#የኦነጋዊያን የፍርሃት ጉዞ የአማራ ወጣት እና ፋኖ አዲስ ትግል መጀመር አለበት! ~~~ሻለቃ አንተነህ ድረስ የምንይልክ ብርጌድ መሪ~~~ ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ እንደሚታ…

#የኦነጋዊያን የፍርሃት ጉዞ የአማራ ወጣት እና ፋኖ አዲስ ትግል መጀመር አለበት! ~~~ሻለቃ አንተነህ ድረስ የምንይልክ ብርጌድ መሪ~~~ ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ እንደሚታወቀው ኦነግ በ1960ዎቹ ከተመሰረቱት ነፃ አውጭዎች መካከል አንዱ ነው። በዋናነት በጀርመኖችና በግብፆች እየተደገፈ ለበርካታ ዓመታት ለኦሮሞ ህዝብ እታገላለሁ በማለት በጎረቤት አገር ሳይቀር ተንቀሳቅሷል። የድርጅቱ መሰረታዊ ሐሳብ ውሸትን እውነት በማስመሰል ትርክት ፈጥሮ ለአባላቶቹ ማስተማር ነው። የትርክቱ መሰረቶች ደግሞ ኢትዮጵያ የምትባለዋን አገር ለማፍረስ የታለመ ነው። በተለይ አማራውን ነፍጠኛ፣ ጨቋኝ፣ የድሮ ስርዓት… በማለት ከፍተኛ የሆነ ጥላቻን ለዓመታት አስተምሯል። ኦነግ በ1983 ዓ.ም ከኢህአዴግ ጋር በመሆን ወደ ስልጣን ለመምጣት የተስማማ ቢሆንም ሊቀጥልበት አልቻለም። በዚህ ድርጅት አስፈፃሚነት ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ በአሰቦት ገዳም ፣ በሐረርና በወለጋ በአማራዎች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ተደርጓል። ከኢህአዴግ ጋር የነበረውን አብሮ የመስራት እድል ካበላሸ በኋላ በአብዛኛው ከአገር ውጭ በመውጣት ጫፍ የረገጠ የብሄረተኝነት እንቅስቃሴያቸውን ቀጥለውበታል። ድርጅቱ ገና ከጅምሩ የኢትዮጵያ፣ የአፄ ምንሊክና የአማራ ፍራቻ( Phobia) ከደሙ ጋር የተዋሐደበት በመሆኑ የአፄ ምንሊክን ሐውልት ለማፍረስ የሚታዘዝ መንጋን በተጨባጭ መፍጠር ችሏል። ሌላው ፍራቻው አማራ የሚባል ህዝብ ሲሆን በተገኘው አጋጣሚ እርጉዝ ሴቶችን ሳይቀር በስለት እየወጋ ይገላቸዋል። ይህ ድርጅት ከ2010 ዓ.ም ወዲህ ሁለት ዋና ዋና ቅጥያዎችን ፈጥሯል። የመጀመሪያው ቅጥያ የኦሮሚያ ብልፅግና በመባል የሚጠራ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ኦነግ-ሸኔ በመባል ይጠራል። የኦሮሚያ ብልፅግና ምንም እንኳን የመንግስትነት ስልጣን ቢቆጣጠርም የክልል መንግስት ለመባል የሚያስችሉ ስራዎችን ከመስራት ይልቅ የአባቱን የኦነግ ዓላማዎችን ማስቀጠሉን እንደ ዋና አጀንዳ አድርጎ እያስፈፀመው ይገኛል። ሌላው ቅጥያ ደግሞ ሸኔ በመባል የሚጠራው ሲሆን የተፈቀደለት አሸባሪ በመባል ሊጠራ የሚችል ነው። በኦሮሚያ ብልፅግና የሚመራው ኃይል በመሰረታዊነት ከተወለደበት ድርጅት የተለየ ነገር ባይኖረውም ሁለት ፍራቻዎችን አጠናክሮ እንደቀጠለና አንድ ዋና አጀንዳን ለማከናወን እንዳለመ ማሳያዎቹ ብዙ ናቸው። ዋና አጀንዳቸውም ሁሉም ሰው እንደሚረዳው አዲስ አበባ ከተማን የመሰልቀጥ እንቅስቃሴ ሲሆን የዳሃ ዜጎችን ቤት በማፍረስ በተግባር እያሳዩን ይገኛሉ። ሌሎቹ ሁለቱ ፍራቶች ደግሞ የአማራ ልዩ ኃይል እና ፋኖ ናቸው። የአማራው መደራጀትና አንድ መሆን እንቅልፍ የሚነሳቸው ከመሆኑም ባሻገር ተቋም እና መሪ እንዳይኖረው ደግሞ አብዝተው ከሚሰሩባቸው ጉዳዮች መካከል ናቸው። የአማራ ልዩ ኃይል ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለአገሩ አጥንትና ደሙን እየሰጠ የሚገኝ እንጅ በስጋት የሚታይ አልነበረም። የአማራ ልዩ ኃይል መስዋዕትነት ለእናንተም በስልጣን መቆየት እገዛ እንዳደረገ፤ በዳንሻ፣ በሁመራ፣ በወሎ፣ በጭና እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች የነበረውን ማስታወስ ይቻላል። ሌላው በአማራ ፋኖ ላይ የምታራምዱት የእስር፣ የፍረጃና የፕሮፓጋንዳ ስራ ነው። የአማራ ፋኖ ንፁሃንን እንዳልገደለና ባንክ እንዳልዘረፈ የሚታወቅ ሐቅ ቢሆንም ገዳዩን ደብቃቹህ ለአገሩ የሚሞተውን የምታሳድዱበት ምክንያት ምን እንደሆነ ሊገባን አልቻለም? የአማራ ልዩ ኃይል በካምፕ እንደተቀመጠ በከባድ መሳሪያ የሚመታበት ምክንያትም አልገባንም? ከተማ በዲሽቃ ሳይቀር የሚወድምበት ምክንያትም እንደዚሁ? እነዚህን ጥያቄዎች ለጊዜው ልተዋቸውና ወደ መፍትሔው ልሂድ: የአለም ታሪክ እንደሚያስረዳን አንድ ብሄር ተነጥሎ የሚገደል ከሆነ አማራጩ ሁለት ነው። መጥፋት ወይም ታግሎ ነፃ መውጣት። 1. ጠላቶቻችን ሊያጠፏቸው ሌት ከቀን የሚሠሩባቸው ተቋማት ላይ ትኩረት በማድረግ እንዲጠነክሩና አቅም እንዲፈጥሩ ማድረግ ነው። በተለይ የአማራ ክልል መሪዎች ያለፈውን በመተው የክልሉን ህዝብ አንድ የማድረግ እና የፀጥታ ተቋሙን የማጠናከር ስራው ለነገ የሚባል እንዳልሆነ መረዳት ያስፈልጋል። በእኔ እምነት በዚህ አካሄዱ አሁን በስልጣን ላይ ያለው ኃይል ከጊዜ በኋላ አጋር የሚላቸውን ድርጅቶች መብላት እንደሚጀምር መረጃዎችን ማንሳት ይቻላል። 2. የአማራ ወጣትና ፋኖ አዲስ የትግል እንቅስቃሴ መጀመር እንደሚጠበቅበት ማንም ሊነግረው አይገባም። አዲስ የትግል እንቅስቃሴ ሲባል የተገደበ የሚመስልን ወይም ለመሞት ብቻ መታገል የሚባልን አሮጌ ነገር በመተው ወደ ግብ ያዘነበለ አካሄድና እንደ ማህበረሰብ ንቅናቄ ሊፈጥር የሚችል መንገድን ተመራጭ ማድረግ የመዳኛ መንገዱ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል። የኦነጋዊያን የፍርሃት ጉዞ ይብቃ! ፋኖ አንተነህ ድረስ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የምንሊክ ብርጌድ መሪ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply