የኦነግ ሸኔ ኃይሎች በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ጥቃት መክፈታቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ መነሻቸውን በአማራ ክልል…

የኦነግ ሸኔ ኃይሎች በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ጥቃት መክፈታቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ መነሻቸውን በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ያደረጉ የኦነግ ሸኔ ኃይሎች በሰሜን ሸዋ ዞን አንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ልዩ ስሙ ሀገረማርያም ሟጨራ በተባለ ቀበሌ ላይ ጥቃት መክፈታቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ ጥር 17/2015 ዓ/ም ለአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ አዋሳኝ በሆነው ማጀቴ አካባቢ እና ጨፋ ሮቢት ከተማ ላይ በቡድን መሳሪያ ጭምር የታገዘ ተኩስ ከፍተው መዋላቸውን የአማራ ድምፅ መዘገቡ አይዘነጋም። ጥር 18/2015 ዓ/ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ገደማ ጀምሮ በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ሀገረማርያም ሟጨራ ቀበሌ ስር በሚገኙ ከስምንት በላይ የሚሆኑ መንደሮች ላይ ታጣቂዎቹ ተኩስ መክፈታቸውን ነው የቀበሌው ሊቀመንበር አቶ ግርማ ለአማራ ድምፅ ያረጋገጡት። እስከ አሁን የደረሰላቸው የመከላከያ ሰራዊትም ይሁን የክልሉ ፀጥታ ኃይል አለመኖሩን የገለፁት ሊቀመንበሩ የቀበሌዋ ነዋሪዎች አከባቢያቸውን ለቀው ላለመውጣት እልህ አስጨራሽ ትግል እያደረጉ እንደሚገኙ አመላክተዋል። ሌሎች የአማራ ድምፅ ያየነጋገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች፡ ወራሪ ቡድኑ ብዛት ያለው ኃይል ከማሰለፉ በተጨማሪ ላውንቸር እና ድሽቃን የመሳሰሉ የቡድን መሳሪያዎችን ጭምር በመጠቀም ጥቃቱን እየሰነዘረ እንደሚገኝ ገልፀው፡ ታጣቂዎቹን ተከትሎ የሚመጣ ዘራፊ ቡድን መኖሩንም ጠቁመዋል። ጥቃቱን በመከላከል ላይ የነበሩ ሰዎች መቁሰላቸውን እና ህክምና አለማገኘታቸውን የተናገሩት ነዋሪዎቹ የክልሉ መንግስት የፀጥታ ኃይል በአስቸኳይ ወደ አከባቢው እንዲያሰማራ ጥሪ አቅርበዋል። ዘገባው የአማራ ድምፅ ሚዲያ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply