የኦሮማይ፣ የቀይ ኮከብ ዘመቻ ፀሃፊ የበዓሉ ግርማ ባለቤት አልማዝ አበራ አረፉ! ሕዳር 01 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ወይዘሮ አልማዝ ደጀን ክፍት አድርጌ በዓሉን እጠብቀዋለ…

የኦሮማይ፣ የቀይ ኮከብ ዘመቻ ፀሃፊ የበዓሉ ግርማ ባለቤት አልማዝ አበራ አረፉ! ሕዳር 01 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ወይዘሮ አልማዝ ደጀን ክፍት አድርጌ በዓሉን እጠብቀዋለሁ እያሉ አርባዓመታትን ጠብቀዋል። በዓሉ ግን ጠፍቶ ቀረ። ሚስጢራዊ የደራሲ በዓሉ ግርማ አጠፋፍ ዛሬም ድረስ አወዛጋቢ ነው። ኮሌኔል መንግስቱ ሀይለማርያም፣ በዓሉን እኔ አላስገደልኩትም ሲሉ በመፅሃፋቸው ላይ ገልፀዋል። ብዙዎች ግን በዓሉ የኤርትራ እና የኢትዮጵያን ጦርነት በኦሮማይ ልብወለዱ በመቃወሙ በደርግ ተገሏል እያሉ ነው። መልከመልካሙ በዓሉ ግርማ በ2005 ዓም ባህርዳር ጣና ሀይቅ ዳጋ ገዳም ታየ ተብሎ ወከባ ተፈጥሮ ነበር። በሗላ ግን በዓሉ አለመሆኑ ተረጋግጧል። በዓሉ ከቤቱ እንደወጣ ሳይመለስ የቀረ ደራሲ ነው። ባለቤቱ አልማዝ አበራ በዓሉ አልሞተም፣ ቤት ይመጣል እያሉ እንደጠበቁ ከትናንት ወዲያ ምሽት ማረፋቸው ታውቋል። የበዓሉ ድርሰቶች እንዲያምሩ የባለቤቱ የአልማዝ አበራ ሚና ከፍተኛ ነበር። የዝነኛው ደራሲ በዓሉ ግርማ ባለቤት ወ/ሮ አልማዝ አበራ ዛሬ ሱማሌ ተራ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ተሰምቷል፤ ወ/ሮ አልማዝ ሁሌም ስለባለቤቷ እና ስለልጆቿ አባት ተናግራ አታበቃም ነበር፤ ዓመት በዓልን ጠብቄ ስደውልላት እንኳ ከሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ቀጥሎ አጀንዳው በዓሉ ነበር ይላል ጋዜጠኛ ታምራት ሀይሉ። የዛሬ 8 ዓመት ለታሪክ እንዲሆን ከሶስት ሰዓታት በላይ ያደረግነው ቃለ ምልልስ ላይ በበዓሉ ጉዳይ ተስፋዋ እንዳልተሟጠጠ ይታይ ነበር፤ ‹ በዓሉ ይመጣል ብዬ አሁንም በር በሩን አያለሁ›› ነበር ያለችኝ፤ ‹መጨረሻውን የሚያውቁ ሁሉ ለህሊናቸው ሲሉ ቢናገሩ ጥሩ ነው › የምትለው ወ/ሮ አልማዝ ባዶ ቤት ሶስት ልጆቹን ጥሎ እንደ ወጣ የቀረውን ባለቤተቷን ፅናት ተጋርታ ልጆቿን አስተምራ ለወግ ለማዕረግ ያበቃች ጠንካራ ሴት ናት። በዓሉ ግርማ የካቲት 24 ቀን 1976 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 11 ገደማ ከቤቱ እንደወጣ አልተመለሰም፤ ለባለቤቱም ሆነ ለልጆቹ እዚህ ነው የወደቀው፤ እዚያ ነው የተቀበረው ብሎ የነገራቸው ሰው የለም፤ ጉዳዩን ያውቃሉ የተባሉ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት መንግስቱ ኃይለማርያም ጀምሮ ወንጀሉን ሲያድበሰብሱት ኖረዋል፤ ባለቤቱ ግን አሁንም በር በሩን እያየች ኖራ ኖራ ኖራ ዛሬ ወደ እርሱ ጋር ሄዳለች። መቼም የኢትዮጵያ አገዛዞች ጀግና እየበሉ ቀጥለዋል። ደርግ በዓሉ ግርማን በላ፣ ኢህአዴግ እና ብልፅግናም ከደርግ በባሰ ደህና ሰውን ማጥፋታቸውን ቀጥለዋል። ዘገባው የሳተናው ሚዲያ ነው። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply