የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በሰሜን ሸዋ ዞን በኩታ ገጠም እርሻ የለማ ማሳን ጎበኙ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በሰሜን ሸዋ ዞን በኩታ ገጠም እርሻ የለማ ማሳን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በሰሜን ሸዋ ዞን በኩታ ገጠም እርሻ የለማ ማሳን ጎበኙ፡፡

ጉብኝቱ በዞኑ በሂዳቦ አቦቴ ወረዳ ውስጥ ዳሮ አሙማ ወጁ ቀበሌዎች ነው የተካሄደው፡፡

በዚህም የለማ ጤፍን ጨምሮ ምርጥ ዘር ቡና እና የችግኝ ማፍያ ስፍራን ተመልክተዋል፡፡

በዞኑ ከ105 ሺህ በላይ ሄክታር በላይ መሬት በክላስተር እየለማ መሆኑ ተነግሯል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ባዩት ነገር መደሰታቸውን ጠቅሰው መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በአፈወርቅ አለሙ

The post የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በሰሜን ሸዋ ዞን በኩታ ገጠም እርሻ የለማ ማሳን ጎበኙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply