You are currently viewing የኦሮሚያ ክልል መንግስት ታላቁ የህዳሴ ግድብን ወደ ኦሮሚያ ለመጠቅለል ጫፍ ደርሷል። መጋቢት 04 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የግድቡ ውሃ የሚተኛበት መሬት የማስፋፊያ ስራ እየተሰራ ነ…

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ታላቁ የህዳሴ ግድብን ወደ ኦሮሚያ ለመጠቅለል ጫፍ ደርሷል። መጋቢት 04 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የግድቡ ውሃ የሚተኛበት መሬት የማስፋፊያ ስራ እየተሰራ ነ…

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ታላቁ የህዳሴ ግድብን ወደ ኦሮሚያ ለመጠቅለል ጫፍ ደርሷል። መጋቢት 04 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የግድቡ ውሃ የሚተኛበት መሬት የማስፋፊያ ስራ እየተሰራ ነው። ለጉባ አዋሳኝ በሆነችው ሸርቆሌ ወረዳ ልዩ ስሙ አውል ቤጎ በተባለ አከባቢ በደን ምንጣሮ ከተሰማሩት 3000 በላይ ወጣቶች መካከል ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው።(የአማራ ተወላጆች ስራውን ለቀው እንዲወጡ ተደርገዋል)። በስራው የተሰማሩት የኦሮሞ ተወላጆቹ ወታደራዊ ስልጠና የተሰጣቸው ናቸው ተብሏል። በአቅራቢያቸው ከሚገኙ የኦነግ ታጣቂዎች ጋር ሰፊ ግንኙነት እንዳላቸውም ተጠቁሟል። በተጨማሪም ለጉባ ወረዳ በቅርብ ርቀት በሚገኘው ልዩ ስሙ ሲርባባይ በተባለ አከባቢ በኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል እና በቤኒሻንጉል ክልል ልዩ ኃይል መካከል ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው። ከዚህ አልፎ ግድቡ በሚገኝበት ጉባ ወረዳ እና በምዕራብ ወለጋ ዞን መካከል የሚገኘው የካማሺ ዞኑ ኦዳ ቡልዱ ጉሉ ወረዳ ነዋሪዎች አከባቢያችሁ ወደ ኦሮሚያ ክልል ስለተካለለ በአስቸኳይ ለቃችሁ ውጡ የሚል ትዕዛዝ ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል እንደተሰጣቸውም ተሰምቷል። የአማራ ድምፅ ሚድያ አንድ የቤኒሻንጉል ክልል ከፍተኛ አመራርን ጨምሮ ነዋሪዎቹን እንዲሁም በደን ምንጣሮው የተሰማሩ ወጣቶችን አነጋግሯል። የአማራ ድምፅ እንደዘገበው “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply