የኦሮሚያ ጤና ቢሮ በክልሉ ያለው ግጭት የጤና ስርአቱን ሁሉም ቦታ ደርሶ የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት እንቅፋት ሆኖብኛል ሲል ገለፀ፡፡

በችግር የተጎዱ አካባቢዎች ላይ የባለሙያዎች እጥረቶች እንዳሉና የህክምና መስጫ መሳሪዎችን አንቀሳቅሶ መስራት ባለመቻላቸው ችግሮች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡

በኦሮሚያ ጤና ቢሮ የጤና ስርአት ጥራት ኢኖቬሽን እና ሊደርሺፕ ዳሬክተር ደረጄ አብዲሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት እንደ ኦሮሚያ ክልል ከአንድ መቶ 20 በላይ ሆሰፒታሎች፣ ከ1 ሺ 4 መቶ በላይ ጤና ጣቢያዎች እና ከ7 ሺ በላይ ጤና ኬላዎች መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡

ሆኖም ሁሉንም የጤና ተቋማት በእኩል ደረጃ ተደራሸ ማድረግ እንዳልተቻለም አንስተዋል፡፡
የጤና አገልግሎት ከፍተኛ በጀት ስለሚፈልግ በቂ የሆነ በጀት አለመኖሩም ስራቸው ላይ ችግር እንደሆነባቸው ተናግረዋል፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ህብረተሰቡን በማሳተፍ የችግሩን መንስኤ በማጥናትና የመፍቻ መንገዶችን በማዝጋጀት ላይ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

ያሉትን ግብአቶችም በተቻለ መልኩ በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ተደራሽ የማድረግ ስራዎችን እየሰሩ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ጥራት ማምጣት የሚቻለው ብዙ ሀብት ንብረት ስላለ ሳይሆን የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት ስንችል ስለሆነ የህብረተሰቡ የጤና ችግር ምን እንደሆነ በህብረተሰቡ በኩል ሆኖ ችግሩን መረዳት አስፈላጊ መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply