You are currently viewing የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በአንገር ጉትን ከተማ እያደረገ ያለውን ተከታታይ ትንኮሳ እና የጦር አውርድ እንቅስቃሴ እንዲያቆም ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር 17 ቀን 2015 ዓ/ም…

የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በአንገር ጉትን ከተማ እያደረገ ያለውን ተከታታይ ትንኮሳ እና የጦር አውርድ እንቅስቃሴ እንዲያቆም ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 17 ቀን 2015 ዓ/ም…

የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በአንገር ጉትን ከተማ እያደረገ ያለውን ተከታታይ ትንኮሳ እና የጦር አውርድ እንቅስቃሴ እንዲያቆም ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 17 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንገር ጉትን ከተማ ከተለያዩ የዞኑነወረዳዎች በማንነታቸው ብቻ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ፣ ቤት፣ አዝመራና ሀብት ንብረታቸው የተቃጠለባቸው በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ አማራዎች ያለምንም የሰብአዊ እርዳታ በከፍተኛ ችግር የሚኖሩበት አካባቢ መሆኑ ተመላክቷል። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከህዳር 9/2015 ጀምሮ በኪረሞ እና በጃርዴጋ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በዚህ ከተማም ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ኃይሉን አስገብቷል። ኃይሉን ካስገባበት ጊዜ ጀምሮ አላስፈላጊ ትንኮሳ እና የጦር አውርድ እንቅስቃሴ በማድረግ ነዋሪውን ህዝብ እያሸበረ ነው የሚል ቅሬታ በተደጋጋሚ እየተነሳበት ነው። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት ኪረሞ፣ ሰቀላ እና ጃርዴጋ ላይ እንደፈጸሙት ሁሉ በጊዳ አያና ወረዳ አንገር ጉትንም አማራ ተኮር ጥቃት ሊፈጽሙ ስለመዘጋጀታቸው የእለት ከእለት የትንኮሳ እንቅስቃሴያቸው፣ የሰው ኃይል እና የትጥቅ ዝግጅታቸው አመላካች ነው ተብሏል። ልዩ ኃይሉ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ኦዳቡልቅ ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጋር አድርጓል የተባለውን ስምምነት ተከትሎ እየተናበበ ስለመሆኑ የሚናገሩት ምንጮች ህዳር 13/2015 በጃርዴጋ በተመሳሳይ ሰዓት በሁለት አቅጣጫ ጦርነት ከፍቶ እንደነበር አውስተዋል። ከሰሞኑ ወደ አንገር ጉትን የገባው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦሮሚያ ልዩ ኃይልም ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅሎ በከተማዋ የሚኖረውን ህዝብ እያሸበረ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ በብዙዎች ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያነጋገራቸው የአንገር ጉትን ነዋሪዎች እንደሚሉት:_ 1) አቶ አዝመራው የተባለ የአማራ ሚሊሻ በሳሲጋ ወረዳ ጥቅምት 2015 የአሸባሪው ኦነግ ሸኔን ጥቃት ለመከላከል በምስራቅ ወለጋ ዞን በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ከሌሎች ሚሊሾች ጋር በመሆን ሲታገል ነበር። በወቅቱም በመቁሰሉ በአንገር ጉትን ከተማ እየታከመ ሳለ ህዳር 15/2015 ከቀኑ 12 ሰዓት ላይ ግሉኮስ ተሰጥቶት በቤቱ በተኛበት አፍነው ለመውሰድ በመኪና ላይ አስገድደው ሲያሳፍሩት ጭሆት ማሰማቱን ተከትሎ ቁስለኛው ምን አደረገ በሚል የሰፈር ሚሊሻ እና ህዝቡ በመቆጣቱ እንዲለቀቅ መደረጉ ተገልጧል። አፋኙ ቡድንም ከቁስለኛው ላይ ግሉኮስ ነቅሎ አቶ አዝመራውን ከቤት ጎትቶ ሲወስድ በቤተሰቦቹ ላይም ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት መፈጸሙ ተነግሯል። የአሸባሪው ኦነግ ሸኔዎችን አደራ ለመወጣትና አፍነው ወደ ጫካ በመውሰድ ሊጨርሱት ፍላጎት እንደነበራቸው የአሚማ ምንጮች ተናግረዋል። 2) ከቀናት በፊት ደግሞ አማራውን እያሰለጠኑ ነው በሚል ሁለት ነዋሪዎችን አፍነው ለመውሰድ ያደረጉት ሙከራ የአንገር ጉትን ነዋሪ የልዩ ኃይሉ አካሄድ ለማንም በዘላቂነት የማይጠቅም የጦር አውርድ እንቅስቃሴ ነው ሲሉ በማውገዛቸው መክሸፉ ታውቋል። 3) በተመሳሳይ የህዝብ መኪና እንቅስቃሴ ከቀናት በፊት ከነበረው የኪረሞው ጥቃት ጀምሮ እንዲቆም መደረጉ እና የባንክ አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉ ልዩ ኃይሉ በቀጣይ ለመውሰድ ስላሰበው እርምጃ አመላካች በመሆኑ ችግሩ ከመከሰቱ በፊት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግለት ተጠይቋል። 4) በአዋሳኙ ቱሉጋና ከተማ የነበረው የባንክ አገልግሎት ሆንተብሎ የተቋረጠ መሆኑ ተገልጧል። ከአሁን ቀደም የኦሮሚያ ልዩ ኃይል የተለያዩ ባንኮችን ካዝና፣ኮምፒውተርን ጨምሮ አጠቃላይ ንብረትን ጭኖ ወደ ነቀምት ለመውሰድ ያደረገው ሙከራ በህዝብ ተቃውሞ ከሸፈ ቢሆንም በሌላ ጊዜ መከላከያ ሰራዊት መሆናቸውን በገለጹ አካላት እንዲወሰድ መደረጉን ያወሱት ምንጮች ነዋሪው እስካሁን አገልግሎት እንዳያገኝ እና ለከፍተኛ ችግር እንዲዳረግ የተፈረደበት መሆኑን ጠቁመዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply