
#የኦሮሙማ ስርዓት የረጅም ጊዜ እቅዱን በgoogle map በኩል ሰሜን ሸዋን ወደ ኦሮሚያ ማካተቱን ይፋ አድርጓል‼️ ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የጎግል የካርታ መተግበሪያ ሙሉ ሰሜን ሸዋን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ አካቶ አዉጥቱዋል። ከዚህን ቀደም የተለያዩ ክልል የመሬት ክፍሎችን በኦሮሚያ ክልል የሚገኝ እንደሆነ አድርጎ የተሳሳተ መረጃ ለተጠቃሚዎች ሲያደርስ የቆየው ይህ መተግበርያ አሁን ላይ ደግሞ የሰሜን ሸዋ ሙሉ መሬቶችን ወደ ኦሮሚያ አካሎ አቅርቡዋል። ይሀዉ ተቋም ካሁን በፊትም በተመሳሳይ መልኩ ደብረብርሃንን ከአማራ ክልል አውጥቶ ለኦሮሚያ በሰጠው ተመሳሳይ የጎግል ካርታ ስህተት ላይ የኢትዮጵያ ካርታ ሥራዎች ኤጀንሲ ማብራሪያ እንዲሰጠው የአማራ ክልል መንግስት ጠይቆ ነበር። የአሁን ለየት የሚያደርገዉ ሙሉ የሸዋ ግዛቶችን ጠቅልሎ ለኦሮሚያ ማስረከቡ ነዉ። በተደጋጋሚ ሰሜን ሸዋ ዞንን ወደ ሌላ ክልል በማካተት ካርታውን በመተግበሪያዉ እያካተተ የተሳሳተ መረጃ በማቅረብ ላይ የሚገኝዉ ይህ ተቋም አሁንም በተመሳሳይ መንገድ ቀጥሉዋል። ደብረ ብርሀን ፣ሸዋ ሮቢትንና ሌሎች በአካባቢው የሚገኙ ቦታወችን በጎግል ማፕ ወደ ኦሮሚያ አካለውታል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post