የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ድጋፍ ሲያደርጉ ለነበሩ አካላት እውቅና እየሰጠ ነው

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ድጋፍ ሲያደርጉ ለነበሩ አካላት እውቅና እየሰጠ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ በትምህርት ልማት ዘርፍ በተለያያ መልኩ ድጋፍ ሲያደርጉ ለነበሩ ተቋማት እና ግለሰቦች የእውቅና አሰጣጥ መርሀግብር እያካሄደ ነው።

በአዳማ ከተማ ገልመ አባ ገዳ እየተካሄደ ባለው መርሀግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ።

በመርሀግብሩም እውቅና የሚሰጣቸው ለትምህርት ሴክተሩ በተለያያ መልኩ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ ዩኒቨርሲቲዎች ፣ ባለሀብቶች ፣ መምህራን ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች እንዲሁም የተሻለ አፈፃፀምን ያስመዘገቡ ዞኖችና ወረዳዎች ናቸው።

በክልሉ የትምህርት ልማት ስራው ውጤታማ እንዲሆንም የህዝቡ ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበረ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ ገልፀው በዚህም ከህብረተሰቡ በተለያየ መልኩ ከ5.2 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን አንስተዋል።

በክልሉ ባለፈው የክረምት ወራት ብቻ በበጎ ፈቃድ 34 ሺ 200 በላይ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል።

ይህም 5 ቢሊዮን ብር የሚገመት መሆኑ ተገልጿል።

ትዝታ ደሳለኝ እና ረጋሳ ፍሮምሳ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ድጋፍ ሲያደርጉ ለነበሩ አካላት እውቅና እየሰጠ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply