የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በቄለም ወለጋ ዞን ሰዲ ጫንቃ ወረዳ እገታ፣በዳሌወበራና በጋዋ ቄቤ ወረዳዎች ደግሞ በባንክ ላይ ዝርፊያ መፈፀማቸውን የአይን እማኞች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በቄለም ወለጋ ዞን ሰዲ ጫንቃ ወረዳ እገታ፣በዳሌወበራና በጋዋ ቄቤ ወረዳዎች ደግሞ በባንክ ላይ ዝርፊያ መፈፀማቸውን የአይን እማኞች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በቄለም ወለጋ ዞን ሰዲ ጫንቃ ወረዳ እገታ፣በዳሌወበራና በጋዋ ቄቤ ወረዳዎች ደግሞ በባንክ ላይ ዝርፊያ መፈፀማቸውን የአይን እማኞች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን በሰዲ ጫንቃ ወረዳ መንደር 11 ቀበሌ ልዩ ስሙ 12 በሚባል አካባቢ ሀሙስ ሌሊት ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 1ሰዓት ተኩል ላይ 32 የሚሆኑ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የእንሰሳት ሀኪም የሆነውን ዶ/ር ኤሊያስ ተስፋዬን፣ ጠጁ ደረሰ እና መኮንን ደረሰ የተባሉ ወንድማማቾችን የፊጥኝ አስረው አግተው ወስደዋል። የዶ/ር ኤሊያስ ተስፋዬን መኖሪያ ቤቱን እና ሱቅን ዘርፈዋል፣በሱቁ ውስጥ 460 ሽህ ብር የሚገመት አዳዲስ እቃ ከ3 ቀናት በፊት በአይሱዙ ተጭኖ መግባቱም ያወቁት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የሚፈልጉትን ሁሉ ከዘረፉ በኋላ ቤንዚን አርከፍክፈው ማቃጠላቸው ነው የተገለፀው። እድሜያቸው እስከ 35 ባለው የሆኑት ወንድማማቾች ጠጁ ደረሰ እና መኮንን ደረሰም ታግተው ተወስደዋል ነው ያሉት በዋሪዎቹ። የአቶ ጠጁን ሱቅም ያለማንም ሀይ ባይ ዘርፈው ካቃጠሉ በኋላ ነው ሁሉንም የፊጥኝ አስረው ጥይት ወደ ላይ በመተኮስ ከአካባቢው የሸሹት ተብሏል። በወቅቱም ከመስጊድ የሚወጣና የሚገባውን “ዞራቹህ አትዩ፣ ተደፉ”በማለት ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመዋል ነው ያሉት። “አንድም የፀጥታ አካል አልደረሰም፣የክልሉ ልዩ ሀይሎችም ከኦነግ ሸኔ ጥቃት ሊከላከሉን አልቻሉም፣ዋስትና የለንም” ያሉት ነዋሪዎቹ ጅብ ካለፈ ውሻ ጮኸ እንዲሉ አሁን ላይ ግን የወረዳው አስተዳደር ከኦሮሚያ የልዩ ሀይል አባላት ጋር በመሆን ፍለጋ ላይ ናቸው ብለዋል። በተመሳሳይ ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ በቄለም ወለጋ ዞን ዳሌወበራ ወረዳ በቃጤ ከተማ ከ54 በላይ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል አባላት ባለበት 17 የሚሆኑ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ገብተው የባንክ ማናጀሩንና ዘበኛውን ከገደሉ በኋላ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍን ዘርፈዋል፤ በግርግሩም የቆሰለ ሰላማዊ ሰው ስለመኖሩ ተጠቁሟል። በወቅቱ የአካባቢው የልዩ ሀይሉ ኃላፊ ወደ ጫንቃ ከተማ አባላትን ለምሳ ግብዣ ይዞ ሄዶ እንደነበር የገለፁት ነዋሪዎቹ ነገሩ ሆንተብሎ የተደረገ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ አላቸው። በተመሳሳይ በጋዋ ቄቤ ወረዳ በቄቤ ከተማ ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት 1 ሰዓት አካባቢ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ዝርፊያ መፈፀሙንም ነዋሪዎች አውስተዋል። የኦሮሚያ ክልል የልዩ ሀይል አባላት እና የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች አይነካኩም ያሉት ነዋሪዎቹ መንግስት መከላከያ ሰራዊት እንዲመድብላቸው ጠይቀዋል። መከላከያ መውጣቱን ተከትሎ እንደአብነትም ከቡጊ ወረዳ ደምቢ ዶሎ አካባቢ በርካታ አማራዎች ስጋት ስላደረባቸው ወደ ጋምቤላና መቻራ ሲለቁ ታይተዋልም ብለዋል። ከአካባቢው የመስተዳድር አካላት ለማጣራት ያደረግነው ጥረት ከኔትወርክ ችግር ጋር በተያያዘ ጥረታችን ለጊዜው አልተሳካም። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማናጀር ለሆኑት ለአቶ ደበበ ደውለን ለማጣራት ጥረት ብናደርግም እሳቸውም “የደረሰኝ መረጃ የለም፤ የማውቀው ነገር የለኝም”የሚል ምላሽ ነው የሰጡን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply