You are currently viewing የኦሮሚያ ክልል ለሸኔ የድርድርና እርቅ ጥሪ አቀረበ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ለሸኔ የድርድርና እርቅ ጥሪ አቀረበ፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለጨፌው በዛሬው እለት ሪፖርት አቅርበዋል።
በሪፖርታቸውም በክልሉ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ እንደ ሸኔ ያሉ ሀይሎችን በንግግር ወደ እርቅ እንዲመጡ ጥሪ አድርገዋል፡፡

በሪፖርታቸውም በግብርናው ዘርፍ ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ ሰፊ ስራ ተከናውኗል ያሉት የክልሉ ፕሬዝዳንት በዚህም አመርቂ ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል፡፡

በክልሉ በመህር እና በመስኖ በክላስተር ከለማው ስንዴ ለውጭ ገበያ ማቅረብ መቻሉን አብራርተዋል፡፡
በክልሉ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አልፎ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በተከናወነው የስንዴ ምርት በንቃት በመሳተፍ ውጤታማ መሆን ተችሏልም ነው ያሉት፡፡

በተያያዘም እንደ ሀገር በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የኦሮሚያ ክልል ስኬታማ ስራ አከናውኗል ያሉት አቶ ሽመልስ፣ በዚህም ባለፈው ክረምት በ1 ነጥብ 15 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ላይ የተተከሉ 4 ነጥብ 16 ቢሊዮን ችግኞች እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑንና በመጀመሪያው ምዕራፍ በተደረገው ግምገማ 92 በመቶ መፅደቁን መናገራቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply