የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ አካላት ከአሸባሪው ኦነግ ጋር በመሆን በሳሲጋ ወረዳ በጣሳ ጃርሶ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ ተኩስ ከፍተዋል፤ በቡድን መሳሪያ በመታገዝ ንጹሃንን እየጨፈጨፈ ስለመሆኑ የሚናገሩ…

የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ አካላት ከአሸባሪው ኦነግ ጋር በመሆን በሳሲጋ ወረዳ በጣሳ ጃርሶ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ ተኩስ ከፍተዋል፤ በቡድን መሳሪያ በመታገዝ ንጹሃንን እየጨፈጨፈ ስለመሆኑ የሚናገሩት አማራዎች የድረሱልን ጥሪ አቅርበዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 26 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ አካላት ከአሸባሪው ኦነግ ጋር በመሆን ህዳር ፣25/2015 ከቀኑ 5:30 ጀምሮ በሳሲጋ ወረዳ በጣሳ ጃርሶ ቀበሌ አማራዎች ላይ በቡድን መሳሪያ የታገዘ ተኩስ ከፍተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በጦርነቱ ምክንያት እየተሳደዱ ያሉ ንጹሃን አማራዎችን እያነጋገረ በነበረበት ወቅት ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር ለማወቅ ችሏል። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች የክልሉ ኃይሎች ጋር በመሆን በበጣሳ ጃርሶ ቀበሌ በተለምዶ 24 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚኖሩ አማራዎች ላይ የተደራጀ ጦርነት የከፈቱባቸው መሆኑን የገለጹት የአሚማ ምንጮች ሰላማዊ እና ንጹሃንን ሰዎችን እየጨፈጨፉ በመሆኑ እባካችሁ ድረሱልን ሲሉ ጥሪ አድርገዋል። በአካባቢው መከላከያ እንደሌለ የሚናገሩት ምንጮች ወደ ጫካ ወጥተን እየተሳደድን ነው፤ ጥቃቱ በጣም አስደንጋጭ ነው ብለውታል። በምስራቅ ወለጋ ዞን የሳሲጋ ወረዳ በሬዳን ጨምሮ ሌሎች አካባቢዎች ቀደም ብለው ሆንተብሎ በሚመስል አግባብ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ወረራ ስር እንዲያዙ ስለመደረጋቸው ምንጮች ተናግረዋል። ከነቀምት በ24 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው 24 አካባቢ በተደራጀ ጥቃት ስር መሆኗን ተገንዝባችሁ እባካችሁ በአስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ አቅርቡልን ሲሉ ተማጽነዋል። አማራ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች አገር አልባ ተደርጎ በተደራጁ ግፈኞች መጨፍጨፍ፣መሳደድ እና መፈናቀሉ ከጀመረ በርካታ ዓመታት የተቆጠሩ ቢሆንም ባለፉት 4 ዓመታት የደረሰበት እልቂትና መፈናቀል ግን በእጅጉ ከፍተኛ ስለመሆኑ በብዙዎች ዘንድ ሲገለጽ ይሰማል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply