የኦነግ ሸኔ አባላት በምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች የሞከረው የገንዘብ ዘረፋ ከሸፈ።በምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ አካባቢ ትናንት ምሽት የባንክ ገንዘብ በእንቅስቃሴ ላይ በነበረበት ወቅት…

የኦነግ ሸኔ አባላት በምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች የሞከረው የገንዘብ ዘረፋ ከሸፈ።

በምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ አካባቢ ትናንት ምሽት የባንክ ገንዘብ በእንቅስቃሴ ላይ በነበረበት ወቅት የኦነግ ሸኔ አባላት ለመዝረፍ ያደረጉትን ሙከራን በፀጥታ ሀይሎች መክሸፉ ተነገረ፡፡

የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ታዬ ደንደአ ፣ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ የባንክ ገንዘብ በእንቅስቃሴ ላይ በነበረበት ወቅት የኦነግ ሸኔ አባላት ለመዝረፍ ያደረጉትን ሙከራን በክልሉ የፀጥታ ሀይሎች መክሸፉ ተናግረዋል፡፡

ዘረፋ ለመፈፀም ሙከራ ያካሄዱት የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ የቆሰለ እና በቁጥጥር ስር የዋሉ መኖራቸውም ተናግረዋል፡፡

ከኦነግ ሸኔ የዘረፍ ቡድን አባላት ያመለጡም መኖራቸውን እና በጥብቅ ክትትል በፀጥታ ሐይሎች እየታደኑ እንደሚገኝም አቶ ታዬ ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ክልሉ በሁሉም አቅጣጫዎች በልዩ ጥበቃ ላይ መሆኑንም ሀላፊው ተናግረዋል፡፡

ልዩ ጥበቃውም ከሚሊሻ ፣ ከህዝቡ ፣ ከፖሊስ እና ከልዩ ሐይሉ ጋር በመጣመር የጥፍት ሀይሎች ሴራን ለማክሸፍ እየሰራ ነው ተብሏል፡፡

ዳንኤል መላኩ ፡፡
ሕዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply