የኦሮሚያ መጅሊስ 13 አባላት ያሉት ብሄራዊ ኮሚቴ በቅርቡ የተፈጸሙትን ግድያዎች አጣርቶ ድጋፍ እንዲያደርግ እና ዘላቂ መፍትሄ እንዲያፈላልግ ተሰይሟል፡፡በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ወለ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/kipSPYzaVCCuoBC1WyDs3T9fG1XgLZ1FO1CXpn7sgAppjs01rb-oCweiW0nRqLlB_HJka4VA3qPOzy7YgM6gG21hNGG0NJlHX7eCX0aYJREYfRfbKsHpYzuKF-rGNJmkLzHn024OcRNubFdHOPoQNtkqKZo8YQjfu711d90w0uIZjWk2QqSQyyC4OanWaXL2VPFBowtzLz1AuP0YaxvHDHu6QJM7n-sWNtsZZSw7T5fe86_2ZtRfD3fN6o7tokumHA9A-y_zn7UKn1h6sZBK8qzrx62UAvz4kJg748qs1SpzrnbAnAXI7DwbvprtWtCzXbRsi53DcKQqYDZqoU6piQ.jpg

የኦሮሚያ መጅሊስ 13 አባላት ያሉት ብሄራዊ ኮሚቴ በቅርቡ የተፈጸሙትን ግድያዎች አጣርቶ ድጋፍ እንዲያደርግ እና ዘላቂ መፍትሄ እንዲያፈላልግ ተሰይሟል፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በንፁሀን ዜጎች ላይ በደረሰው ግድያ በኦሮሚያ ክልል መጅሊስ አስተባባሪነት 13 አባላት ያሉት ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቁሟል።
አዲስ ስታንዳርድ እንደዘገበው በቀድሞው መሪ የተቋቋመው 13 አባላት ያሉት ኮሚቴ የሀገር ሽማግሌዎች፣ታዋቂ የእስልምና መምህራን እና ምሁራን፣ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እና ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ እንዲሁም የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጣ ነው።

ኮሚቴው ከፌዴራል እና ከክልል መንግስታት ጋር በሦስት ዋና ዋና ተግባራት ላይ ለመስራት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
ይህም የተረፉትን ተጎጂዎችን ለመደገፍ እና መልሶ ለማቋቋም እና አስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የተፈናቃዮች ማዕከላት ድጋፍን የማስተባበር ስራ ይሰራል ተብሏል።

የተፈፀመውን አሰቃቂ ጥቃት በዝርዝር በማጣራት የደረሰውን ጉዳት ለህዝብ እና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት በማሳየት ተጎጂዎች ፍትህ እንዲያገኙ ማድረግ፣ በሙስሊሙ ላይ የሚደርሱ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ ለመስራት ያስችላል ተብሏል።

በያይኔአበባ ሻምበል
ሰኔ 21 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply