የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከትግራይ ልዩ ሃይል ጋር በማበር በአገር መከላከያ ሰራዊት ጥቃት የተሳተፉ አባላቱን እያጠራ መሆኑን አስታወቀ።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ከታጠቁ እና ጸረ -ሰላም ከሆኑ ሀይሎች ጋር ግንኙነት ያላቸውን አባላቱን በመለየት እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡

የግንባሩ ቃላ ቀባይ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ለኤትዮ ኤፍ ኤም እንዳሳወቁት ከሰሞኑ በተለያዩ የመንግስት መግለጫዎች ከህወሃት ቡድን ጋር የኦነግ ሸኔ አባላት በጦርነቱ መሳተፋቸው ተነግሯል፡፡

ይሆን እንጂ ኦነግ የሚለው ስም ከዚህ ተቀጥሎ እንዳይጠራ እየተነጋገርን ነው ብለዋል፡፡

ምክንያቱም እኛ ከሸኔ ጋር ግንኙነት የለንም ፤የታጠቀ ሰራዊትም የለንም ነው ያሉት፡፡

ኦነግ በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ ምህዳሩን ተቀላቅሏል፣ የምንሰብቀው ጦርም የለም በእኛ ስም የሚንቀሳቀስ የታጠቀ ሃይል ካለ መንግስት እርምጃ ይውሰድ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እንዲህ አይነት ተግራት ላይ የሚሳተፉ እንዲሁም በተዘዋዋሪ ደግሞ ድጋፍ የሚሰጡና የሚያሰባስቡ አባላቶቻችንን እየለየን ነው ብለዋል አቶ ቀጀላ፡፡

መንግስት በሚሰጣቸው መግለጫዎች የኦነግ ሸኔ አባላት ሳይሆን የሸኔ ታጣዊዎች እንዲልም አሳስበዋል፡፡

አቶ ቀጀላ እንዳሉት በቀደመው ዘመን ሸኔ ማለት የስራ አስፈጻሚ አባላት የሚጠሩበት እንደነበር አስታውሰው በኃላ ላይ ግን ይህንን ስም አሁን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቲ በሚል እየተጠራ ነው ብለውናል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ትኩስ ትኩስ ዜናዎችን፣ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ሕዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply