
የኦሮሚያ ክልል ለአፈነገጡ ህገ ወጥ ቡድኖች ሙሉ ድጋፍ በመስጠት ላይ መሆኑ ተመለከተ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 24 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ላይ የሚደረገው ወከባ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የኦሮሚያ ክልል ለአፈንገጡት አባቶች ሙሉ ድጋፍ በመስጠት ላይ መሆኑ ተመላክቷል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ላይ የሚደረገው ወከባ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ህገ ወጥ በተባለና የቤተክርስቲያኗን አንድነት ለማናጋት በታቀደ መልኩ በተካሄደ ስነ ስርዓት የጵጵስና እና ሹመት ላገኙ አባቶች በኦሮሚያ ክልል መንግስት ድጋፍ በአንዳንድ አብያት ክርስቲያናት አቀባበል እየተደረገላቸው መሆኑም ታውቋል። በተለይ በወለጋ የተለያዩ አካባቢዎች በልዩ ሃይል የደህንነት ጥበቃ ስር የሆኑት አባቶች አብያተ ክርስቲያናትን እየተረከቡ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። በጂማ ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ለማድረግ ከወዲሁ የሀገረ ስብከቱን ንብረቶች በእግድ ስር እንዲሆኑ መደረጉን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የጂማ ፣ የየም እና የኮንታ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልከአ ሰላም ተስፋ ሚካኤል አሰፋ፣ ከተወሰዱበት ለሰዓታት በጸጥታ ሃይሎች ከተወሰዱ በኋላ የተመለሱ ሲሆን የሀገረስብከቱ ተሽከርካሪዎች እንዲታገዱ መደረጉም ተገልጿል። መሰል እርምጃዎች በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች እየተካሄዱ እንደሆነም መረጃዎች ይጠቁማሉ ሲል ንስር ብሮድ ካስት ሚዲያ ዘግቧል።
Source: Link to the Post