You are currently viewing “የኦሮሞን ህዝብ ከቀየው አዲስ አበባ መግፋትና ማሳደድ አክትሞለታል”   ሽመልስ አብዲሳ

“የኦሮሞን ህዝብ ከቀየው አዲስ አበባ መግፋትና ማሳደድ አክትሞለታል” ሽመልስ አብዲሳ

ዋዜማ- የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በግፍና በኢ-ፍትሀዊነት  ከቀየው ፊንፊኔ (አዲስ አበባ) እንዲሰደድ የተደረገውን የኦሮሞ ሕዝብ ወደ ቀደመ ስፍራው  እንዲመለስ እያደረግን ነው ሲሉ በይፋዊ ማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ተናግረዋል።

የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት ሲደርስበት በነበረው መገፋት የተነሳ ከተማዋን ለሌሎች ለቆ እስከመውጣት ደርሷል ያሉት ሽመልስ፣ይህም መገፋት ሄዶ ሄዶ እትብቱ በተቀበረባት ፊንፊኔ (አዲስ አበባ) የባዕድነት ስሜት እንዲሰማውና በራሱ ቀየ ላይ ባይተዋር እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል።

ከተማዋ በሌሎች የበላይነት ስር ሆና በተለይም የኦሮሞን ሕዝብ ለዘመናት እንደ ባዕድ የመመልከት አካሄድን ስትከተል ቆይታለች ያሉት ርዕሰ መሥተዳድሩ፣ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በከተማዋ አንዳችም የኦሮሞን ህዝብ ማንነት የሚገልጽ ምልክት (symbolic represention) አለመኖሩ ነበር በማለት ጠቁመዋል።

“ከዚህ በኋላ ግን መንግሥታችን፣ያለፈውን የውድቀት ታሪክ፣ጉዳትና መፈናቀል ማውራት፣ እንዲህ ተደረግን ብሎ ስሞታ ማቅረብ አይሻም” ሲሉ ገልጸዋል።

ይልቁንም የተገኘውን ዕድል በመጠቀም፣ትላንት በሕዝባችን ላይ ሲደርስ የነበረውን ግፍና በደል ለመካስ ብሎም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም አዲስ ምዕራፍ ከፍተን ወደ ሥራ ገብተናል ብለዋል።

በዚህም መሠረት፣መንግሥት በግፍ ከቀየው የተፈናቀለውን ሕዝብ በመመለስ በከተማዋ በሁሉም ዘርፍ ካሉ ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራ ይገኛልም ሲሉ ጠቁመዋል።

አዲስ አበባን በዚህ ወቅት ስንመለከት፣ በፖለቲካው፣በኢኮኖሚ፣በማኅበራዊ እንዲሁም በባሕል የሕዝባችንን ሰፊ ተሳትፎ የሚሹ እጅግ ግዙፍ የሆኑ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ ይገኛሉ ያሉት ሽመልስ፣ይህም ሀሳባችንን ከግብ ለማድረስ ትልቅ መሳሪያ ይሆነናል ብለዋል።

እየተሠሩ ካሉት ከነዚህ ፕሮጀክቶች መካከል፣የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣የኦቢኤን ሚዲያ ኮምፕሌክስ፣የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተፕራይዝ፣የኦሮሞ አርት ማሠልጠኛ ማዕከል፣የኦሮሞ ባሕላዊ ምግብ አሰራርና ዝግጅት ማዕከል፣የኦሮሞ ባሕላዊ እቃዎች ማሳያና የገበያ ማዕከል፣ሲንቄ ባንክ፣ቡሳ ጎኖፋ እንዲሁም የተለያዩ ኢንተርፕራይዞችን በጥቂቱ ማንሳት ይቻላል ሲሉ ገልጸዋል።

እስካሁን ያለው አፈጻጸም፣መንግሥት የሕዝባችንን የዘመናት ጥያቄና እውነትን ወደ ቦታዋ ለመመለስ እንዲሁም ቃል የተገባውን ለመፈጸም ያለውን ቁርጠኛነት ያሳየ ነው ብለዋል።

አሁንም የሕዝባችንን ያልተመለሱ ጥያቄዎች በሂደት ለመመለስ በትኩረት እንሰራለን ያሉት ርዕሰ መሥተዳድሩ፣ሕዝባችንን ከከተማው መግፋትና ማሳደድ ግን ከዚህ በኋላ አክትሞለታል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። [ዋዜማ]

The post “የኦሮሞን ህዝብ ከቀየው አዲስ አበባ መግፋትና ማሳደድ አክትሞለታል” ሽመልስ አብዲሳ first appeared on Wazemaradio.

The post “የኦሮሞን ህዝብ ከቀየው አዲስ አበባ መግፋትና ማሳደድ አክትሞለታል” ሽመልስ አብዲሳ appeared first on Wazemaradio.

Source: Link to the Post

This Post Has One Comment

  1. Tesfa

    የደንቆሮ ጩኸት መልሶ ደጋግሞ ይባላል። ጉረኛው ሽመልስ አብዲሳ ሜዳ ተገኘ ብሎ ያለ ልጓም መጋለቡ የኦሮሞን ህዝብ ዋጋ ያስከፍላል እንጂ ሰላምን አይሰጥም። ውሾች ሁልጊዜ የሚጣሉትና የሚጮኹት በቆሻሻ ክምር ነው። የሚያዪት ነገር የለም። በሽታው ግን ምግብ አለ በማለት እርስ በእርስ ይናከሳሉ። ሌላውን የህበረተሰብ ክፍል እያፈናቀለና እያሳደደ፤ እያሰረ፤ እየገደለ ጊዜው የእኛ ነው ብሎ መጨፈር በኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች የተጀመረ አይደለም። ወያኔም ጊዜ ጥሎት ከሥርቻ ውስጥ ገብቶ ትግራይ ላይ እስኪደበቅ ድረስ ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት እልፍ በደል ፈጽሟል አሁም በመፈጸም ላይ ይገኛል። የብሄር የፓለቲካ ሰካራሞች ራስን እንጂ ሌላውን አያዩም። ጠ/ሚሩ በመደመር ሂሳብ ሰውን መቀነስ ከጀመረ ወዲህ ኦሮምኛ ተናጋሪ የሆኑ በውጭና በሃገር ውስጥ ያሉ ሁሉ ጊዜው የእኛ ነው በማለት እቃቸውን ጠቅለው የተመለሱ ሥልጣን የተሰጣቸው፤ ወይም በተመላላሽ የመንግስት ተላላኪና አትራፊ ነጋዴዎች የሆኑ ቁጥራቸው ብዙ ነው። የዓሳ ግማቱ ከጭንቅላቱ እንዲሉ “አዲስ አበባ ውስጥ ኦሮሞ ጠል በዝቷል” በማለት ጠ/ሚሩ በሰው ላይ ጥላቻን ከዘራበት ጊዜ ጀምሮ በህቡዕና በይፋ ሰዎች ይመነጠራሉ። ቤቶች/የታሪክ አሻራዎች ያለምንም ርህራሄ ይናዳሉ። በሥፍራው በልማት ስም ይህም ያም ይቆማል። አቶ ሽመልስ በአዲስ አበባ እስከ አሁን በኦሮሞ ህዝብ የተሰሩትን ሲቆጥር የዘነጋው ነገር በእነማን እንባ በእነማን ደም በማን ሃብት እንደተገነባ አለመናገሩ ነው። እንኳን ይህ የሰንበሌጥ ግንባታ ይቅርና ለዘላለም ይቆማሉ የተባሉ ሃውልቶችና ቤቶች በህዝብ አመጽ ወድመዋል። የአንዲት ሃገር የመንግስት አጥር ህዝብ ነው። የአንዲት ሃገር የላእላይና የታህታይ መዋቅር ተቋማት ጠባቂው ህዝብ ነው። ሌላውን እያገለሉ ለእኔ ብቻ መባሉ ጥፋትን ያስከትላል እንጂ ሰላምን አያመጣም።
    ብልጽግና በአንድ መልኩ ደርግን ይመስላል። አረቋ ላይ ተቀምጦ ለምን እርጥበት ይሰማኛል የሚሉ ጅሎች። ለገባው የሽዋ ኦሮሞ ከሃረሩ፤ የወለጋው ከአርሲው፤ የጅማው ከሌሎቹ ወዘተ በስነ ልቦናም ሆነ በአስተሳሰብ አይገጣጠሙም። የሚነገድባቸው ግን በወል ስማቸው ኦሮሞ ነው። እንደ ሽመልስ አብዲሳ ያሉት ከፋፋዪች በስልጣን ላይ መቆየት ለኦሮሞ ህዝብ ጥፋት እንጂ ጥቅምን አያስገኙም። ልብ ያለው ነገሮች በጊዜ እንዲስተካከሉ መስራት አለበት። ያለበለዚያ ሽመልስ በስም እየጠቀሰ ለኦሮሞ ህዝብ የሰራነው በማለት የሚያላግጠውም ሆነ የኦሮሞን ህዝብ በሰፈራ ወደ አዲስ አበባ እንመልሳለን የሚለው ድንፋታው ትርፍ ሳይሆን የከተማ ጦርነትን ቀስቃሽ ነው። አዲስ አበባ በታሪኳ የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሆና አታውቅም። የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መናኸሪያ እንጂ! አንድ መንግስት ምንም ያህል ትጥቅ ቢኖረው፤ በወታደራዊ ሃይሉ ብቻ ስልጣን ላይ ዘንተ ዓለም ሊቆይ አይችልም። በማፈን፤ በመግደል፤ በማሳደድ፤ መከራ በማዝነብ ቢሆን ኑሮ ደርግና ወያኔ ዛሬም በሸለሉ ነበር። ግን ታሪክ ሆነዋል።
    ጠ/ሚሩ ተናግሮ የማይደክመው ፍጡር ነው። በቅርቡ ስለ ዲጂታል ጉዳይ ሲናገር ለሰማው ምን ያህል አለማወቁን ነበር የሚረዳው። ምን አለ ሁሉን ለባለሙያ ብቻ ቢሰጥ። ሁሉን አውቆ የኖረና ያለፈ የለምና። ቁጥርን ከቁጥር እያጋጩ እንዲህና እንዲያ እያሉ በየመድረኩ መዘባረቅ ትዝብ እንጂ ላድማጭ ትምህርት አይሰጥም። እኔ ጠ/ሚሩ አሃዝ እየጠቀሰ ሲያወራ አንድ ያነበብኩት መጽሃፍ ትውስ አለኝ። How to Lie with Statistics -Darrell Huff. ለዚህ ይሆን አንዳንድ የድጂታል ተሳታፊዎች ጠ/ሚሩ ሲናገር ፈገግ ይሉ የነበሩት? አዎን ስቆ ማሳለፍ ለቻለ መልካም ነው። ግን ምድሪቱ ስቆም ሆነ አልቅሶ የማይኖርባት ምድር ሆናለች። አቶ ሽመልስ ጠላት እያለ ደጋግመው የሚጠራው እነማን እንደሆኑ በምድሪቱ ላይ የሚሰራው ግፍ ያሳያል። ግን ለሁሉም ጊዜ አለው ብሎ የለ ሰለሞን ሰው በሰፈረበት መስፈሪያ ለራሱም ሞልቶ እስኪፈስ ይሰፈርለታል። እንኳን የሃበሻው ገዳዳ ፓለቲካ ቀርቶ የሮም መንግስትም ተንዷል። የኢትዮጵያ ችግር እጅግ የተወሳሰበና በዘርና በቋንቋ በክልል መርዝ የተለወሰ በመሆኑ አሁን ከምናየው መጠፋፋት በላይ መጭው ጊዜ ያስፈራል። መቀሌ ላይ ተቀምጠው በጉልበት ከወሎና ከአማራ የቆረሷቸውን መሬቶ ካልተመለሱ ዋ እንተያያለን የሚሉን ወያኔዎች ጥርስ የሌለው አንበሳ መሆናቸው አልገባቸውም። ከአሁን በህዋላ እነርሱ እየገደሉ ሌላው እየሞተ የሚኖርበት ጊዜ አክትሟል። ውጤቱ ተያይዞ ማለቅ ነው። ጌታቸው ረዳ ያን ሁሉ ዲስኩር በ 3 ጊዜው ጦርነት ደስኩሮ አሁን የሰላም ሰው መስሎ መቅረቡ ለእርሱም ለትግራይ ህዝብም አይበጅም። አዲስ አመራር አዲስ ትውልድ አዲስ እይታ ነው የትግራይ ህዝብ የሚፈልገው እንጂ ይህ ያንተ መሬት ነው ያ የእኔ ነው እያለ ዝንተ ዓለም ሲገድልና ሲሞት መኖርን አይፈልግም። ወልቃይት፤ ራያ ገለመሌ የሁሉም ኢትዮጵያዊ እንጂ የክልል ፓለቲካ በፈጠረው ትርክት የእኔ ነው ባይ ብቻ የሚፈነጥዝበት ምድር ሊሆን አይገባም። ሰው አልገባውም እንጂ ጦርነቱ ቀጣይ ነው። የሃገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ትግራይና አማራ በሚቆራቆሱበት ቦታ ይሰፍራል መባሉ እግሩ ለተቆረጠ የፋሻ ሽፋን እንደማድረግ ይቆጠራል። ለውጥ የለም። ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ። አማራውም ወያኔውም ይህን የመንግስት አሰላለፍ አልፈለገውም። ግን አማራና ትግራይ ሲራኮቱ ኦሮሞው ቤቱን ይሰራል። የወያኔን የቆየ የፓለቲካ ስልት እንዳለ ሰልቅጦ የሚገለገሉበት ጠባቦች የኦሮሞ ብሄርተኛች ካለፈው ታሪክ መማር አይፈልጉም። የሽመልስ ድንፋታ፤ የጠ/ሚሩ የመደመር ሂሳብና የቅነሳ ስልቱ ሃገሪቱን ወደ ከፋ የመተላለቅ መንገድ ይመራታል እንጂ ፍትህና ሰላምን ለህዝባችን አያመጣም። ጊዜ በደመና ሲሸፈን የበላና ያስበላ፤ የገደለና ያሰረ፤ ያፈናቀለና በዘር ፓለቲካ የነገደ ሁሉ ትርፍ አልባ ይሆናል። ሰው ግን ጅል ነው። እኖራለሁ እንጂ እሞታለሁን አያስብም። በቃኝ!

Leave a Reply