የኦሮሞ ህዝብ ያገኘውን ለውጥ በማስቀጠል ሠላሙን መጠበቅና አንድነቱን ማጽናት አለበት አሉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የመሩት የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል ከ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/FRVDeRSZtw7l3TD9WpWiuTxskFfPw4W3vOvgXUtf6BZ7_270VKwFxy07uUqa2GKj_ygabFy2mgHWGOyoPWginsPsWPfpmXvcYaou2ZPd_H4G-s9OaEzXLXgDZvTtO1B-MUp-xiX7O1IuNIwlBTISGeV0gRNqAaAJTZSiqJu1-Di2ycsxPT0Ev7Wv7WXiGGAIOyaeURL-jSL2iXBc0OZTkACbM1OnBgdmOrJpT2LPUfQ1CEn14JSi89Yk88hnN9gZwZgZcyhRY42wkKPifcgDWUbqFGPWaC30WdhlNGAxR_QIr8QmTXAa12J1qI7hl6QNSN33KChk96QiXfbZ-CpCPg.jpg

የኦሮሞ ህዝብ ያገኘውን ለውጥ በማስቀጠል ሠላሙን መጠበቅና አንድነቱን ማጽናት አለበት አሉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የመሩት የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የባለሥልጣናት ጓድ የምዕራብ ኦሮሚያ የወለጋ ዞኖችን ለመጎብኘት ዛሬ ጠዋት ነቀምት ገብቷል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ ፅሕፈት ቤት ዛሬ በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ ገፁ እንደዘገበዉ ዶክተር ዓብይ አሕመድ የመሩት የመልዕክተኞች ጓድ ነቀምት አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኦሮሞ ህዝብ ያገኘውን ለውጥ በማስቀጠል ሠላሙን መጠበቅና አንድነቱን ማጽናት እንዳለበት ወለጋ ስታድየም በተደረገ ዝግጅት ላይ ተናግረዋል::

ዉስጥ አዋቂ ምንጮጭ ነገሮኝ ብሉ ዶቼቪሊ እንደዘገበው በጠቅላይ ሚንስትሩ በወለጋ ጉብኝታቸዉ ከአራቱም የወለጋ ዞኖች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ አላቸዉ።

አራቱ የወለጋ ዞኖች ባለፉት አምስት አመታት በኢትዮጵያ መንግስት የመከላከያ ሠራዊት፣ በኦሮሚያ ክልል ፀጥታ አስከባሪዎችና በአካባቢዉ በሸመቀዉና መንግስት ኦነግ ሸኔ በሚል ስም በአሸባሪነት በፈረጀዉ ነገር ግን ራሱን የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ሠራዊት (OLA) ብሎ በሚጠራዉ ታጣቂ ቡድን መካከል ተደጋጋሚ ዉጊያ የሚደረግባቸዉ አካባቢዎች ናቸዉ።

በዉጊያዉ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሠላማዊ ሰዉ አንዳዴ በአሰቃቂ ርምጃ ተገድሏል፤ በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ተፈናቅሏል።

ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ምክትል ጠቅላይ ሚንስር ተመስገን ጥሩነሕ፣ የሕዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች አፈ-ጉባኤያትና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ወደ ነቀምት ተጉዘዋል።

ሚያዚያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply