የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ ኦነግ ሸኔ እና አጋሮቻቸው በጃርዴጋ ጫቶ፣ ሰምቦ ዋቶ እና አጋምሳ ጦርነት ከፍተው አማራዎችን ሲገድሉ፣ ሲያፈናቅሉ፣ በየጫካው ሲያሳድዱ፣ ሀብት ንብረት ሲዘርፉ እና ሲያቃ…

የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ ኦነግ ሸኔ እና አጋሮቻቸው በጃርዴጋ ጫቶ፣ ሰምቦ ዋቶ እና አጋምሳ ጦርነት ከፍተው አማራዎችን ሲገድሉ፣ ሲያፈናቅሉ፣ በየጫካው ሲያሳድዱ፣ ሀብት ንብረት ሲዘርፉ እና ሲያቃጥሉ ውለዋል፤ የድረሱልን ጥሪም ቀርቧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንዳሉት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ ኦነግ ሸኔ እና አጋሮቻቸው በጃርዴጋ ጫቶ፣ ሰምቦ ዋቶ እና አጋምሳ ጦርነት ከፍተው አማራዎችን ሲገድሉ፣ ሲያፈናቅሉ፣ በየጫካው ሲያሳድዱ፣ ሀብት ንብረት ሲዘርፉ እና ሲያቃጥሉ ውለዋል። በተለይም በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ሰምቦዋቶ እና አጋምሳ ቀበሌዎች የገባው ከሻምቡ የመጣው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ህዳር 25/2015 ሌሊቱን ጥቃት ሲፈጽም ማደሩ ታውቋል። በተመሳሳይ ህዳር 26/2015 በጫቶ፣ በሰምቦ ዋቶ እና በአጋምሳ ቀበሌዎች አማራዎችን እያሳደደ ሲገድል፣ ሲያፈናቅል፣ ሀብት ንብረት ሲዘርፍ እና ሲያወድም መዋሉ መዋሉ ተገልጧል። በየጫካው የሚሳደዱ አማራዎች በከፍተኛ ጭንቀት እና ስጋት ውስጥ ሆነው እባካችሁ በአስቸኳይ ድረሱልን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply