የኦሮሚያ ክልል ለ560 አርሶ እና አርብቶ አደሮች ሽልማትና እውቅና ሊሰጥ ነው

የኦሮሚያ ክልል ለ560 አርሶ እና አርብቶ አደሮች ሽልማትና እውቅና ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለ560 አርሶ እና አርብቶ አደሮች ሽልማትና እውቅና ሊሰጥ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የኦሮሚያ ክልል ግብርናና ተፈጥሮ ኃብት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በክልሉ ከሁለት አመት ወዲህ በዘርፉ ውጤታማና ግንባር ቀደም ለሆኑ አርሶ እና አርብቶ አደሮች ሽልማትና እውቅና ሊሰጥ ነው፡፡
እውቅናው የሚሰጠውም በግብርናው ዘርፍ አስተዋፅኦ ላበረከቱ፣ በክላስተር አምርተው ውጤታማ ለሆኑ፣ በማህበራት ተደራጅተው በመስኖ ልማት ግንባር ቀደምትነታቸውን ላስመሰከሩ፣ በእንስሳት ማድለብ እና ተፈጥሮ ኃብት እንክብካቤ ለተሰማሩ አርሶ እና አርብቶ አደሮች ነው፡፡
በተጨማሪም ለውጤታማ የግብርና ልማት ሰራተኞች፣ ዘርፉ እንዲጎለብት በምርምር አስተዋፅኦ ላበረከቱ እንዲሁም ጥሩ አፈጻፀም ላስመዘገቡ ማህበራትና ዩኒየኖች እውቅናው ይሰጣል ብለዋል ኃላፊው፡፡
የእውቅናና የሽልማት ፕሮግራሙ የነገ ሳምንት የሚካሄድ መሆኑን አቶ ዳባ ደበሌ ገልፀዋል፡፡
ከነገ ጀምሮም በ258 ከተሞች ውስጥ ያሉ አርሶና አርብቶ አደሮች ምርቶቻቸውን በአውደ ርዕይ የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡
በዝግጅቱም የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ገበያ ትውውቅ እና ትስስር ለመፍጠር ይሰራልም ነው ያሉት፡፡
የቁጠባ ባህል እንዲያድግ አርሶና አርብቶ አደሮች፣ ማህበራትና ዩኒየኖች ከሚያገኙት ገቢ 60 በመቶ እንዲቆጥቡ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር እየተሰራ ይገኛልም ነው ያሉት ኃላፊው፡፡
በረጋሳ ፊሮሚሳ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የኦሮሚያ ክልል ለ560 አርሶ እና አርብቶ አደሮች ሽልማትና እውቅና ሊሰጥ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply