የኦሮሙማ ማኔፌስቶ!!! ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫ ዉጡ!!! አዲስ አበባን ለማዳን ጊዜው አሁን ነው!!! (ክፍል አንድ) ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

አዲስ አበባን ለማዳን ጊዜው አሁን ነው!!! ለባልደራሱ አንበሳ ስክንድር ነጋና ለፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ይሁን፡፡  

#1-አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያንና የአፍሪካዊያን ህዝቦች የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የባህል ማዕከል ሆና በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡ አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ፣ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መናህሪያ፣ የተለያዩ ሃገራቶች ኢንባሲዎች፣ ቆንስላዎች መገኛ፣ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴሎች፣ ባንኮች፣ ሆስፒታሎች፣ ዩኒቨርቲዎች፣  ወዘተ  ህብረብሔር ሀዝብ የሚኖሩባት ከተመ ናት፡፡ አዲስ አበባ ከተማ 1889 እኤአ የኢትዮጵያ ዋና መዲና ሆና በእቴጌ ጣይቱ ከተቆረቆረች ጀምሮ የሸወ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ ለመቶ ሁለት ዓመታት  እንደነበረቸ ታሪካዊ ምረጃዎች ይገኛሉ፡፡ ህወሓት ኢህአዴግ በ1991 እኤአ ሥልጣን እንደጨበጠ ኢትዮጵያን በዘጠኝ ክልሎች ሸንሽኖ ወልጋዳ ካርታ በመንደፍ ሃገሪቱን ወደማያባራ የክልሎቸ ድንበር  ግጭት ለሠላሣ ዓመታት በማስቀጠል የሰው ልጆች በዘራቸው ምክንያት የሚገደሉበትና የሚታረዱበት ሥርዓት በመዘርጋት የወያኔና ኦነግ ነፍሰገዳዬች ለዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለማቅረብና አዲስ አበባን ለማዳን ጊዜው አሁን ነው፡፡ According to the Ethiopian Constitution, Addis Ababa has a power of self-administration and is governed by the Addis Ababa City Government Revised Charter, Proclamation No. 361/2003. Addis Ababa City is divided into 10 sub-cities and 116 woredas under the sub-cities.

 

#2-የኢትዮጵያ አመታዊ ጥቅል ምርት (Gross Domestic Product)፡- የኢትዮጵያ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት በቢሊዮን ዶላር GDP  በ2015 (64.6)፣ 2016 (74.3)፣ 2017 (81.8)፣2018 (84.3)፣ 2019 (96) ቢሊዮን ዶላር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2011ዓ/ም  2.2 (ከሁለት ነጥብ ሁለት) ትሪሊዮን ብር (75.9 ቢሊዮን ዶላር)፣ በ2012 የበጀት ዓመት 3.37 (3.4) ትሪሊየን ብር (94.4 ቢሊዮን ዶላር) ጠቅላላ አገራዊ ምርት ተመዝግቦለ፡፡ ወያኔ ኢህአዴግና  ኦነግ ብልፅግና  የአዲስ አበባ ከተማ   በሃገሪቱ ኢኮኖሚ የሚያበረክተውን የአንበሳ ድርሻ ለመቆጣጠር ከተማዋ የምታመነጨውን ኃብት  ወያኔና ኦነግ የመዲናዋን ኢኮኖሚውን ለመቆጣጠር ያላገላበጡት ድንጊያ አይገኝም፡፡

 

#3- የአዲስ አበባ ከተማ  አመታዊ ጥቅል ምርት ወይም አመታዊ አማካይ አጠቃላይ ምርት (ጂዲፒ) በ2011እኤአ 85 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን በ 2017እኤአ አመታዊ ጥቅል ምርቱ 165 ቢሊዮን ብር ደርሶ ነበር፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ንዋሪዎች የነፍስ ወከፍ ገቢም  2086 ዶላር  ተገምቶ ነበር በ2020 እና 2021 ስንት ሊደርስ እንደሚችል መገመት አያዳግትም፣ለዚህ ነው የአዲስ አበባ ነገር የማትዋጥ የማትተፋ የጉሮሮ ላይ አጥንት የሆነችው፡፡ The gross domestic product (GDP) of the city government has shown an increase from ETB 85.1 billion in FY2011 to ETB 164.77 billion in FY2017. The per capita income has also reached US$2,086 in the budget year of 2016/2017. የአዲስ አበባ ከተማ ህብረ ብሔራዊ ኃብት እንጂ የአንድ ብሔር ኃብት ለማድረግ ከህወሓት ማኒፌስቶ እስከ በኦሮሙማ ማኔፌስቶ አላዋቂ ምሁራን የስግብግብነትና የሰቀቀናምነት ስሜት በመነሳት ሻሸመኔን፣ አጣዬን፣ ካራቆሬን፣ ማጀቴን፣ የማቃጠልና የማውደም የተቀናጀ ዘመቻ መንግሥት መር በመሆኑ ምክንያት መጥፋት ባለመቻሉ  የዘር ፍጅቱ (ጆኖሳይድ)ና የስብዓዊ መብት ጥሰቶች ሆን ተብሎ የሚደረጉ በመሆናቸው፣  የኦዴፓ ብልጽግና መንግሥት መወገድ አለበት አንላለን፡፡ የኦነግ ብልፅግና ህብረ ብሔር ህዝብ የሚኖርባቸውን ከተሞች ከማቃጠልና ከማውደም ወደኃላ ስለማይሉ ጥንቃቄ ለደብረዘይት፣ ናዝሬት፣ አሰላ፣ ሻሸመኔ፣ ጅማ፣ ድሬዳዋ፣ ሃርር፣ ባሌ፣ ሮቤ፣ ወዘተ እንላለን፡፡ የኦነግ/ኦህዴድ ብልፅግና አስር ሚሊዩን ካድሬዎች ባንክ ከመዝረፍ፣ ግለሰቦች ከመንጠቅ ሌላ ለሃገር ያበረከቱት ሥራ የለም ፣ ግብረገብነት ከጎደለው የቦዘኔ ሥራቸው  ውጪ የሚያውቁት አንዳችም ነገር የለ እንላለን፡፡

የአውሮፓ ህብረትና የአሜሪካ መንግሥት በትግራይ ጦርነት እንዲቆም፣ ለርሃብተኛው ወገን የስብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ፣ የኢትዮጵያ ምርጫ ነጻና እንከን የለሽ ምርጫ ባለመሆኑ ታዛቢ አንልክም ብለዋል ለተፎካካሪ ፓርቲዎች አንባገነን የኦዴፓ ብልፅግናን መንግሥት ለማጋለጥ  ወርቃማ አጋጣሚ ነው እንላለን፡፡ ኤርትራና ሱዳን የጣሰውን ሉዓላዊነት፣ ሉዓላዊነታችን ተጣሰ በማለት የብልፅግና ማላዘን ነገር ማስቀየሻ በመሆኑ ከምርጫው ተፍካካሪ ፓርቲዎች በመውጣት ታሪክ ሥሩ እንላለን፡፡ ተወዳድራችሁ ኦዴፓ ብልፅግና ካነገሳችሁ በኃላ  ማልቀስ ‹‹የውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን!!!›› ስለምርጫ አናንሳ ይለችኃል ህዝብ፡፡ አዲስ አበባን ለማዳን ጊዜው አሁን ነው!!!   

#4- የአዲስ አበባ ከተማ የኢኮኖሚ ዘርፎች፡- በ2016/2017 እኤአ የአዲስ አበባ ከተማ አጠቃላይ ኢኮኖሚ ዘርፍ ውስጥ የግብረና ዘርፍ ድርሻ 1.73 ቢለዮን ብር (1.16 በመቶ)፣ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ድርሻ 33.24 ቢሊዮን ብር (20.43 በመቶ)፣ የአገልግሎት ዘርፍ ድርሻ 122.04 ቢሊዮን ብር (78.4 በመቶ) የነበረ ሲሆን አመታዊ ጥቅል ምርቱ 165 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡ ወያኔ እና ብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ከተማን ኃብትና ንብረት ተቆጣጥሮ ለመዝረፍ አስር ሚሊዮን ‹አይሸምቴን ምን አከሳው› የፖለቲካ ካድሬዎች ለአለፉት ሠላሳ አመታት የመዘበሩት አልበቃ ብሎቸው ህዝቡን ለጦርነትና ለርሃብ በመዳረጋቸው በቃችሁ ልንላቸው ይገባል፡፡ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የህዝቡን ጥያቄ ስምታችሁ የፓርላማ ውስጥ የንጉስ አጫዋች ከመሆን ያውጣችሁ እንላለን፡፡ እነ ታከለ ኡማ፣ አዳነች አቤቤ፣ ሽመልስ አብዲሳ ወዘተ ጢባጢቤ የሚጫወቱበት ገንዘብ የግብር ከፋዩ ህዝብ አንጡራ ኃብትና ንብረት መሆኑን የሚረዱት ካድሬዎች በዚህ ምርጫ ባለመሳተፍና የውይይትና የድርድር መድረክ ሲመቻች ብሎም ሥልጣናቸውን ሲያጡ መሆኑን አንጠራጠር፡፡ የፖለቲካ ካድሬ ሥርዓት ማክተሜው ዘመን 2014 ዓ/ም ነው፡፡  The contribution of the economic sectors for the development was(a) agriculture contributing ETB 1.73 billion, (b) industry – ETB 33.24 billion, and (c) the service sector – ETB 122.04 billion in the FY 2016/2017. In addition, the GDP of the city government has shown an increase of 11.19 percent in the same year. (The gross domestic product (GDP) ETB 164.77 billion in FY2017.) The sectors that have contributed to the economic development of the city were the service sector with a lion’s share of 78.4 percent, industry of 20.43 percent, and others related to agriculture of 1.16 percent……………….(1)

#5- የአዲስ አበባ ከተማ የገቢዎች አስተዳደር፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች አስተዳደር የሚሰበስበው ግብር ከሃገር ውስጥ ቀጥተኛ ታክስ፣ ቀጥተኛ ካልሆነ ታክስ፣ እንዲሁም ከማዘጋጃ አገልግሎት ክፍያ ገቢ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2013ዓ/ም 336, 173 የተመዘገቡ ግብር ከፋየች አሉት፡፡ ከዚህ ውስይ አንደኛ ደረጃ ግብር ከፋዬች 69,319 ነጋዴዎች፣ ሁለተኛ ደረጃ ግብር ከፋዬች 46,981 ነጋዴዎች፣ ሦስተኛ ደረጃ ግብር ከፋዬች 219,873  ነጋዴዎች ይገኙታል፡፡  የአዲስ አበባ ግብር ከፋይ ህዝብ ከተማዋን የማስተዳደር መብትና ነፃነት ከማንም በላይ አለው፡፡ የብልጽግና አስር ሚሊዮን ካድሬ በግብር ከፋዩ ህዝብ ላይ ለሠላሳ አመታት እንደ መጅገር ተለጥፎ ደም የሚመጥበት ዘረኛና ተረኛ የፖለቲካ ሥርዓት   ዘመን በህዝባዊ እንቢተኛነት በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ፣ ከምርጫ በመውጣት፣ ድምፅ ባለመስጠት ማክተምና መጋለጥ አለበት እንላለን፡፡ Currently there are 336,173 registered under the Addis Ababa City Government Revenue Authority. The report indicated that out of the total, 69,319 are category A or large tax payers, while 46,981 are category B or medium tax payers and the remaining 219, ngadywoce B tax payers annual turnover in between 100,000 – 500,000 birr. While those with the turnover of less than 100,000 birr are grouped under category C…………(2)

 

#6- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እራሱ ገቢ የሚተዳደር ሲሆን ከፌዴራል መንግስቱ የሚደጎመው ባጀት የለውም፡፡ በከተማው የሚሰበሰበው ግብርና ታክስ  በ2014/2015 እኤአ  26 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን በ 2017/2018 እኤአ 33.07 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሎ የነበረ ሲሆን አሁን 40 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን በሚቀጥሉት አመታት ውስጥ 60 ቢሊዮን ብር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ የገቢዎች ድርሻ ከአመታዊ ጥቅል ምርቱ 14.2 በመቶ አመታዊ እድገት ነበረው፡፡ The city government is a self-financed entity, which does not receive a subsidy from the federal government except from the Federal Road Fund as a specific grant for maintenance and construction of roads. The revenue collected from taxes has reached ETB 33.07 billion in FY2017/2018 from ETB 26 billion in FY2014/2015…. The revenue contribution to GDP of the city government is still 14.26 percent.

 

#7-  የአዲስ አበባ ከተማ ኢኮኖሚ አጠቃላይ ገቢውና አጠቃላይ ወጪው ከሃገሪቱ አመታዊ ጥቅል ምርቱ (ጂዲፒ) በመቶኛ ሲሰላ የነበር ድርሻ ለመመልከት

  • የአዲስ አበባ ከተማ በ2015/2016እኤአ አመታዊ ጥቅል ምርቱ (ጂዲፒ) 141.01ቢሊዮን ብር ሲሆን አጠቃላይ ገቢው የጂዲፒውን 18.93 በመቶ ሲሆን አጠቃላይ ወጮው የጂዲፒው 15.77 በመቶ ነበር፡፡
  • በ2016/2017እኤአ አመታዊ ጥቅል ምርቱ (ጂዲፒ)157.03 ቢሊዮን ብር፣ ሲሆን አጠቃላይ ገቢው የጂዲፒውን 18.68 በመቶ ሲሆን አጠቃላይ ወጮው የጂዲፒው 17.47 በመቶ ነበር፡፡
  • በ2017/2018 እኤአ አመታዊ ጥቅል ምርቱ (ጂዲፒ)164.77 ቢሊዮን ብር ሲሆን አጠቃላይ ገቢው የጂዲፒውን 20.53 በመቶ ሲሆን አጠቃላይ ወጮው የጂዲፒው 18.21 በመቶ ነበር፡፡ (Source: Addis Ababa BoFED Accounts and Treasury Directorates.)

 

#8-የአዲስ አበባ ከተማ  በትምህርትና በጤና ዘርፍ ከፍተኛ እድገት አስገኝቶል፡፡ በዚህም መሠረት በከተማዋ ውስጥ 1,168 የህፃናት መዋያዎች፣ 806 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ 217 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ፡፡ በጤና ተቌማት 67 የመንግሥታዊ የጤና ማዕከላት፣ ስድስት ሆስፒታል፣ ሁለት የጤና ኬላበከተማዋ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ Significant achievements have been made in Addis Ababa in the education and health sectors in recent years. At present, the numbers of preprimary schools are 1,168; primary schools stand at 806, and secondary schools are 217. The gross enrolment ratio as of 2017/2018 for preprimary, primary, and secondary schools has reached 91.93, 135.4, and 117.24, respectively. For the health Ethiopia PEFA Assessment 2018 The City of Addis Ababa 17 sector, most health clinics are privately owned. At present, there are 67 government health centers, six hospitals, and two health posts. The under-five mortality rate has reduced to 28 deaths per 1,000 live births in 2016/2017. Mortality rate of mothers has been reduced to 412 deaths per 100,000 live births. Access to safe water stood at 91.35 percent in FY2016/2017, and life expectancy is currently 67 years. 

 

#9- የአዲስ አበባ ከተማ በጀት፡- ባለፉት ሦስት አመታት አጠቃላይ ገቢው ከአጠቃላይ ወጪው ትርፋማ በመሆን ከተማዋ ያለ ፌዴራልመንግሥት ድጎማ በእራሶ ተዳደራ ነበር፡፡   ከ2015 እኤአ አጠቃላይ ገቢ 26.069 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ወጪ 22.010 ቢሊዮን  ብር ነበር፡፡ በ2016 እኤአ አጠቃላይ ገቢ 28.820 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን አጠቃላይ ወጪ 27.430 ቢሊዮን  ብር ነበር፡፡ በ2017/2018 እኤአ አጠቃላይ ገቢ 33.445 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን አጠቃላይ ወጪ 30.013 ቢሊዮን  ብር ነበር፡፡ Addis Ababa City Administration has registered budget surplus for the three consecutive fiscal years, and the expenditure of the city is financed through own revenue mainly from tax collection. The contribution of tax revenue percentage to GDP showed an average of 14.11 percent for FY2014/2015 to FY2016/2017, showing a similar trend each year.

 

#10-2014/ ኢትዮጵያ መንግሥት ዓመታዊ  በጀት 561.67(አምስት መቶ ስልሣ አንድ ቢሊዮን ስድስት መቶ ሰባ ሚሊዮን) ብር ውስጥ ለመደበኛ ወጪዎች 162 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪዎች 183.5 ቢሊዮን ብር፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ 203.95 ቢሊዮን ብር፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ 12 ቢሊዮን ብር መያዙ ተገልጿል።………….(3)

2013/ ኢትዮጵያ መንግሥት ዓመታዊ  በጀት 476 (አራት መቶ ሰባ ስድስት) ቢሊዮን ብር ውስጥ 176 (መቶ ሰባ ስድስት) ቢሊዮን ብር (37 በመቶ) ለክልሎች ድጎማ፣ 160 (መቶ ስልሳ) ቢሊዮን ብር (34 በመቶ) ለካፒታል በጀት፣ 133 (መቶ ሠላሣ ሦስት) ቢሊዮን ብር (28 በመቶ) መደበኛ በጀት እና 6 (ስድስት) ቢሊዮን ብር ለዘላቂ ልማት የተደለደለ ነው፡፡ በመደበኛው በጀት ውስጥ የሚካተተው የፌዴራልና የክልሎች የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ ኃይል ደሞዝ፣ ወዘተ ያጠቃልላል፡፡  ኢትዮጵያ መንግሥት ዓመታዊ  በጀት በዋናነት የሚገኘው ከህዝብ ከሚሰበሰብ ግብርና ታክስ ከፋዬች ኢትዮጵያዊያን ነው፡፡ ግብር ከፋዬች ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በህይወት የመኖር መብቶቹ፣ ኃብትና ንብረት የማፍራት መብቱ፣ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ የመሥራት ነጻነቱ፣ ወዘተ የሚጠበቅለት  በኢፊድሪ መከላከያ ሠራዊት (ኮማንድ ፖስት) በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መሥሪያ ቤት ሠራተኞች የሚከፈል ደሞዝና አበል ሲሆን ዛሬ በሃገሪቱ ኮማንድ ፖስት  በሰባት ቦታዎች ታውጆ በወታደራዊ አስተዳደር ስር ይሰቃያል፡፡ ኢትዮጵያ መንግሥት ዓመታዊ  በጀት አንደ ሦስተኛ ገንዘብ የሚደጉሙት የአውሮፓ ህብረትና የአሜሪካና የካናዳ ወዘተ መንግሥቶች ድጎማ የነበረ ሲሆን ዛሬ ማእቀብ ጥለዋል፡፡ ዋናው ጥያቄቸው ጦርነት አቁሙ፣ የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ ይውጣ፣ ስብዓዊ እርዳታ ያለገደብ ይዳረስ  ችግራችሁን በውይይትና ድርድር ፍቱ!! ወዘተ የሚሉ ናቸው፡፡  የኢትዮጵያ ህዝብ በጦርነትና በዘር ፍጅት በየቦታው ይታረዳል፣ ይቆስላል፣ ይዘረፋል፣ ይሰደዳል፡፡ እንደ ዘመነ ዬዲት ጉዲት፣ ዘመነ ዐብይ ጉዱ ተሸጋግረናል፡፡በመሆኑም ገዳዬቻችንን አሠልጥኖና አስታጥቆ ለሚልክብን የኦሮሙማ ሥርዓት አገዛዝ ከነሰንኮፉ እስካልተወገደ ‹‹በቃን!!! ብለን ህዝባዊ አመፁን ማቀጣጠልና ግብር ባለመክፈል እንቢተኝነት የብልፅግናን ዘረኛና ተረኛ መንግሥት አስር ሚሊዮን የፖለቲካ ካድሬዎችን መንቀል ታሪካዊ ኃላፊነታችን ነው፡፡ ከአራጆቻችን እራስን የመከላከል ተፈጥሮዊ መብታችንን በመጠቀም ማንኛውም ዓይነት ጥቃትንና የዘር ፍጅትን ለመከላከል መደራጀት የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡ አዲስ አበባን ለማዳን ጊዜው አሁን ነው!!!   

 

ምንጭ፡-

 

Leave a Reply