የኦሮሚያ ክልል ጠቅሎይ አቃቤ ህግ አቶ ልደቱ አያሌው ላይ ያቀረበውን ሁለተኛ ክስ አሻሻለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ የኦሮሚያ…

የኦሮሚያ ክልል ጠቅሎይ አቃቤ ህግ አቶ ልደቱ አያሌው ላይ ያቀረበውን ሁለተኛ ክስ አሻሻለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኦሮሚያ…

የኦሮሚያ ክልል ጠቅሎይ አቃቤ ህግ አቶ ልደቱ አያሌው ላይ ያቀረበውን ሁለተኛ ክስ አሻሻለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ችሎት አቃቤ ሕግ ከዚህ በፊት ያቀረበው ክስ ተጣምሮ በመሆኑ እና ግልፅ ባለመሆኑ ተሻሽሎ አንዲቀርብ ለዛሬ በተሰጠው ቀጠሮ መሰረት ነው ክሱ ተሻሽሎ የቀረበው። በዚሁ መሰረትም አቶ ልደቱ አያሌው የወንጀል ህግ በመተላለፍ ፣ ህገ መንግስት እና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ የተለያዩ የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነዶችን አዘጋጅተው እና በፍተሻም የተያዘባቸው ነው ሲል አቃቤ ሀግ ክሱን ነጥሎ እና ግልፅ በማድረግ አሻሽሎ አቅርቧል። ክሱን የተቀበለው ፍርድ ቤቱ የተሻሻለውን ክስን በችሎት አንብቧል። የአቶ ልደቱ ጠበቆችም በተሻሻለው ክስ ላይ መቃወሚያቸውን በጽሁፍ እናቅርብ ሲሉ የጠየቁ ሲሆን በጥያቄያቸው መሰረት መቃወሚያቸውን ለመመልከት ለታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ስለመሰጠቱ ኡዴፓ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply