You are currently viewing የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጽመው ግፍ ማቆሚያ አላገኘም፤ በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ከፋኖ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የ80 ዓመት እናትን ጨምሮ ሁለት ሴቶችን አስሯል።…

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጽመው ግፍ ማቆሚያ አላገኘም፤ በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ከፋኖ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የ80 ዓመት እናትን ጨምሮ ሁለት ሴቶችን አስሯል።…

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጽመው ግፍ ማቆሚያ አላገኘም፤ በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ከፋኖ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የ80 ዓመት እናትን ጨምሮ ሁለት ሴቶችን አስሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 16 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአማራ ተወላጆች የሚፈጽመው ግፍ ማቆሚያ አላገኘም፤ በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ቂልጡ ጬካ ቀበሌ በተባለ ቀበሌ ከፋኖ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የ80 ዓመት እናትን ጨምሮ ሁለት ሴቶችን በፖሊስ ማሳሰሩ ተገልጧል። ወ/ሮ ካሳዬ ሰጭው የተባሉ የ80 ዓመት እናት እና ወ/ሮ መካ አሊ የተባሉ የ2 ልጆች እናት በቂልጡ ጬካ ቀበሌ ከሚኖሩበት ማክሰኝት ገበያ ነው ታህሳስ 14 ቀን 2014 ከቀኑ 5 ሰዓት በወረዳው ፖሊሶች ታስረው የተወሰዱት። ወ/ሮ ካሳዬ ሰጭው የመከላከያ ምልስ የሆነው ልጅዎት ከፋኖ ጋር ይገናኛል እንዲሁም ያሰለጥናል በሚል ሲታሰሩ ጎረቤታቸውና ቅርብ ቤተሰባቸው የሆኑት የሁለት ልጆች እናት ወ/ሮ መካም በተመሳሳይ ከፋኖ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ታስረዋል ሲሉ የአካባቢው ምንጮች ተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል መንግስት በጫካ ባለው ኦነግ ሸኔ ከሚፈጸምብን ግፍ እና በደል ባልተናነሰ የተረፍነውን ወደ እስር ቤት በማጋዝ፣ ለተፈናቀሉት እርዳታ ባለማቅረብ እንድንሰቃይ የማድረጉ ነገር በአሳሳቢነቱ እየቀጠለ በመሆኑ እባካችሁ ሰሚ ካለ የፍትህ ያለ እያላችሁ እንድትጮሁልን እንለምናችኋለን ሲሉ ተማጽነዋል። የወ/ሮ ካሳዬ ልጅ አቶ በለጠ አባተ የመከላከያ ምልስ ሲሆን “ለመሆኑ ለእስር የሚያበቃ ምን ወንጀል ሰራሁ? እናንተ ደግሞ ከኦነግ ሸኔ ጋር እየተመሳጠራችሁ አማራን እየጨፈጨፋችሁ ነው፤ በአላማ አንድ ናችሁ፤ በመሆኑም እንዴት አድርጌ ነው ለኦነግ እጄን የምሰጠው” በማለት ወደ ጫካ መሸሹ ተገልጧል። መሃል ከተማ በመንግስት ቢሮ ያሉ የኦነግ ሸኔ ክፉ እና ከፋፋይ አላማ አስፈጻሚዎች ስንቅ፣ትጥቅና መረጃ በማቀበል ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እያስፈጸሙ ከመሆናቸው በተጨማሪ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ የሚፈሩ የአማራ ጀግኖችን ወደ እስር ቤት እያጋዙ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ ተዘግቧል። እንደአብነትም በጥር 2013 አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በጊዳ አያና ወረዳ መንደር 10 በሚኖሩ አማራዎች ላይ ይፋዊ ጦርነት ሲከፍት በተሰጠው ጠንካራ የአጸፋ ምላሽ በመመታቱ የተበሳጩ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት በየካቲት 2013 አንድ ባለሃብትን በአደባባይ ከመግደል ባሻገር 31 የአማራ ባለሃብቶችን አፍነው ወደ ነቀምት መውሰዳቸውና ያለፍትህ በእስር ቤት ማጎራቸው አይዘነጋም። ከነቀምት በተጨማሪ በአቢ ደንጎሮ፣ በአሙሩ፣ በጃርቴ እና በአንገር ጉትንም ግፍንና ነውረኝነትን የሚቃወሙ በርካታ አማራዎች በግፍ እስር ላይ ይገኛሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply