
የኦሮሚያ ብልጽግና አመራር የሆኑት አቶ ታዬ ደንደኣ አዲስ ይገነባል የተባለውን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ቤተ መንግሥት ተቃወሙ። ግንቦት 09 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ አቶ ታዬ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ‹የሕዝቡ ጥያቄ ቤተ መንግሥት አይደለም› ብለዋል፡፡ የአቶ ታዬ ደንደኣ ተቃውሞ የመጣው የክልሉ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የሚያስገነቡትን ቤተ መንግሥት ሥራ ማስጀመራቸው ከተነገረ ከሰዓታት በኋላ ነው፡፡ የወቅቱ የሠላም ሚኒስቴር ዲኤታው አቶ ታዬ የክልሉ ሕዝብ ጥያቄ ቤተ መንግሥት አለመሆኑን ጠቅሰው፤ ሌሎች ጉዳዮች ቅድሚያ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ አቶ ታዬ የሕዝቡ ጥያቄ የመልካም አስተዳደር፣ የሰላም እና ኢኮኖሚ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በአቶ ሽመልስ የተጀመረውን የቤተ መንግስት ግንባታም ለታማሚ ሰው የተሳሳተ መድሃኒት እንደመስጠት ነው ብለውታል፡፡ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post