You are currently viewing የኦሮሞ ልዩ ኃይል ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጋር በመሆን በኪረሞ ወረዳ ቤተሰቦቻቸውን አስሮ ከገደለባቸው እና ካሳደዳቸው መካከል ሶስት ህጻናት በህይወት ተገኝተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የኦሮሞ ልዩ ኃይል ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጋር በመሆን በኪረሞ ወረዳ ቤተሰቦቻቸውን አስሮ ከገደለባቸው እና ካሳደዳቸው መካከል ሶስት ህጻናት በህይወት ተገኝተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የኦሮሞ ልዩ ኃይል ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጋር በመሆን በኪረሞ ወረዳ ቤተሰቦቻቸውን አስሮ ከገደለባቸው እና ካሳደዳቸው መካከል ሶስት ህጻናት በህይወት ተገኝተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 8 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በህዳር 10/2015 ዓ.ም በምስራቅ ወለጋ ዞን በኪረሙ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በአቶ ፍቃዱ ሁንዴ የተመራው የአማራ ተወላጆችን የማጥፋት ዘመቻ መፈጸሙ ይታወቃል። ከዘመዶቻቸው ሞት ተርፈው በኦሮሚያ ልዩ ኃይል እገታ የነበሩ ሶስት ህጻናት መጋቢት 8/2015 በተሰጠው ጥቆማ መሰረት በመከላከያ ሰራዊት አማካኝነት መገኘታቸው ታውቋል። በአቶ ፍቃዱ ሁንዴ ጦራቸውን እየመሩ፣ በየአማራ ቤቶች በመዘዋወር የጦርነት አታሞ በመምታት የዘር ማጥፋት ጀምረዋል። ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ በተጨማሪ በከተማዋ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ በኦሮሚያ ፖሊስ የወረዳው ምድብ፣ በቄሮዎች፣ በቀሬዎች፣ ልዩ ተዋጊ፣ ሽምቅ ተዋጊዎች እና በወረዳው በሚገኙ የኦሮሞ ሚሊሻዎች በተጨማሪም የወረዳው በዋና ከተማ በሆነችው የኪረሙ ከተማ የሚገኙ የኦሮሞ ማህበረሰብ በአጠቃላይ በአማራ ተወላጆች ላይ ጭፍጨፋ መፈጸሙ ተገልጧል። በሰዓቱ በእስር ላይ የነበሩት 81ዱ በአሰቃቂ ሁኔታ ስለመገደላቸው ተገልጧል። የአማራ ህዝብ በአራቱም መዓዘናት በተከፈተበት ጦርነት መውጫ አጥቶ፣ ደረስኩልህ የሚለው መንግስት አጥቶ እየተሰቃዩ ነው። በዚህ ጭንቀት ውስጥ የአማራ ተወላጆች እግር ወደአመራቸው እየሮጡ ነው። ይሁን እንጂ በተለያዩ ጊዜያት ህጻናት፣ አዛውንቶች፣ ሴቶች እና በህመም የሚሰቃዩ ሁሉ የጥይት እራት ሆነዋል፤ የተረፉት ደግሞ ታግተዋል። በአሰቃቂ ሁኔታ በህግ ጥላ ስር ሆነው ከተገደሉት በተጨማሪ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አግቷቸው፤ በዕለቱ ከተረፉት ከቤተሰቦቻቸው ጋር በገንዘብ እየተደራደረባቸው ቆይተዋል። ከእነዚህ ህጻናት መካከል፦ 1) ሞሚና ጅብሪል፣ 2) ፈሪሃ ሠይድ እና 3) ሀያት ሰይድ የተባሉ ህጻናት ይገኙበታል። እነዚህ ሶስት ህጻናት ከህዳር 10/2015 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሞ ልዩ ኃይል ታግተው፤ በመጨረሻም መጋቢት 8/2015 ዓ.ም በመከላከያ ሠራዊት እጅ መግባታቸው ታውቋል። ለመረጃው_አጉልዞን በምንጭነት ተጠቅመናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply