የኦሮሙማ ማኔፌስቶ! አዲስ አበባ ኬኛ! የኢኮኖሚ ዘርፍ የመሬት ቅርምት!የዘገነም ያልዘገነም እኩል አዘነ! (ክፍል ሦስት) ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

ከህወሓት ኢህአዴግ ኢፈርት ወደ ኦህዴድ ብልፅግና ፊንፊኔ ኬኛ፣ፋብሪካ ኬኛ፣ መሬት ኬኛ ወዘተ ተሸጋግረናል!!!

በኢትዮጵያ ከቁሳዊ ልማት በፊት ስብዓዊ ልማት ይቅደም መጀመሪያ ሰው አንሁን እንላለን፡፡ ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት መጨረሻው አያምርምና ከወያኔ ውድቀት በመማር ህዝቡን በነጻነት፣ በእኩልነትና፣ በፍቅር ያለአንዳች አድሎ ማሰተዳደር የሁሉም ፓርቲዎች ግዴታ ነው እንላለን፡፡  ህብረተሰቡን በአምራችና በገንቢ የሰው ኃይል እውቀትና ክህሎት የተገነባ ስብዓዊ ልማት ከታነፀ ለቁሳዊ ልማት ክብር የሚሠጥ ሰዎች የማያርድ፣ ባንኮች የማይዘርፍ፣ ከተማ የማያቃጥል ፈሪሃ እግዚአብሄር ያለው ትውልድ ይተካል እንላለን፡፡ ይህን ዓይነት ትውልድ እስካልፈጠርን  ከመገንባታችን በፊት እንወያይ  እንላለን፡፡ ካለዛማ በአዲስ አበባ የገነባም ያልገነባም እኩል አዘነ ይሆናል፣ የአክሱም ቀሳውስት ‹‹የዘገነም ያልዘገነም እኩል አዘነ›› እንደሚሉት፡፡ ወያኔ ኢህአዴግ ህዝብ ዘርፎ የገነባውን ህንፃዎች ተወረሠ፣ ኦህዴድ ብልፅግና ዘረኛና ተረኛ ሆኖ በአንድ በኩል ግንባታ ጀምሮል፣ በሌላ በኩል ሻሸመኔን አጣዬን ከተሞች ያቃጥላል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ፣ የአዲስ አበባ ህዝብ፣ ከምርጫው በኃላ በኦህዴድ ብልጽግና አሸናፊነት እጣ ፈንታው ምን ይሆን ይሆን!!!  ዘ-ሐበሻ ሚዲያ የተቃዋሚ ምሁራንን ሃሳባች በዴሞክራሲያዊ መንገድ በማንሸራሸርና በማስተናገድ የህዝብ ድምፅ በመሆን ለሠጡን አገልግሎት ዘ-ሐበሻ ከልብ እናመሠግናለን፡፡ ሰኔ 14ቀን 2013ዓ/ም ለኢትዮጵያ ህዝብ መልካም ምርጫ እንዲሆን እንመኛለን! እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ እንላለን!!!

‹‹የአዲስ አበባ ጉዳይ፡ 2013 ምርጫ ዋነኛ ጉዳይ›› ‹‹ላለፉት አስርት ዓመታት የፖለቲካ ፓርቲዎች ዋነኛ አጀንዳዎች መካከል የመዲናዋ የአዲስ አበባ ጉዳይ አንዱ ነው። የከተማዋ የአስተዳደር ጉዳይ፣ የከተማዋ የባለቤትነት መብት እና በሕገ-መንግሥቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ያገኛል የሚሉት ነጥቦች ብዙ ያከራክራሉ። ከጥቂት ቀናት በኋላ በሚካሄደው 6ኛው አገራዊ ምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ከአዲስ አበባ የሚወከሉ 23 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበርን ለማሸነፍ እንዲሁም ከከተማዋ 138 የምክር ቤት መቀመጫ አብላጫውን ለማሸነፍ ወደ ፉክክር የገቡት ፓርቲዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው። ለመሆኑ እነዚህ ፓርቲዎች በአዲስ አበባ ላይ ያላቸው አቋም ምንድን ነው?››

ባልደራስ፡አዲስ አበባን ራስ ገዝ አስተዳደር እናደርጋለን‹‹በእስክንድር ነጋ ‘የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት’ በሚል የተጀመረው እንቅስቃሴ ‘ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ’ ወደሚል ፖለቲካ ፓርቲነት መሸጋጋሩ ይታወሳል። መሠረቱን አዲስ አበባ ከተማ ላይ ያደረገው ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በምርጫው ድል ከቀናው አዲስ አበባ ከተማን ራስ ገዝ አስተዳደር እንደሚያደርግ አስታውቋል። ባልደራስ አዲስ አበባ ለፌደራሉ መንግሥት ተጠሪ መሆኗ ቀርቶ እንደተቀሩት ክልሎች ራሷን የቻለች ራስ ገዝ አስተዳደር እንድትሆን እሰራለሁ ይላል። ባልደራስ በሕገ-መንግሥቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ያገኛል መባሉን አጥብቆ የሚቃወም ሲሆን፤ ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ያለው ሕዝብ፣ ብሔር ወይም ክልል የለም ይላል። የኢፌድሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 49.5 የኦሮሚያ ክልል ለፌደራሉ መንግሥት ተጠሪ ከሆነችው አዲስ አበባ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅበታል ይላል። ሕገ-መንግሥቱ የኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምን እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ፤ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል የምትገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ልዩ ጥቅም ይጠበቃል ይላል።››

ኢዜማ፡ “አዲስ አበባ የነዋሪዎቿ ነች‹‹የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትሕ ፓርቲ በበኩሉ አዲስ አበባ የነዋሪዎቿ ነች የሚል አቋምን ያንጸባርቃል። “አዲስ አበባ በአስተዳደር በኩል፣ በባለቤትነት እና በመብት ጥያቄ የነዋሪዎቿ ነው” ይላል ፓርቲው። ምንም እንኳ ፓርቲው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዙሪያ በግልጽ ያስቀመጠው ነገር ባይኖርም፤ የፓርቲው መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በቅርቡ ባደረጉት ንግግር “ክልሎች የተዋቀሩበት ሁኔታ ተጠንቶ እና ሕዝቡ ተወያይቶበት የሚወሰን ይሆናል” ብለዋል። የአዲስ አበባ ጉዳይም ከክልሎች አወቃቀር እና አስተዳደር ጋር ከምርጫ በኋላ አብሮ የሚታይ እና መፍትሄ የሚያገኝ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል።››

‹‹ብልጽግና፡አዲስ አበባ የኦሮሞ ሕዝብ ርዕሰ ከተማ ናት“አዲስ አበባ ከተማ የኦሮሚያ ክልል እና የኦሮሞ ሕዝብ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ማዕከል ናት” ያሉት በሚንስትር ማዕረግ የመለስ አካዳሚ ፕሬዝደንት አቶ አወሉ አብዲ ናቸው። የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ጥቅም ያገኛል ተብሎ በሕገ-መንግሥቱ የተደነገገው መጠበቅ አለበት ይላሉ አቶ አወሉ። ምንም እንኳ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 49 የሰፈነው ኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ጥቅም የማግኘት ጉዳይ ተግባራዊ ሳይሆን ለዓመታት የዘለቀ ጉዳይ ቢሆንም አቶ አወሉ ፓርቲያቸው ብልጽግና ቀጣዩን ምርጫ ቢያሸንፍ የኦሮሞ ሕዝብ ከአዲስ አበባ ከተማ ማግኘት ስላለበት ጥቅም ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል። “ከዚህ ሽግግር በኋላ ጠንካራ መንግሥት ተቋቁሞ የኦሮሞን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ብሔር ብሔረሰቦች ጥያቄ ሙሉ በሆነ መንገድ መመለስ በሚቻልበት ሆኔታ ላይ እንሰራለን የሚል አቋም ይዘናል” ብለዋል።››……………………………(1)

‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት››

‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት›› የኦቦ ለማ መገርሳና ዶክተር አብይ አህመድ አስተዳደር የኦሮሚያ ክልል ህዝብ በአዲሱ የኦሮሚያ ካቢኔ ‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት››በሚል መርህ በኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዩት በፍጥነት ወደ ተግባር ለማስገባት፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና የኦሮሞ ባለሃብቶች ጥምረት ምክር ቤት መሥርቶ ወደ ልማት ለመገስገስ ተወጥኖ የኢኮኖሚ ፍኖተ-ካርታ ተቀርፆ በሥራ ላይ ውሎል፡፡

የኢኮኖሚ ዘርፍ የመሬት ቅርምት!!! ….መሬት አይሸጥም አይለወጥም! መንግሥት ከመሬት ባለቤትነት ይነቀል! መሬት ከፖለቲካ ካድሬዎች የኃብት ምንጭነት ይላቀቅ!!!

ኦህዴድ ብልፅግና ፓርቲ አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ የኢኮኖሚ ዘርፍ የመሬት ቅርምት በመሬት ሽሚያ ለተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መስሪያ ቦታዎች የመሠረት ድንጊያ ማስቀመጥ፣ የተለያዩ  የባህል ማዕከል ግንባታ ቦታ  በኦሮሚያ በአማራ፣ በጉራጌ ወዘተ በህዝብ ስም የመሬት ቅርምት ተጦጡፎ ይገኛል፡፡ የአዲስ አበባ የመሬት ቅርምት ፎርሙን ቀይሮና ዛሬ ፋሽኑ የአዲስ አበባ ፓርክና መናፈሻና የኢሬቻ ባህል ማክበሪያ ሰፊ ሥፍራ መቆጣጠር የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤትና የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ፅህፈት ቤት አዲሱ ፋሽን ሆኖል፡፡  በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በህወሓት ኢህአዴግ የተከናወኑ የመሬት ቅርምቶች ውስጥ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚና የመለስ ፋውንዴሽን የመሳሰሉት ተቆማት በአሁኑ ጊዜ በኦህዴድ ብልጽግና ፓርቲ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ 22 ሽህ ካሬ መሬትን ወደ  ሆስፒታልነት መቀየሩ ጎሽ የሚያስብል ቢሆንም በኦሮሙማ ማኒፌስቶ ፊንፊኔ ኬኛ የሚለውን የመስፋፋት ፖሊሲ አንዱ አካል እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ከስታዲየም ከፍ ብሎ  የዋቆ ጉቱ ፋውንዴሽን ቢሮ መከፈቱን ስንቶቻችሁ አስተውላችኃል፡፡

ዶክተር አብይ አህመድ የአዲስ አበባ ፓርክና መናፈሻ እንደ ሻሸመኔና አጣዬ እንዳይቃጠሉ ኦነግ ሸኔን በህብረ ብሔር  የአዲስ አበባ ከተማ ላይ ጥቃት ቢፈፅም የመከላከል አቅማችን እንዴት ነው? ከተማዋን የሚጠብቅ ህዝባዊ ጋርድ አላትን!!!

#{1} ወንዞችና የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት (Rivers and Riversides Development Project)

ዶክተር አብይ አህመደ በሃያ ዘጠኝ  ቢሊዮን ብር (This 29 billion birr (about $1.028 billion) በላይ በአዲስ አበባ ከተማ የወንዝ ዳር መናፈሻ ውብና ድንቅ ሥራ  ገንብተው ጨርሰዋል፡፡በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሻሸመኔ ቃጠሎ በኃላ የግሉ ዘርፍ ኢንቨስተርም በኦሮሚያ ክልል እንኳን ቱሪስት ወፍ ዝር አይልም በማለት ንዋዩን ከማፍሰስ ታቅቦል፡፡ ክልሉ መንግሥት አስተማማኝ የደህንነትና የፀጥታ ሁኔታን ካላመቻቸ አሁን ካለው የስራ ፈቱ ቁጥር ከአስር ሚሊዮን በላይ ይሆናል፡፡ ወጣቶች ተስፋ በመቁረጥ ወደ ኦነግ የመመልመል አማራጭ ሊሳቡ ይችላሉ እንላለን፡፡ የኦነግ ሽምቅ ተዋጊዎች ልጅ ሆነው እንዳዩት የሲሊቨስትሪ ስታሊዩን ፊልም ነፃ አውጪነትን ይተውናሉ፣ ጸጉራቸውን እንደ ባህታዊ አሳድገህ፣ ባንኮች እየዘረፉ፣ ከብቶች እየነዱ፣ ሴቶች እየደፈሩ፣ ህዝብ እያስገበሩ ይኖራሉ፡፡  ለዚህ ነው ሚሊዮን የኦሮሞ ሠራዊት ቀን ከሌት የግብርና ስራውን ትቶ የውትድርና ስልጠና በኦሮሚያ በክልል  መንግሥትና በኦነግ ሽምቅ ተዋጊዎች ስልጠና እየተሰጠው በሽፍትነት ኑሮ የሚኖረው፡፡ ከህወሓት ኢህአዴግ የጦር አበጋዞች የኦሮሚያ  የጦር አበጋዞች ምንም አልተማሩ፡፡  ሁለቱም የጦር አበጋዞች ለኦሮሞ ወጣቶች የፈጠሩላቸው የሥራ ዕድል ጠመንጃ ነካሽነት በመሆኑ በሠራዊትነት ተመልምለው በዘረፋ ሥራ በመሠማራት የኦሮሙማን ማኔፊስቶን ለማስፈፀም ሰዎች በመግደል፣ ባንክ መዝረፍና ከተማ በማቃጠል የጥላቻ ፖለቲካ በመስበክ የዘር ፍጅት ማስፋፋት ነው እንላለን፡፡ የፌዴራልና የክልል መንግሥት የኦሮሚያ ወጣቶችን ወደትምህርት ገበታ ለመመለስ ከፍተኛ የስብዓዊ ልማት መርሃግብር ዘርግተው ከገዳይነት ወደ ሠላማዊ ህይወታቸው ለመመለስ ትልቅ ሥራ መስራት ይጠበቅባቸዋል እንላለን፡፡ በኢትዮጵያ ከቁሳዊ ልማት ይልቅ ስብዓዊ ልማት  ይቅደም መጀመሪያ ሰው አንሁን እንላለን፡፡

 

#{2} ‹‹አዲስ የከተማ መንደር ምሥረታ››

ጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ‹‹አዲስ የከተማ መንደር ምሥረታና ግንባታ›› የአስር ሽህ ፎቆች ግንባታ የመሥሪያ ቦታ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መጠየቁን በሁሉም ሚዲያ ተሰራጭቶል፡፡ ዋና ዓላማው የኦሮሚያ ክልልን ተጠቃሚ ለማድረግ በብልጥግና ፓርቲ መንግሥት መር ግንባታ በማድረግ በኦሮሙማ ፐሮጀክት ሥም የከተማ ኮንዶሚኒየሞች ኃብትና ንብረት በተዘዋዋሪ ዘረፋ ነው፡፡ የግሉ ዘርፍ ግብርና ታክስ የሚከፍሉ ሪል ስቴት ዲቨሎፕርስ ባሉበት ሃገር፣ በአዲስ አበባ ከተማ የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሥራ ላይ የተሠማሩ ባለሃብቶች እያሉ የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት በግንባታ ሥራ የዘርፍ ላይ ምን ጥልቅ አረገው!!! ኮንዶምንየም ቤቶች፤ የኮዬ ፌጫና ገላን የሚገኙ ሠላሣ ሶስት ሽህ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ዜጎች ከባንክ ተበድረው ገንዘብ አጠራቅመውና በባንክ ቆጥበው ኮንዶሚኒም ከሰሩ ዜጎች ተነጥቆ ለኦሮሚያ ዲያስፖራ ተመላሽ፣ ቄሮና  ኦዴፓ ካድሬዎች  እንደተሰጠና የዶክተር አብይ መንግሥት የኢትዮጵያን ህዝብ በእኩልነት ዘር ሳይለይ እንደማያስተዳድረን ተስፋችንን እንደገደለ ሁሉም ይመሰክራል፡፡ ታዲያ    ‹‹የአዲስ የከተማ መንደር ምሥረታና ግንባታ›› ለማን? 

ፕሮፐርቲ 2020” የደቡብ አፍሪካ ሪል ስቴት;-‹‹ባሕር ዳር፡ ግንቦት 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) “ፕሮፐርቲ 2020” የተባለው የደቡብ አፍሪካ በቤት ልማትና ግንባታ ዘርፍ የተሠማራው ኩባንያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 100 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት ስምምነት ወስዷል። ኩባንያው በመዲናዋ ያለውን የመኖሪያ ቤት ፍላጎትና እና ጥያቄ በመመለስ በኩል ሚናው የጎላ እንደሚሆን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።ኩባንያው በመጀመሪያው ዙር 100 ሺህ ቤቶችን የሚገነባ ሲሆን በመጭዎቹ 5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ደግሞ 500 ሺህ ቤቶችን ይገነባል ተብሏል። ይህም በከተማዋ ያለውን የቤት ፍላጎትና አቅርቦት ያለውን ከፍተኛ አለመመጣጠን ለመቅረፍ ያሥችላል ተብሏል። ፕሮጀክቱ ለከተማዋ ብሎም ለኢትዮጵያ ወጣቶች የኮንስትራክሽን ተመራቂዎች ከፍተኛ የሥራ እድል እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ይፈጥራል ነው የተባለው። 4 ነጥብ 1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጭ የሚጠይቀውን የቤቶች ግንባታ ለመከወን የከተማ አስተዳደሩ መሬት በነጻ ለማቅረብና መሠረተ ልማት ለማሟላት የወሰደውን ተነሳሽነት ያደነቁት ኩባንያውን ወክለው ንግግር ያደረጉት ኢንጅነር ጃርሶ ጎሊሶ ናቸው፡፡››ሃገር በቀል ሪል ስቴት ዲቨሎፐርስ፣ ግብር ከፋዬቹን ያገለለ ልማት ለምን አስፈለገ? ……………………….(2)

#{3} በአዲስ አበባ የኦሮሙማ መንግሥታዊ ተቆማት ግንባታ

የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት መር ኢንቨስትመንት፡- በኦሮሚ ክልል የግል ኢንቨስትመንት ባለመኖሩ የተነሳና ብዙ ኢንቨስተሮች ከክልሉ መውጣት ዋና ምክንያት ንብረትና ኃብታቸው የወደመባቸው ባለኃብቶች ከመንግሥት ምንም ካሣ ባለማግኘታቸው ነው፡፡ የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት መንግሥት መር ኢንቨስትመንት

  • የኦሮሞ ክልል ፍርድ ቤት በ1.8 (አንድ ቢሊዮን ስምንት መቶ ሚሊዮን) ብር፣
  • የኦሮሚያ ፖሊስ ፅህፈት ቤት በ700 (ሰባት መቶ) ሚሊዮን ብር፣
  • ለኦሮሚያ ጀግኖች መታሰቢያ አንድ ቢሊዩን ብር በጠቅላላው ሦስት ቢሊዮን አምስት መቶ ሚሊዮን ብር በማውጣት መንግሥት መር ኢንቨስትመንት እድገት ጨምሮል፡፡
  • ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (Oromia Broadcasting Network) ህንፃ ግንባታ 1.5 billion dollar
  • የኦሮሚያ ባህል ማዕከል ግንባታ ቦታ ወዘተ

#{4} የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች (State Owned Enterprise)፡-

የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ከህወሓት ኢህአዴግ መንግሥት መንግሥታዊ ዘርፍ ኢንቨስትመንት በማስፋፋት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር በመውሰድ አትራፊነታቸው ያልተረጋገጠ ፕሮጀክቶች በመገንባትና የግሉ ዘርፍ ሊሰራቸው የሚችሉትን ሥራዎች በመሻማት ዘለቄታና ቀጣይነት የሌላቸው ፕሮጀክቶች በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በህወሓት ኢህአዴግ የሃያ ሰባት አመታት አገዛዝ ዘመን 780 ቢሊዩን ብር እዳ ያለባቸው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች እንደ ኢፈርት ድርጅት ዓይነቶችን በኦህዴድ ብልፅግና እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡

ልማታዊ መንግሥት (Developmental State)፡-የመንግሥታዊው ዘርፍ 53 በመቶ፣ የግሉ ዘርፍ 47 በመቶ ብድር አገኙ፣ የአገሪቱ ባንኮች የሰጡት ብድር ከአንድ ትሪሊዮን ብር (25 ቢሊዮን ዶላር) ደረሰ፡-ሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮችና 16ቱ የግል ባንኮች የሰጡት ከተበዳሪዎች የሚፈለግ የብድር መጠን፣ በሃያ በመቶ በመጨመር ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገጸ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሰኔ የ2012 ዓ.ም. መጨረሻ ዓመታዊ ሪፖርት እንዳመለከተው፣ ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ የደረሰው የብድር መጠን የተመዘገበ ነው፡፡ በሪፖርቱ እንደተጠቀሰው በ2012 የሒሳብ ዓመት ተሰብሳቢ ሆኖ ከተመዘገበው ብድር ውስጥ 53 (ሃምሳ ሦስት በመቶ)፣ ወይም ከ530 (አምስት መቶ ሠላሳ) ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆነው ለመንግሥት ተቋማት የተሰጠ ነው፡፡ ከግሉ ዘርፍ የሚጠበቁት ተሰብሳቢ ብድሮች መጠን ደግሞ 484.4 (አራት መቶ ሰማንያ አራት ነጥብ አራት) ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ይህም ባንኮች ከሰጡት ጠቅላላ ብድር ውስጥ 47 (አርባ ሰባት) በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛል፡፡ (የአገሪቱ ባንኮች የሰጡት ብድር ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገለጸ | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic)/ 7 February 2021

የኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ መንግሥታዊ ዘረፍ ወጪ በዶክተር አብይ የሦስት አመት አገዛዝ እየጨመረ መሄዱን በአንድ በኩል ለመንግሥታዊ ዘርፍ የተሰጠ ብድር 530 (አምስት መቶ ሠላሳ) ቢሊዮን ብር ሲሆን  በሌላ በኩል ለግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ የተሰጠው ብድር 484.4 (አራት መቶ ሰማንያ አራት ነጥብ አራት) ቢሊዮን ብር ለግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ ትኩረት አለመሰጠቱን ያሳያል፡፡ በህወሓት ኢህአዴግ የሃያ ሰባት አመታት አገዛዝ የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶች (State Owned Enterprises) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው መክፈል ያልቻሉት 780 (ሰባት መቶ ሰማንያ) ቢሊዮን ብር ከንግድ ባንክ ተበድረው አለመክፈላቸው እየታወቀ ከወያኔ ኦዴፓ ብልጽግና መማር አልቻለም እንላለን፡፡ ኦዴፓ ብልጽግና ቦዘኔ ቢሊዮነር በጨረቃ እየፈለገ ይገኛል፣ ፋብሪካ ከፍቶ ሸቀጣ ሸቀጥ አምርቶ፣ እርሻ አርሶ ሰብል አምርቶ፣ የሥራ እድል የሚፈጥር ኢንቨስተር ከሃገራችን ምድር ጠፍቶል፡፡ በዚህም የተነሳ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ የመንግሥትና መንግሥታዊ የልማት ድርጅቶቸ የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ እዳ ጨምሮል፣ አመታዊ የእዳ ወለድ የመክፈል አቅም ማጣፍያው ማጠር፣ የመንግሥታዊው ዘርፎች ወጪ ጨምሮል፣ የግብርና ታክስ መሰብስብ ችሎታ ዝቅተኛነት፣ ህዝብ በኑሮ ውድነት መሰቃየት የሸቀጣ ሸቀጦችና ምርቶች የዋጋ ግሽበት  መናርና ሃገሪቱ በኮማንድ ፖስት ወታደራዊ አስተዳደር ወጪና በጦርነት ኢኮኖሚ ኪሳራ ተዘፍቃለች፡፡  የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲም በዘረኛነትና በተረኛነት ስሜት አዲስ አበባን ከተማ ዲሞግራፊውን ለመቀየር ‹‹ፊንፌኔ ኬኛ›› የፖለቲካ ሴራ ብዙ ንጹሃን ዜጎች ከከተማዋ ሲያፈናቅሉ ኮንዶሚኒየም ሲዘርፉ ተስተውለዋል፡፡ የኦዴፓ ብልፅግና የኦሮሙማ የመስፋፋት ፖሊሲና የዘር  ፍጅት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ወንጀለኞች ፍርድ ቤት  ዶክተር አብይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ ለፍርድ መቅረባቸው አይቀርም እንላለን፡፡

ኦዳ ኢንቲግሬትድ ትራንስፖርት አክሲዩን ማህበር ODAA Integrated Transport S.C.

ኦዳ ኢንቲግሬትድ ትራንስፖርት አክሲዩን ማህበር በትራንስፖርት የንግድ ዘርፍ ሃምሳ አገር አቆራጭ አውቶብሶች በመግዛትና ሁለት የቤንዚን ማደያ ጣቢያዎች በመገንባት የተጀመረ የኦሮሞ ክልል መንግሥት ንብረት ነው፡፡  ኦዳ ከቮልቮ የሲውድን ካንፓኒ አንዱን አውቶብስ በ5.8 (አምስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሽህ) ብር ዋጋእንዲሁም ሃምሳ አውቶብሶች በ400 (አራት መቶ) ሚሊዮን ብር ጠቅላላ ዋጋ ገዝቶል፡፡ ኦዳ በገላን ሁለት የቤንዚን ማደያ ጣቢያዎች በ42 (አርባ ሁለት) ሚሊዮን ብር ወጪ ገንብቶል፡፡ኦዳ በሚቀጥሉት ሦስት አመታት ውስጥ መቶ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች  ለመገንባት አቅዶል፡፡…………………………… (3)

ኬኛ ቤቬሬጅ (ኬኛ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ) Kegna Beverages

ኬኛ ቤቬሬጅ (ኬኛ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ) በኦሮሚያ ክልል የኢኮኖሚ አብዬት ለማምጣት ከጀርመን ካንፓኒ ጋር በ2017 እኤአ ስምምነት ተፈራረመ፡፡  ኬኛ ቤቬሬጅ በጊንጪ ከተማ የሚገነባ ሲሆን 5.5 (አምስት ቢሊየን አምስት መቶ ሚሊዮን) ብር የግንባታ ወጪ የሚሰራ ሲሆን አንድ መቶ አንድ ሄክታር መሬት ላይ ግንባታው ያርፋል፡፡ ኬኛ ቤቬሬጅ ቢራ፣ ለስላሳ፣ ጭማቂ፣ የታሸገ ውኃ ያመርታል፡፡ ኬኛ በሙሉ አቅሙ ሲሰራ ሦስት ሚሊዮን ሄክቶሊትር በዓመት ያመርታል፡፡ ለሦስት ሽህ አምስት መቶ ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል፡፡  ኬኛ ቤቬሬጅ  አምስት ሽህ የአክሲን ባለድርሻ ባላቸው የተመሠረተ ሲሆን 1.5 (አንድ ቢሊዮን አምስት መቶ ሚሊዮን) ብር ካፒታልና 700 (ሰባት መቶ) የተከፈለ ተቀማጪ ብር  የተመሠረተ ካንፓኒ ነው፡፡……………….. (4)

ኬኛ የግብርና ትራክተር መገጣጠሚያና ማሽነሪዎች Kegna Agricultural Machinery

ኬኛ የትራክተር መገጣጠሚያ ማሽነሪ በሻሸመኔ ከተማ በ37000 ስኩየር ሜትር  ላይ የተገነባ ፋብሪካ ሲሆን በሃምሳ ሠራተኞች ሃያ ትራክተሮች  በቀን የመገጣጠም አቅም እንዳለው፣ በቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት ለማ መገርሳ ተገልፆ ነበር፡፡የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አንዱ ክንፍ የሆነው ኬኛ የግብርና መሣሪያዎች ማኑፋክቸሪንግና ጠቅላላ ንግድ  ድርጅት ትራክተሮች በመገጣጠም እንዲሁም የኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ባንክ በብድር አቅርቦት ለተደራጁ የኦሮሚያ ወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር የኦሮሚያ ክልል መንግሥት 350 ሦስት መቶ ሃምሳ ትራክተሮችን 285 በሁለት መቶ ሰማንያ አምስት ሚሊዮን ብር  ብድር  ለወጣቶች ተበርክቶላቸዋል፡፡……………..….(5)

#{5} የኢትዮጵያ አብሥራ ዓየር መንገድ፡- The Absera Airport ‹‹የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ጋር በኢትዮጵያ ሁለተኛው ሜጋ ፕሮጀክት በሆነው አዲሱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የግንባታ ቅድመ ዝግጅት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ››………………………………………….(6)

የኢትዮጵያ አብሥራ ዓየር መንገድ፡- የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ (Ethiopian Airlines) የአፍሪካን ትልቁን ዓየር መንገድ ለመስራት ማቀዱን አስታውቆል፡፡ ዓየር መንገዱ ይህን እቅዱን ለማሳካት አምስት ቢሊዮን ዶላር (ሁለት መቶ ቢሊዮን) ብር የግንባታ ወጪ ይጠይቀናል፡፡ የአዲሱን ዓየር መንገድ ትልቅ ኢንቨስትመንት እንደሆነ በቀላሉ ለመረዳት የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አምስት ቢሊዮን ዶላር የግንባታ ወጪ ጋር እኩል መሆኑን በመገንዘብ ነው፡፡ አዲሱ ዓየር መንገድ በውድድር ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት፣ ብዙ መንገደኞችን በማስተናገድ ከደቡብ አፍሪካው ጆሃንስበርግ ዓየር ማረፍያ የበለጠ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅበታል፡፡……………………………… (7)

Ethiopian Airlines Announces Plans to Build Africa’s Largest Airport (Video) /BY CAILEY RIZZO/

FEBRUARY 04, 2020/ Ethiopian Airlines is spending an estimated $5 billion to build the largest airport in Africa. It could also become Africa’s busiest airport, capable of handling more passengers than the current busiest hub in Johannesburg, South Africa.

#{6} ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (Oromia Broadcasting Network) ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክአንድ ቢሊዮን አምስት መቶ ሚሊዮን ብር  እንደሚገነባ ታውቆል፡፡ ኦሮሙማ ጨፍላቂ ባህል ፀረ-ዴሞክራሲ ባህል ነው፡፡ ኦሮሙማ ባህል የአንባገነኖች የአረመኔ አራጆች የመንጋ ወንጀለኞች ባህል ነው፡፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መሪ ሽመልስ አብዲሳ የጥላቻ ንግግርና የዘር ማፅዳት ቅስቀሳ ነገ በዓለም አቀፍ ወንጀለኖች ፍርድ ቤት ቀርቦ ፍርዱን ማግነቱ አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡

የአፍሪካ ቀንድ ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ  (‘OBN Horn of Africa’) በተመሳሳይ የኦሮሞ የውጪ ብሮድካስቲንግ  ስቱዲዬና ሦስት ኤፍኤም ስቱዲዬ በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ በሦስት መቶ ስልሣ ሚሊዮን ብር ወጪ ተገንብተው በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ተመርቀዋል፡፡ የአፍሪካ ቀንድ ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ  በአፍሪካ ቀንድ አገሮች የኢኮኖሚ ግንኙነትን በማሳለጥ ትልቅ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው  ተገልጾል፡፡  የአፍሪካ ቀንድ ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ  በምስራቅ አፍሪካ፣ በአፍሪካና ለዓለም ዜናውን በማሰራጨት ስራውን ጀምሮል፡፡ አንዴ በዘጠኝ አንዴ ባስራ ዘጠኝ የሃገር ውስጥና በውጪ  ቌንቌዎች ስርጭቱን ይጀምራል፡፡   ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ የሚዲያ እውቀትና ልህቀት በሌላቸው አድርባይ ምሁራን የተሞላ በጥላቻ ንግግርና የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ ወንጀል ተጠያቂዎች ናቸው፡፡

#{7} የሕክምና መንደር ግንባታ 300 ሚሊዮን ዶላር ወይም 12 ቢሊዮን ብር ወጪ ይገነባል

በአዲስ አበባ ቦሌ ሃያት ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ዓድዋ ፓርክ ሜዳ  ላይ ከተማዋን የጤና ቱሪዝም ማዕከል በ12 ቢሊዮን ብር የሚፈጀው የሕክምና መንደር ግንባታ ተጀመረ፡፡

ሆስፒታሉም 400 አልጋዎች፣ 16 የምጥና የማዋለጃ ክፍሎች፣ ሰባት የቀዶ ጥገና ክፍሎች፣ ከ20 በላይ የተመላላሽ የሕክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎች የመረጃ አያያዝ ሥርዓቱ ከወረቀትና ከካርድ ነፃ በማድረግና ሌሎች ነገሮችን በማካተት ነው ለአገልግሎት ክፍት የሆነው፡፡ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ወደ ሆስፒታልነት በመቀየር በ22 ሺሕ ካሬ መሬት ላይ ያረፈው አበበች ጎበና የእናቶችና ሆስፒታልና የሕፃናት ሆስፒታል ነው።…………….(8)

#{8} “የህክምና ማዕከል ሮሀ የህክምና ማዕከል”:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በ300 ሚሊዮን ዶላር የሚገነባውን የሕክምና ማዕከል የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ:-ወደ ውጭ የሚጓዙ ዜጎችን ያስቀራል የተባለውንና ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ይገነባል የተባለውን ሮሃ ሕክምና ማዕከል  ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ /ር) ናቸው።
#{9} በብላቴ ኮማንዶ ማሰልጠኛ ከኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር ከ10,00 በላይ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ሰልጥኖ ተመርቋል 700 የሚሆን የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ሁለተኛ ዙር ከመከላከያ VIP እየሰለጠነ ይገኛል::ዛሬ ፍትህ መጽሔት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ያስነበበችው መረጃ የሚገርም ነው።–“… በብላቴ ኮማንዶ ማሰልጠኛ ከኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር ከ1000 በላይ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ሰልጥኖ ተመርቋል። (ይህ ስልጠና ለሁሉም ወታደር የሚሰጥ ሳይሆን በVIP ልዩ የተልዕኮ ኮማንዶ ብቻ የሚሰለጥኑበት ነው) … ባሁኑ ሰአትም ከየካቲት መጀመሪያ ጀምሮ ከ600-700 የሚሆን የኦሮሞ ልዩ ሃይል ሁለተኛ ዙር ከመከላከያ VIP እየሰለጠነ ይገኛል።

#{10} የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ 39ኛ ወዘተ ጊዜ ስልጠና ተደርጎል፡፡ የአዲስ አበባ የፌዴራል ፖሊስ ተቆም ግንባታ ባለው ከመጠቀም ይልቅ በሌለ ገንዘብ ህንፃ ከመቆለል ማለትም ከቁሳዊ ልማት ይልቅ ስብዓዊ ልማት ለፖሊስ ሠራዊት አባላት ኮሌጅ በመክፈት እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን በዲጂታል ቴክኖሎጂ መገንባት ያሻል እንላለን፡፡

በኢትዮጵያ ከቁሳዊ ልማት በፊት ስብዓዊ ልማት ይቅደም!!!

ምንጭ፡-

Ethiopia to Build the Largest Airport in Africa | Travel + Leisure (travelandleisure.com)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በ300 ሚሊዮን ዶላር የሚገነባውን የሕክምና ማዕከል የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic

Leave a Reply