የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የተገነቡ ፕሮጀክቶችን መረቁ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የተገነቡ ፕሮጀክቶችን መረቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡

ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል የአርሶ አደሮች ማዕከልና የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ይገኙበታል፡፡

በፕሮጀክቶቹ የምረቃ ስነስርዓት ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በይፋ የተመረቁት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል፡፡

The post የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የተገነቡ ፕሮጀክቶችን መረቁ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply