የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትን እና የአሸባሪው ኦነግ ሸኔን በአማራ ላይ እየፈጸሙት ያለውን ጥቃት በመደገፍ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ የምስራቅ ወለጋ ባለሀብቶችን ጉድ ያጋለጡ የአንገር ጉት…

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትን እና የአሸባሪው ኦነግ ሸኔን በአማራ ላይ እየፈጸሙት ያለውን ጥቃት በመደገፍ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ የምስራቅ ወለጋ ባለሀብቶችን ጉድ ያጋለጡ የአንገር ጉትን ወጣቶች በዚህ ተግባር ውስጥ የተሰማሩ አካላትን ስም በመዘርዘር ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በሻሎም ሆቴል ስብሰባ አርገው ከዞን እስከ ወረዳ ሰው መርጠዋል፤ ጉትን እና አከባቢውን ማህበረሰብ የማፅዳት ስራን ተሰብስበው ያቀዱበት ቀን እና የወገን ጭፍጨፋን ለማካሄድ የተፈራረሙበት ቀን ጭምር በመጥቀስ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በህብረቱ በኩል ያሳሰቡት የአንገር ጉትን ወጣቶች ናቸው። በዚህ ጸረ አማራ ጭፍጨፋ ተዋናኞች ሲል በስም ዝርዝር ከጠቀሳቸው መካከልም:_ 1) አበራ ኦላኒ፣ 2) ዳመና ጎሞሮ፣ 3) ጀመራ ካባ፣ 4) ለታ አብሸ፣ 5) አዳነ ረጋሳ፣ 6) ደቻሳ፣ 7) ናቶል 8 ወዳጆ፣ 9) ኦልጅራ እና 10) ሻምበል ኦላ የተባሉ እንደሚገኙበት ህብረቱ ጠቅሷል። ከዚህ በኃላ ጋምቤላና ቤንሻጉል መሬት ፍለጋ አንሄድም፤ አማራን ጨፍጭፈን አፈናቅለን፣ ኢንቨስት እናደርጋለን በሚል ባቀናጁት ሴራ ይህንን ያልተቀበሉ ንፁሃን ወንድሞቻችን እንደ ገመችስ ጉደታ (ገሚ 24) ያሉት ንፁህ ኦሮሞወች በአባ ቶርቤ ተገደሉ፤ ገሚሶቹ ደግሞ ወደ አዲስ አበባ ሸሽተዋል ነው ያለው። ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ከአማራ የማፅዳት አላማን ያነገቡ መሆናቸው ህግ ያውቃል፤ ነገር ግን ለህግ ሊቀርቡ አልተቻለም ምክንያተቱም ከባለ ስልጣኑም ከላይም ከታችም ዋና መሪ ኮሚቴወች በመሆናቸው ነው ሲልም አክሏል። ዘላቂ ሰላም ከተፈለገ እኛ ምሥራቅ ወለጋ ወጣቶች ህብረት እነዚህ ባለሀብቶች እና ግብረ አበሮቻቸው በህግ ሊቀርቡ ይገባል የሚል ጥሪም አስተላልፈዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply