የኦሮማራ መድረክ የፊታችን ሐሙስ በባህርዳር   ይደረጋል፡፡ (አሻራ ጥር 2፣ 2013ዓ.ም) የህወኃትን የበላይነት ከማሽመድመድ ውጭ በኢትዮጵያ  ፖለቲካ ብዙም ፋይዳ የሌለው የኦሮማራ መድረክ…

የኦሮማራ መድረክ የፊታችን ሐሙስ በባህርዳር ይደረጋል፡፡ (አሻራ ጥር 2፣ 2013ዓ.ም) የህወኃትን የበላይነት ከማሽመድመድ ውጭ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ብዙም ፋይዳ የሌለው የኦሮማራ መድረክ…

የኦሮማራ መድረክ የፊታችን ሐሙስ በባህርዳር ይደረጋል፡፡ (አሻራ ጥር 2፣ 2013ዓ.ም) የህወኃትን የበላይነት ከማሽመድመድ ውጭ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ብዙም ፋይዳ የሌለው የኦሮማራ መድረክ ሀሙስ በቀን 6 በባህርዳር እንደሚደረግ ተሰምቷል፡፡ በመድረኩ የኢትዮጵያ ሁኔታ እና የሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት ይተርክበታል ተብሎ ታስቧል፡፡ በመድረኩ የአማራ ነክ ፓርቲዎች እና የኦሮሞ ነክ ፓርቲዎች የሚሳተፉ ሲሆን ኦነግ እና አፌኮ ግን ኦሮማራ የሚባል ምናባዊ ፖለቲካ የለም ሲሉ ሰንብተዋል፡፡ ባለፈውም በአዲስ አበባ በተደረገው ስብሰባ ኦነግ እና ኦፌኮ አኩርፈው ስብሰባውን ሲነቅፉት ተስተውሏል፡፡ የሁለቱ ህዝብ ፓርቲዎች በህዝቦች አንድነት፣በታሪክ አረዳድ እና መሰል ዙሪያዎች ውይይት ከውይይት ያለፈ ስምምነት ቢደረግም ጠብ የሚል ለውጥ ግን አልመጣም፡፡ አማራ ከወለጋ እና ከሸዋ ከርዕስቱ እየተፈናቀለ እና እየሞተ ነው፡፡ የመተከል ጉዳይ ላይ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እጅ አለበት የሚለውም በስፋት እየተነገረ ነው፡፡ አሁን ላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በአማራ እና በኦሮሞ ፖለቲከኞች ሽኩቻ የተሞላ ሆኗል፡፡ በሁለቱ ሽኩቻ ምክንያት ቀጣይ ምርጫ እና የሀገሪቱ መፃኢ ዕድል ይሰናከላል በሚል ኦሮማራ አስፈላጊ ሆኗል፡፡ ከኦሮማራ ይልቅ በሀገሪቱ ላይ የህግ እና የፖለቲካ ማሻሻያ ማድረግ ለህዝቦች አንድነት ይጠቅማል የሚሉት ብዙዎች ናቸው፡፡ በህወኃት ነጣጣይ ህገመንግስት እና ስራዓት እየተመሩ ግን በካድሬዎች ስብሰባ ብቻ መፍትሄ ሊመጣ አይችልም እየተባለ ነው፡፡ ያም ተባለ ግን በአማራ ምሁራን መማክርት አመቻችነት መድረኩ ሐሙስ ይደረጋል፡፡ የአማራ ምሁራን መማክርትም ከነገ ሰኞ እስከ ማክሰኞ አጋር አካላትን አካቶ በባህርዳር ምክክር ያደርጋል፡፡ ምክክሩ ግን ማለዘቢያ እና ማከኪያ ካልሆነ በስተቀር በአማራ ብሎም በኢትዮጵያ ፖለቲካ የረባ ሚና አያመጣም የሚሉ ተንታኞች አሉ፡፡ የምሁራን መማክርቱ ስልጣን እና ጥቅም ፈላጊ መሆኑ ነፃ እና ገለልተኛ ሆኖ እንዳይቆም አድርጎታል ሲሉም አስተያያታቸውን ለአሻራ የሰጡ ተንታኞች ተናግረዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply