የኦሮሞ ታጋዮች ፋውንዴሽን በአዲስ አበባ ባለ 15 ወለል ህንፃ ሊያስገነባ ነው

የኦሮሞ ታጋዮች ፋውንዴሽን በአዲስ አበባ ባለ 15 ወለል ህንፃ ሊያስገነባ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሞ ታጋዮች ፋውንዴሽን በ1 ቢሊየን ብር ባለ 15 ወለል ህንፃ ሊያስገነባ ነው፡፡
ፋውንዴሽኑ የኦሮሞ ታጋዮችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በኢኮኖሚ ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ ያግዛል ተብሏል፡፡
በ2008 ዓ.ም የተመሰረተው ይህ ፋውንዴሽን የራሱን ባለ 15 ወለል ህንፃ በ1 ቢሊየን ብር በአዲስ አበባ ካሳንችስ አካባቢ የሚገነባ ይሆናል፡፡
ለሚያስገነባው ህንጻም በዛሬው እለት ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ጋር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
የግንባታ ስራው በ2 አመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡
ተመሳሳይ ህንፃዎች በሌሎች ከተሞችም እንደሚያስገነባ ፋውንዴሽኑ ገልጿል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የኦሮሞ ታጋዮች ፋውንዴሽን በአዲስ አበባ ባለ 15 ወለል ህንፃ ሊያስገነባ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply