You are currently viewing # የኦሮሙማው ገዳይ ሃይል ሸዋን ለመሰልቀጥ ተደጋጋሚ ትንኮሳ እያደረገነው ተባለ። መጋቢት 09 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከሰሞኑ ተደጋጋሚ ትንኮሳ ሲያደርግ የቆየው የኦሮሙማው ገዳይ…

# የኦሮሙማው ገዳይ ሃይል ሸዋን ለመሰልቀጥ ተደጋጋሚ ትንኮሳ እያደረገነው ተባለ። መጋቢት 09 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከሰሞኑ ተደጋጋሚ ትንኮሳ ሲያደርግ የቆየው የኦሮሙማው ገዳይ…

# የኦሮሙማው ገዳይ ሃይል ሸዋን ለመሰልቀጥ ተደጋጋሚ ትንኮሳ እያደረገነው ተባለ። መጋቢት 09 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከሰሞኑ ተደጋጋሚ ትንኮሳ ሲያደርግ የቆየው የኦሮሙማው ገዳይ ሃይል መጋቢት 5/2015 ዓ/ም ሰሜን ሽዋ ሃላላ በምትባል ቦታ ዘልቆ በመግባት የአርሶ አደሮችን ከብት ዘርፎ ለመሄድ ሲሞክር በፋኖዎች ጥምረት ሳይሳካለት መቅረቱን ቦታው ላይየነበሩ ፍኖዎች ገልፀዋል። በመንግስት ድጋፍ የሚደረግለት አሸባሪው የኦሮሙማ ሃይል ከሰሞኑ ሸዋ ላይ ጥቃት ለመፈፀም ከፍተኛ የሆነ የፀብ አጫሪነት ሙከራ እያደረገነው ተብሏል። ትንኮሳው ድንገት የተከሰተ ሳይሆን ታስቦበት እና ስምሪት ተሰጥቶት ነው ሲሉ የገለፁት ፋኖዎቹ ለዚህ ማሳያው ደግሞ በሃይል ከገበሬው ተነጥቀው የተወሰዱትን ከብቶች ለማስመለስ ጥረት በምናደርግበት ወቅት የመከላከያ ሰራውይት ፋኖን ከበባ ውስጥ በማስገባት ጥቃት ለመፈፀም ሙከራ አድርጓል ሲሉ አብራርተዋል። በመሆኑም ይህ ለዳግም ጭፍጨፋ የተሰማራው ገዳይ ሃይል መጋቢት ከ6/2015 ዓ/ም ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊት መኪና እየተጫነ መግባቱን ገልፀው በዚህም ምክንያት የአካባቢው ማህበረሰብ ስጋት ውስጥ መውደቁን ለአሻራ ሚዲያ ጠቁመዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply