የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የሠላምና የልማት የጋራ መድረክ እየተካሄደ ነው

የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የሠላምና የልማት የጋራ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የሠላምና ልማት የጋራ መድረክ በአዲስ አበባ እያካሄዱ ነው።

በመድረኩ የሁለቱ ክልሎች የአምስት ዓመት የልማት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት የሚደረግበት ሲሆን ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችም ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በውይይቱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልሎች የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በውይይቱ ማጠቃለያም ክልሎቹ በቀጣይ ለሚያከናውኗቸው የሠላምና የልማት ስራዎች የመግባቢያ ስምምነት ይፈራረማሉ ተብሏል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የሠላምና የልማት የጋራ መድረክ እየተካሄደ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply