
ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የትጥቅ ግጭት ውስጥ ያለው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሰላም ንግግር ጥያቄ ከመንግሥት አልቀረበልኝም አለ። አማጺው ቡድን ይህን ያለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕምድ ማክሰኞ መጋቢት 19/2015 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከታጣቂው ጋር ንግግር ለማድረግ መንግሥታቸው ያደረገው በርካታ ጥረት አለመሳካቱን ከተናገሩ በኋላ ባወጣው መግለጫ ነው።
Source: Link to the Post