
የኦሮሚያ ፀጥታ ኃይሎች የአማራ ተወላጆች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ማገዳቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ መነሻቸውን ከሰሜን እና ደቡብ ወሎ ወሎ ያደረጉ የአማራ ተወላጅ የሆኑ መንገደኞች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ በኦሮሚያ ፀጥታ ኃይሎች መታገዳቸውን ተናግረዋል። መንገደኞቹ ሸኖ ላይ ሲደርሱ የአማራ ተወላጅ የሆኑት ተለይተው ከተሳፈሩበት ተሽከርካሪ እንዲወርዱ ከተደረጉ ቦኋላ ወደ አዲስ አበባ መግባት እንደማይችሉ የተነገሩ ሲሆን ነገር ግን የሌላ ብሔር ተወላጆች እንዲያልፉ ተፈቅዶላቸዋል ብለዋል። ከመንገደኞቹ መካከል የህክምና እና የውጭ አገራት የጉዞ ቀጠሮ ያለባቸው ሰዎች እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ከመታገዳቸው በተጨማሪ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ነው ለማረጋገጥ የተቻለው። ተጓዦችን በማንነታቸው እየለዩ እገዳ የሚፈፅሙት የኦሮሚያ ፀጥታ አካላት መሆናቸውን የገለፁት መንገደኞቹ፡ የኦሮሚያ ክልል መንግስትን ስርዓት የሚያሲይዝ የበላይ አካል መጥፋቱን ጠቁመዋል። የኦሮሚያ ፀጥታ ኃይሎች ከደብረ ብርሀን አዲስ አበባ ባለው የፌደራል መንገድ በተጨማሪ በጎኅፂዮን አድርገው ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ የአማራ ተወላጅ የሆኑ መንገደኞችን እያገዱ መሆናቸው ተረጋግጧል። ከባለፈው አመት ወዲህ ይህ ችግር በተደጋጋሚ እየተፈጠረ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን የፌደራል መንግስቱም መፍትሔ ከማስቀመጥ ይልቅ ዝምታን መርጧል። አማራ ድምፅ ሚዲያ እንደዘገበው።
Source: Link to the Post