የኦሮሚያ ክልል ከ500 ሺህ በላይ የክልሉን ሰራተኞች መረጃ ዲጂታል ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

የኦሮሚያ ክልል ከ500 ሺህ በላይ የክልሉን ሰራተኞች መረጃ ዲጂታል ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

አዲስአ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ከ500 ሺህ በላይ የክልሉን ሰራተኞች መረጃ ዲጂታል ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሐመድ የተመራ ቡድን በኦሮሚያ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ እየተካሄዱ ያሉ የዲጂታላይዜሽን ስራዎችን ጎብኝቷል፡፡

ቢሮው በክልሉ ባሉ ተቋማት ስር የሚሰሩ ከ500ሺህ በላይ የመንግስት ሰራተኞችን መረጃ ወደ ዲጂታል ለመቀየር የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ ቢሮው አሰራሩን ወደ ዲጂታል ለመቀየር የሚያደርገውን ጥረት ሚኒስቴሩ እንደሚደግፍና በትብብር ለመስራትም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ አቶ ነመራ ቡሊ ለዲታላይዜሽን ስራው ስኬት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እገዛ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

የኦሮሚያ የሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢኒጅነር ጂማ ቱሉ የክልሉን ዲጂታል ትራንስፎረሜሽን ለማፋጠን እና በክልሉ የሚከናወኑ የዲጂታል ስራዎችን በተቀናጀ ሁኔታ ለመምራት “የዲጂታል ኦሮሚያ ስትራቴጂን” ለመንደፍ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ዲጂታይዝ የሚያደርጋቸው ሰነዶች ከዚህ በፊት በክልሉ እየተተገበረ ካለው የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ ማኔጅመንት ሶፍተዌር አማካኝነት ወደ ስራ እንዲገባ ይደረጋል መባሉን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የኦሮሚያ ክልል ከ500 ሺህ በላይ የክልሉን ሰራተኞች መረጃ ዲጂታል ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply