You are currently viewing የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ አማራዎች ላይ አሁንም የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈጸም የሚገፋፋ አደገኛ የጥላቻ መልዕክት አስተላልፏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ አማራዎች ላይ አሁንም የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈጸም የሚገፋፋ አደገኛ የጥላቻ መልዕክት አስተላልፏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ አማራዎች ላይ አሁንም የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈጸም የሚገፋፋ አደገኛ የጥላቻ መልዕክት አስተላልፏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ነሃሴ 30/2014 ባወጣው መግለጫ አሁን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጥቃት እያደረሰ ያለው ፋኖ ነው በማለት ዛሬም እንደለመደው በውሸት የአማራ ፋኖን ስም አጥፍቷል። ፋኖ ሲል የጠራቸው አካላትንም አስቀድመው በሰፈራ መልክ ኦሮሚያ ውስጥ የነበሩትን ከለላ በማድረግ ከአማራ ክልል ስለመምጣቱ በመግለጽ የተለመደ እና የኖረበትን የማለያዬት፣ የነባር እና መጤ የረከሰ ፖለቲካውን አሰራጭቷል። በኦሮሚያ በሚኖሩ አማራዎች ላይ ጄኖሳይድ እያወጀ ያለው ኦነግ “በሰፈራ መልክ ኦሮሚያ ውስጥ በነበሩ ዜጎችና በመንግሥት ፀጥታ መዋቅር የሚደገፈው ቡድን” ሰሞኑን በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አጋምሳ ከተማ እና ሆሮ ቡሉቅ ወረዳን በመውረር ጥቃት ፈጽሟል ሲል በሀሰት ወንጅሏል። ሲቪል የለበሱ የፌደራል ሃይሎችም አብረው እንደነበሩ በመጠቆም በግድያዎች ውስጥ የመንግሥት ሃይሎች እጅ ሊኖር እንደሚችል ጥርጣሬ እንዳለውም ገልጿል። በብዙ ሚሊዬን የሚቆጠር አማራ ለዘመናት ከሚኖርበት ቀዬው ልጆቹን በአሰቃቂ መልኩ በመጨፍጨፍ በየቀኑ በሚባል ሁኔታ እየተፈናቀለ መሆኑ እየታወቀ ኦነግ ከዚህ በተቃራኒው የኦሮሞን ህዝብ ከመሬቱ ለማፈናቀል የተቀናጀ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ይላል። ሰኔ 11/2014 በአንድ ቀን በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ላይ 1,500 እንዲሁም በቄለም ወለጋ ነሃሴ 27/2014 በአንድ ቀን ከ300 በላይ አማራዎች በኦነግ፣ በመንግስታዊ መዋቅሩ እና በብዙ የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፎ ጭምር መጨፍጨፋቸውን የዘነጋው ቡድኑ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጭፍጨፋ ሲፈፀመ መንግሥት በዝምታ እንዳለፈው አድርጎ ገልጧል። የአያሌ አማራዎችን ደም ያፈሰሰው ይህ የኦነግ ድርጅት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ከኢትዮጵያ ምስረታ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ጭፍጨፋ እንደሚፈጸምበት በመግለጽ በአንድነት ተነስቶ ራሱን እንዲከላከል በመግለጫው ቀስቅሷል። ቡድኑ በኪረሞ ስኒ ዶሮ በአንድ ቀን ከ300 ስለተጨፈጨፈው አማራ፣ የጃዋር መሀመድን ተከብቤያለው ጩኽት ተከትሎ ስለተጨፈጨፉት ከ96 በላይ ንጹሃን፣ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን መገደልን ተከትሎ በተደረገ የአደባባይ ቅስቀሳ የተጨፈጨፉ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች፣በጉሊሶ በአንድ ቀን ተገደው ስብሰባ እንዲወጡ ተደርገው በግፍ በቡድን መሳሪያ ጭምር እንዲጨፈጨፉ ስለተደረጉት ከ250 በላይ አማራዎች፣ በባቦ ገምቤል ስለተጨፈጨፉት ከ200 በላይ አማራዎች እና በሌሎች ኦሮሚያ አካባቢዎች በየቀኑ በዘረኝነት ባሳበዳቸው የእሳቤ ድኩማኖች ስለሚያልቀው አማራ የሰማ አይመስልም። አማራዎች በገፍ እና በግፍ በጅምላ ሲጨፈጨፉ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ምላሽ ሲሰጡ የተገደለ ኦነግ ሸኔ ካለ ንጹሃን እንደሞተ ተደርጎ ማቅረብ የተለመደ ነው። “ሲገድሉ ኦነግ ሸኔ፣ ሲሞቱ ንጹሃን” የሚል ሽፋን እየተሰጣቸው በተለይ ላለፉት አራት ዓመታት በአደባባይ ጭምር የዘር ፍጅት እየተፈጸመበት ባለው ኦሮሚያ ክልል አሁንም ደም እንዲፈስ ኃላፊነት የጎደለው የጥላቻ ቅስቀሳው ቀጥሏል። አጋምሳ ላይ ነሃሴ 22/2014 ምሽት ላይ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ህዝቡን ለኦነግ ሸኔ ያለ ተኩስ ጥሎ መውጣቱን ተከትሎ ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ የገባው የሽብር ቡድኑ ከ43 በላይ አማራዎችን አግቶ እስከ ነሃሴ 24/2014 በአሰቃቂ መልኩ እየቆራረጠ መግደሉንና ሶስት ባንኮችን መዝረፉ እየታወቀ የታገቱ ቤተሰቦቻቸውን ለማስለቀቅ በሄዱ በታጋች ቤተሰቦችና በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ መካከል የተደረገውን የተኩስ ልውውጥ ከአማራ ክልል የመጣ ፋኖ በማለት እንዲሁም ከአንድ ወገን ብቻ የሞተ በማስመሰል የተጋነነ የሟች ቁጥር በመጥራት ኦነግ መግለጹ አማራው እንዲጨፈጨፍ መልዕክት እያስተላለፈ መሆኑ ታውቆ ህዝቡ የራሱን ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል። የሚመለከተው የመንግስት አካል፣ የሚዲያ ተቋማትና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በኦሮሚያ ክልል ላለው የአማራ ህዝብ ድምጽ ሊሆኑትና ሊታደጉት ይገባል። OMN በተባለ ልሳኑ በኩል ካስተላለፈው መልዕክት የምንረዳው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በኦሮሚያ ክልል ባሉ አማራዎች ላይ የዘር ፍጅት እንዲፈጸም የተነሱ ቅስቀሳ ማድረጉን ነው። ብዙውን ጊዜ በክልሉ በአማራ ላይ የዘር ፍጅት ከመፈጸሙ ቀደም ብሎ የተለያዩ የመገናኛ አውታሮችን በመጠቀም የተለመደ ዓይነት የሀሰት ክስ እና ቅስቀሳ በጽንፈኛ ግለሰቦችና ድርጅቶች እንደሚደረግ ይታወቃል። ከተደራጀ እና ተከታታይ ቅስቀሳ በኋላም የዘር ፍጅቱን የሚፈጽሙ የተደራጁ አካላት ወደተለመደ ዘር ተኮር የጭፍጨፋ ተግባራቸው እንደሚገቡም የመጣንበት መንገድ በግልጽ ያሳያል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply