍትሐ ነገስት እስከ ፍትሐ ብሄር ድረስ ታሪክና ድርሳንን እየፃፈች ሊቃውንቶቿን በጦር ግባር እያዘመተች ኢትዮጵያ እንዳትደፈር አድርጋ የኖረች የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን ባለውለታ ናት። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለሀገር ያበረከተችው ውለታዋ እንደመርገም ጨርቅ ተቆጥሮ በወያኔ ሃያ ሰባት አመት በሸኔ ብልፅግና አምስት አመት ከድዮልቅልጥያኖስ ዘመን የከፋ ማሳደድ እየደረሰባት ይገኛል። የብልፅግናው ሊቀ መንበር አቢይ አህመድ አሊ ኦርቶዶክስ ሀገር ናት እያለ በአፉ እየዘመረ እየተናገረ፤ በተግባር ሀገር ያላትን ቤተ ክርስቲያን እያፈረሳት ይገኛል። ከኢትዮጵያ በፊት ተዋህዶን እናፍርስ። ይህ የከሃዲው ብልፅግና መርህ ወንጌል ነው። የሀገር መፍረስ መልክቱ አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታን ይመስላል። የታላቋ ሶቪት ህብረትና የይጎዝ ላቢያን የመፍረስ አደጋ የገጠማቸው የላቲን አሚሪካ ሀገራት የተለያዩ ሀገሮችን ታሪክ ስንመለከት፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሀገር እየመራ ያለው ብልፅግና ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ይዟት እየሞተ እንደሆነ ምልክቶቹ ይታያሉ። መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው የሚለው የወያኔና የኦነግ ህገ መንግስት አሁን በስልጣን ላይ ላለው ሰው በላው ብልፅግና ከሃይማኖቱ መጋረጃ በስተጀርባ ሁኖ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ቁማር እንዲጫዎት አግዝቶታል ። ብልፅግና የኦሮሞ ሸኔና ቄሮዎች መንገድ ሲዘጉ፣ሰው ሲገድሉ ቤተ ክርስቲያን ሲያቃጥሉ የነበሩትን ሃይማኖት የሌላቸው ግለሰቦችን አመንኩሶ፤ ዓለምን ንቀው ሳይሆን ዓለም የናቀቻቸው ሽፍቶችን አደራጅቶ ወያኔ በመቀሌ በዘር የተለከፉ የህወሃት የፖለቲካ ሰለባ የሆኑ ድኩማንን አደራጅቶ ”የትግራይ መነበረ ሰላማ” በሚል የሚንቀሳቀሱ ኢትዮጵያ ሀገራችን አደለችም የሚሉ ሀገረ ትግራይና ሀገረ ኦሮምያ በምትናፍቃቸው ሰዎች የሌላ ሀገር ምስረታ እየተከናዎነ ይገኛል። በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የጨረቃ ጳጳሳት እና በአኩሱም እየተፈፀመ ያለው ቤተ ክርስቲያንን የማፍረስ ተግባር የሀገር ምስረታ ምልክት የኢትዮጵያ ህዝብ በሃይማኖት በዘር ሳይከፋፈል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን የሚያድንበት ጊዜው አሁን ነው። ኦርቶዶክስን ማዳን ሀገር እንደማዳን ይቆጠራል። በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ቤተ ክርስቲያንን አፍርሸ እቀመጣለሁ መስሎት ከሆነ ስህተት ነው። አዲስ አበባ ላይ ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ህዝብና ካህናትን ሰብስቦ ኮሚቴ አዋቅሮ ስልጣኑን ያስረክብ። ቤተ ክርስቲያኒቱን መምራት አልቻለም። በህብረት እንቁም። ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እናድን እላለሁ ። ኢትዮጵያንና ሕዝቦን እግዚአብሔር ይባርክ ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply