You are currently viewing የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ጀሞ ተራራ መድኃኒያለም እና ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ በኃይል ቤት በሚያስፈርስበት ወቅት  በአምስት ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን ነዋሪዎች ተ…

የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ጀሞ ተራራ መድኃኒያለም እና ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ በኃይል ቤት በሚያስፈርስበት ወቅት በአምስት ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን ነዋሪዎች ተ…

የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ጀሞ ተራራ መድኃኒያለም እና ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ በኃይል ቤት በሚያስፈርስበት ወቅት በአምስት ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከአዲስ አበባ ተቀንሶ ወደ ክልሉ እንዲጠቃለል ተደርጓል ባለው አካባቢ ከኦሮሞ ተወላጆች ውጭ የሌሎች ኢትዮጵያዊያንን መኖሪያ ቤት በኃይል እያፈረሰ መሆኑ ይታወቃል። በተለይም በግሬደር፣ በእስካቫተር እና አፍራሽ ግብረ ኃይል በሽህ የሚቆጠሩ የአማራ፣የትግሬ፣ የጉራጌ፣የወላይታ፣የስልጤ፣የጋሞ እና የሌሎችም በሽህ የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶች የፈረሱትም:_ 1) በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ጀሞ ተራራ መድሃኒያለም እና ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ፣ 2) በኦሮሚያ ልዩ ዞን/በአሁኑ አጠራር ሸገር ሲቲ፣ ሰበታ ክ/ከተማ፣ ገዳፈቻ ወረዳ ወለቴ ቀበሌ ልዩ ስሙ አጃምባ እና 3) በኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰበታ ወረዳ 08 ቀበሌ፣ጎጥ 6፣እንቁ ገብርኤል አካባቢዎች ነው። ከእነዚህም መካከል በጀሞ ተራራ መድሃኒያለም እና ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢዎች ነዋሪዎች እንደሚሉት የአምስት ሰዎች ህይወት አልፏል፤ ቢያንስ ከአስር በላይ ሰዎች ቆስከዋል፤ የአንድ ልዩ ኃይል ህይወትም አልፏል። የጀሞ ተራራ መድኃኒያለም ነዋሪዎች እንደሚሉት ከተገደሉት መካከል:_ 1) አብዱ ፈታ የተባለ የስልጤ ተወላጅ እድሜው እስከ 35 የሚሆን የተመታው ታህሳስ 26/2015 ከቀኑ 6 ሰዓት አካባቢ ነው። ግድያው የተፈጸመው በጀሞ ተራራ መድኃኒያለም እና ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን መሃል አካባቢ ነው ተብሏል። በሁለት ጥይት ጀርባው ላይ ተመትቶ ነው የተገደለው። ወደ ወታደር ሰፈር ተወስዶ ስርዓተ ቀብሩ ተፈጽሟል። 2) በስም ያልተጠቀሰ የ13 ዓመት ህጻን ልጅ ወደ ግራር ጤና ጣቢያ ከተወሰደ በኋላ ህይወቱ አልፏል። 3) ከፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን ጎን ሬንጅ ፋብሪካ አካባቢ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። 4) ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን ጸበል አካባቢ ሌላ አንድ ሰው ተገድሏል። ታህሳስ 26/2015 ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6:30 ተኩስ እንደነበር የገለጹት ነዋሪዎች በእንቁ ገብርኤል አካባቢም ታህሳስ 23/2015 እና ታህሳስ 25/2015 በነበረው ቤት የማፍረስ ሂደት ከአስር በላይ የሚሆኑ ሰዎች ተጎድተው ወደ ህክምና እየተወሰዱ እያለ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ተነጥቀው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል ብለዋል። ይህ በዜጎች ላይ የሚፈጸመው አድሎአዊ አሰራር ይቁም በሚል ጥያቄ እየተነሳ ቢሆንም ከፌደራል እስከ ክልል ድረስ ሰሚ አላገኘንም ሲሉ ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች ቅሬታ እያቀረቡ ነው። እንቁ ገብርኤል አካባቢ በደረሰባቸው ጉዳት ሳይታከሙ በፉሪ 04 ፖሊስ ጣቢያ ከታሰሩት መካከል:_ 1) ካሳዬ ድረስለት፣ 2) መኩሪያ ሙጨ፣ 3) ቄስ ሃይለ ማርያም፣ የቅዱስ ሚካኤል ደብር አስተዳዳሪ፣ 4) ቄስ መዝገበ_ተው እያሉ እየተማጸኑ ባሉበት የተመቱ ናቸው። 5) ወርቅነህ ተፈራ፣ 6) ጌታዬ በየነ እና ሌሎችም ይገኙበታል። ቶላ ሰቦቃ የተባለ የአካባቢው ነዋሪ የቆሰሉትን ለማሳከም ሲሄዱ በአንጻሩ ዲባባ ሌሊሳ፣ ኩምሳ ጫላ፣ገመዳ ሌሊሳ እና ዳኜ ሌሊሳ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ደግሞ እያሳሰሩ እና የድሃ ቤት እያስፈረሱ ነው ሲሉ አካሄዳቸውን አውግዘዋል። እንቁ ገብርኤል አካባቢ ታህሳስ 23፣24፣25/2015 ቢያንስ ከ300 በላይ ቤቶች እንዲፈርሱ መደረጉ ተገልጧል። ታህሳስ 27/2015 አሌ ሰፈር አካባቢ ያሉ ቤቶችም እየፈረሱ መሆኑን ለአሚማ ገልፀዋል። ፎቶ_ፋይል

Source: Link to the Post

Leave a Reply