
የኦሮሙማው አገዛዝ “ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ወይም ለማፍረስ የአንድነት ምሰሶዎቿን የማፍረስ” ስልትን እየተከተለ መሆኑን ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የዐማራ ሕዝብ ሲቪክ ድርጅት በታላቋ ብሪታኒያ በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ:_ “ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ወይም ለማፍረስ የአንድነት ምሰሶዎቿን የማፍረስ” በዐድዋ ጦርነት ጊዜ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ከሀሉም ዘር የበላይ ነኝ ይል ለነበረው መላው የአውሮፓ ነጭ ሕዝብ ውርደትን በሚያከናንብ ሁኔታ የተሸነፈው የፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ለሁለተኛ ጊዜ በ1928 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ሲወር እንደዋና የጦርነት መርህ ነድፎት የተነሳው ከላይ በርዕሡ የተገለፀውን መርዘኛ የጦርነት መመሪያ ነበር። ፋሺስቱ የኢጣሊያ መንግሥትም ሆነ “እንዴት ነጭ በጥቁር ይሸነፋል” ብለው የተቃጠሉ የአውሮፓ ዘረኞች ባደረጉት ጥናት (የእነ ሮማን ፕሮቼስካን ” አቢሲኒያ የባሩድ በርሜል” የሚለውን መጽሐፍ ያስታውሷል) ኢትዮጵያን ተቆጣሮ በቅኝ ግዛትነት ለመግዛት ሦስት ተቋማት መጥፋት አለባቸው ብለው ደምዳሜ ላይ ደረሱ። በእነርሱ የጥናት ግኝት መሠረት ለኢትዮጵያ አንድነት ምሰሶ የሆኑና መጥፋት አለባቸው ተብሎ የተወሰነባቸው እነዚህ ሦስት ተቋማት:- 1) ኢትዮጵያውያንን በአንድነት ጥላ ሥራ ያሰባሰበው ዘውዳዊው ሥርዓት፣ 2) ለኢትዮጵያ አንድነት ዘብ የሆነው የዐማራ ሕዝብ፣ 3ኛ. የዐማራው ሕዝብ ርዕዮተ – ዓልም (deology) ነች ብለው የፈረጁት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ነበሩ። ዘውዳዊው ሥርዓት በእነርሱ ሥውር ተልዕኮና በዘመኑ ትውልድ አርቆ አለማስተዋል በ1966ቱ አብዮት እንዲፈርስ ተደረገ። ሁለቱን የአንድነት ምሰሶዎች ደግሞ ወያኔ እንዲያፈርስላቸው በማንኛውም መልኩ እየረዱ ለ27 ዓመታት የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል። የወያኔ ወራሽ የሆነው የኦነግ ብልፅግና መንግሥት ደግሞ ላለፉት አምሥት ዓመታት ከወያኔ በከፋ ሁኔታ በእነዚህ ሁለት የኢትዮጵያ አንድነት ምሰሶዎች ላይ ዘምቶ አሰቃቂ እልቂትና ውድመት እየፈፀመ ነው። ላለፈት አምሥት ዓመታት የብልፅግና ፓርቲ በሚል ስም በትረ – ሥልጣኑን የተቆጣጠረው የኦነግ ኃይል ሥልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ በየቦታው በግፍ የታረዱና የተፈናቀሉ የዐማራ ተወላጆች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ነው። አብሮ ጎን ለጎን እንድትጠፋ ዘመቻ የተከፈተባት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተከርስቲያንም ብዙ አብያተ ከርስቲያኖቿ ሲቃጠሉ፣ አያሌ ካህናትና ምዕመኖቿም በግፍ ታርደዋል። በዓላቷንም እንዳታከበር ከልከላና መዋከብ እየተፈፀመባት ከመሆኑም በላይ የበዓላት ማክበሪያ ይዞታዎቿ ሀሉ በተረኞቹ አሕዛቦች እየተነጠቀች ነው። በኦሮሙማ መርሑ መሠረት ዐማራን፣ ኦርቶዶከስ ሃይማኖትን፣ ብሎም ኢትዮጵያን በማጥፋት በኢትዮጵያ ከርሠ – መቃብር ላይ ታላቋ ኦሮሚያን ለመመሥረት ታጥቆ የተነሳው የብልፅግና/ኦነግ ኃይል ከሰሞኑ ዘመቻውን በሁለቱ የአንድነት ምሰሶዎች ላይ አጠናክሮ በመቀጠል ወደ መጨረሻው ግቡ እየገሰገሠ ነው። በአንድ በኩል ዐማራን አጥፍቶ የዐማራን ርስት ለመዋጥ ሲል በተደጋጋሚ እየወረረ ያወደማቸውን የሰሜን ሸዋ ከተማዎች አሁንም በመወረር እያወደመ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያን ሕዝብ በዕምነት አሥተሣሥራ አንድ በማድረጓ ኢትዮጵያን ለማፍረስ በሚፈልጉ ኃይሎች ጥርስ ውስጥ የገባቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ለመጨረሻ ጊዜ ለማፍረስ ዓይን ባወጣ ሁኔታ በመንግሥት የታገዘ መፈንቅለ – ሲኖዶስ አድርጓል። ይህ ሃላፊነት የጎደለውና በማን አለብኝነት አየተወሰደ ያለ እርምጃ ሕዝብን ከሕዝብ የሚይስተላልቅ እኩይ እርምጃ ከመሆኑም በላይ፣ ከአፍንጫው ርቆ ማየት የመይችለው የደንቆሮ ስብስብ መንጋ አልታየውም እንጅ ለራሱ ለመንግሥት ተብየውም ከፍተኛ አደጋን የሚጋብዝ እኩይ ድርጊት ነው። አርቀው በማያዩና በማያስታውሱ ደናቁርት የተለኮሰው ይህ እሣት ዐማራውንና የኦርቶዶከስ ቢተከርስቲያንን ብቻ አቃጥሎ ይቆማል ተብሎ ታስቦ ከሆነ ከፍተኛ ስህተት ነው። ስለዚህ አባቶቻችን “ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ…” እንደሚሉት፣ መንግሥት ተብየው ሆይ የጫርካትን የጥፋት ከብሪት ለራስህ ስትል አጥፋት እንላለን። ማውራት እንጅ የማያዳምጠውና የማያስተውለው የብልፅግና መንግሥት፣ ሀገር ሠሪውንና የአንድነት ዋልታ የሆነውን የዐማራ ሕዝብ በመግደል፣ በማፈነቀልና በማሠር፣ የዐማራን ከተሞች በእሣት በማውደምና በግጭት አዙሪት ውስጥ በመክተት ሰላም፣ ልማትና የሀገር አንድነትን ማምጣት በፍፁም አይቻልም! ትሕነግ መራሹ የኢሕአዴግ አገዛዝ የዐማራ ሕዝብ ትግል በፈጠረው ግፊት ተወግዶ የተረኛዉ የብልፅግና/ኦነግ አስተዳደር ከተተከለ አምሥት ዓመታት አስቆጥሯል። በእነዚህ አምሥት ዓመታት ውስጥ በጥቅሉ በሀገራችን ኢትዮጵያ፣ በተለየ ሁኔታ ደግሞ በዐማራ ሕዝብ ላይ ሥፍር ቁጥር የሌለዉ መንግሥታዊ የጀምላ እልቂት እስካሁኗ ሰዓት ድረስ እየተፈፀመ ይገኛል። በአሁኑ ስዓት መላዉ የዐማራ ሕዝብ መንግሥት ተብየው አካል በከፈተው ግልፅ የዘር ፍጅት የኅልዉና አደጋ ተጋርጦበታል። በተለይም የመንግሥት ቀዳሚ ተግባር የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ማስከበር መሆን ሲገባው፣ ባለመታደል ግን ባዛሬዋ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ጊዜ ንፁሃን ዜጎች በማንነታቸው በመንግሥታዊ የሽብር ቡድኖች ሲገደሉ፣ ከቀያቸው ሲፈናቀሉና ሃብት ንብረታቸው ሲወድም መመልከት የተለመደ የየዕለት ተግባር ሆኗል። ይህ መንግሥታዊ የጀምላ የዘር ጭፍጨፋ ከላይ ከቁንጮው ጀምሮ መንግሥታዊ መዋቅሩን በተቆጣጠሩ ዘረኛ የጥፋት ኃይሎች በቀጥታ እየተፈፀመ የሚገኝ መሆኑ ገሃድ የወጣ ዕውነታ ነው። ባለፉት ስድስት ቀናት ውስጥ በዐማራ ከልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች በተለይም በጀውሃ፣ ሰንበቴ፣ አጣዬ፣ ቀወትና ሸዋሮቢት አካባቢ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ሰርገው በገቡ አካላት ጭምር የሚደገፉ ኃይሎች በዐማራ ልዩ ኃይል እና ፌደራል ፖሊስ ካምፖች ላይ በከፈቱት ድንገተኛ ጥቃት በርካታ የፀጥታ እና ደህንነት ኃይሎች በግፍ ተጨፍጭፈዋል። እነዚህ ኃይሎች በልዩ ኃይል እና በፌደራል ፖሊስ ላይ ጥቃት በመፈፀም ሳይገቱ በአካባቢው ንፁሃን ነዋሪዎች ላይ ሳይቀር ከፍተኛ ጥቃት እየፈፀሙ ይገኛሉ። ያለማቋረጥ እየተፈጸመ ያለዉን መንግሥታዊ የዘር ጭፍጨፋ ታላቁ የዐማራ ሕዝብ ከልክ ባለፈ ትዕግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየተከታተለዉ ቢሆንም፣ ይህን እንደፍራቻ የቆጠረዉ ተረኛዉ የብልፅግና/ኦነግ መንግሥት በዐማራ ሕዝብ ላይ የጀመረዉን የዘር ፍጅት ከመቼዉም የበለጥ አጠናክሮ ቀጥሏል። ይህ የጭካኔ ተግባር የታላቁን የዐማራ ሕዝብ ትዕግሥት የሚፈታተን ኃላፊነት የጎደለዉ አረመኔያዊ ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል። በእርግጥ ይኸንን ጥቃት የመመከት ሃላፊነት የዐማራ ክልላዊ መንግሥት አሥተዳደር ቢሆንም፣ የክልሉ መንግሥት ከተጠናወተው የአጎብዳጅነት በሽታ ባለመፈወሱና ከገባበት የሤራ ፖለቲካ ቁማር ባለመዉጣቱ ምክንያት አፋጣኝ እና ቆራጥ እርምጃ መውሰድ ሲገባው ባለመውሰዱ አጣዬና አካባቢው ለኛ ጊዜ ከፍተኛ ውድመትና እልቂት እየደረሰበት ይገኛል። ስለሆነም፦ 1) የክልሉ አሥተዳደር ከኦነግ አሽከርነት ራሱን ነፃ አውጥቶ እመራዋለሁ የሚለውን ክልል ሰላም እና ደህንነት የማረጋገጥ ከማንም በላይ ኃላፊነት እንዳለበት የዐማራ ሕዝብ ሲቪክ ድርጅት በጥብቅ ያስገነዝባል፤ 2) የክልሉ መንግሥት ችግሩን ከሥረ- መሠረቱ ለመፍታት እና አካባቢውን ከኦነግ የሽብር ቡድን ነፃ በማድረግ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ አስቀድሞ በጥናት ላይ የተመሠረተ እርምጃ አለመውሰዱ ለችግሩ ተደጋጋሚ መከሰት ዋና ተጠያቂዉ የዐማራ ከልላዊ መንግሥት መሆኑን የዐማራ ሕዝብ ሲቪክ ድርጅት በዕኑዕ ያምናል፤ 3) ለዐማራው ክልል ሰላም መታጣት አንዱ ምክንያት በክልሉ ውስጥ ያለአግባብ የተዋቀረው የከሚሴ ልዩ ዞን ነው። በመሆኑም ኦነግ ይህንን ልዩ ዞን በመጠቀም ዐማራን በየጊዜው በግፍ እያረደ ነው። በማንኛውም ክልል ያልተሰጠ የልዩ ዞንነት ዕድል በዐማራ ክልል እንዲፈጠር የተደረገው ሆን ተብሎ የዐማራውን ርስት ለመንጠቅ ሲባልና ዐማራውን ዘላለማዊ አርፍት ለመንሣት ሲባል በወያኔና ኦነግ የተሸረበ ሤራ ነው። ስለሆነም የዐማራ ክልላዊ መንግሥት ይህንን በተንኮል የተዋቀረ የከሚሴ ብሔረሰብ አስተዳደር ልዩ ዞን በአስቸኳይ በማፍረስ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ በመወጣት ቁርጠኛ እርምጃዎችን እንዲወስድ እና ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን እንዲፈፅም በጥብቅ እንጠይቃለን፤ 4) በሰሜን ሸዋ ዞን ጀዉሃ በጀግናዉ የዐማራ ልዩ ኃይል እና በፌደራል ፖሊስ ካምፕ በተፈፀመዉ ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት በርካታ የፀጥታ አባላት በሤራና በግፍ ተረሽነዋል። በዚህ ሤራ ተሳትፈው በተገኙ አመራሮች ላይ አፋጠኝ አርምጃ አንዲወሰድ እንዲሁም በአጣዬና አካባቢዉ በንፁሃን ወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ የሚገኘዉ መንግሥታዊ የግዛት ማስፋፋት ወረራ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ 5) የ27ኛውን የዐድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ-በዓል ቀደም ብሎ ሲከበርበት ወደነበረዉ የአፄ ምኒልክ አደባባይ ተመልሶ እንዲከበርና ሕዝቡም የነፃነት ምልክቱ የሆነውን የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ ያለማንም ከልካይ በነፃነት ይዞ ማከበር እንዲችል እንጠይቃለን፤ 6) ከጥምቀት በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ ከየቤታቸው እየታፈሱ በግፍ የታሠሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፤ 7) ተረኛው የብልፅግና/ኦነግ መንግሥት የፍትህ ሥርዓቱን የፖለቲካ መሣሪያ አድርጎ መጠቀሙን እንዲያቆም፣ 8 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ አየተሸረበ ያለዉን መፈንቅለ ሲኖዶስና ኤጲስቆጶሳትን የማሳደዱንና የማዋከቡን ዘመቻ እያወገዘን፣ መንግሥትም እጁን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ቤተከርስትያን ላይ እንዲያነሳና ይልቁንም የመንግሥትነት ሃላፊነት ቅንጣት ታከል የሚሰማው ከሆነ ኢ-ቀኖናዊ በሆነ ሁኔታ መፈንቅለ ሲኖዶስ አካሂደው ሀገር በማፍረስ ላይ በተሠማሩ ሕገወጥ ቡድኖች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ በአፅንዖት እንጠይቃለን፤ 9) የኦነግ/ ብልፅግናው መንግሥት በዐማራው ሕዝብ ላይ የሚፈፅመውን ለከት የለሽ የዘር ፍጅት በአስቸኳይ እንዲያቆም በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ አንድ ዐማራ፣ ለሁሉም ዐማራ፤ ሁሉም ዐማራ ለእያንዳንዱ ዐማራ!
Source: Link to the Post