የኦነግ የገንፎ ተራሮችና የሆራ ጨለቅላቃ የወተት ሐይቅ!!! የኦሮሞ ህዝብ በኦነግ ስብዓዊ ጋሻነት ታግቷል!!! (ክፍል ሁለት) ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

ሻብያ፣ ወያኔና ኦነግ አንድም ሁለትም ሦስትም  ናቸው!!! የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና የአማራ  ዘር ማፅዳት  (ጆኖሳይድ) ይቁም!!! ወያኔና ኦነግ በሽብርተኛነት ይፈረጁ!!! ከ…አቧይ ወደ ኦቦ!!!

የኦሮሞ ህዝብ በኦነግ ስብዓዊ ጋሻነት (Human shield) ተይዞል፣ የኦህዴድ የኦሮሞ ክልል የጦር አበጋዞች መንግሥትና የፌዴራል መንግሥት ሽብር ህፃናት ይታረዳሉ፣ ሴቶች ይደፈራሉ፣  አሮጊትና ሽማግሌዎች ይሰደዳሉ፣ ኦነግ ኦህዴድ ሹማምንት  በኢትዮጵያ የዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጆኖሳይድ) በመፈጸም የታሪክ አተላ ሚና ተጫውተዋል፣  ‹‹ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል!››

በኦሮሞ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዜዳንት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ አማራን ‹‹በማሳመን ወይም በማደናገር›› የፖለቲካ ዘመቻ ከፈቱ፡፡ በኦሮሚያ ክልል የሚመራ መንግሥት መር ሽብርተኛነት፣ በመንግሥታዊ መዋቅሮቹ በመጠቀም፣ በመከላከያ ሠራዊቱ፣ ፖሊስ ኃይሉ፣ በጸጥታና ደህንነት ድርጅቱ በጋራ የተቀነባበረ የሽብርተኛነት ድርጊት  የተፈፀመ የዘርና የኃይማኖት ማጥፋትን ያሳያል፡፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና የፌዴራል መንግሥት ስውር  እጅ ለአለፈው ሦስት ዓመታት ተስተውሎል፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ ህዝብ የሰጣቸውን ቃል በልተዋል፡፡ አሁን ህዝቡ  ‹‹ጊዜ እስኪያልፍ ያባትህ ባርያ ይግዛኝ!!!›› እያለ የአበውን ተረት ይተርትላቸዋል፡፡

 • ህወሓት ከ1967 አስከ 2013ዓ/ም በወልቃይት ጠገዴ ወዘተ ህዝብ ላይ የፈጸመው አማራን የማጥፋት የዘር ፍጅት ታሪክ ከ ‹‹welkaite.com›› “TPLF’s genocide on Amhara Welkait, Maikadera Nov 10 2020” ይመልከቱ፡፡ ህወሓት በወልቃይት ማይካድራ በአማራ ላይ የፈፀመው የዘር ፍጅት፣ የወያኔ የፍፃሜው ጦርነት አልቆል፡፡ የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር ሽብር ቀጥሎል፡፡ የኦነግ ግብዓተ መሬት በኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ድል አድራጊነት በአጭር ጊዜ ይፈፀማል፡፡
 • በ1982 ዓ/ም ጥር ወር መግቢያ ላይ፣ በኮነሬል መንግስቱ ኃይለማርያም ወታደራዊ አገዛዝ ዘመን፣ በወለጋ ክፍለ ሃገር በአሶሳ ከተማ ህወሓትና ኦነግና የተሳተፉበት ክርስቲያኖችንና አማራዎች የሚሏቸውን ለይተው ቤት ዘግተው በእሳት ማቃጠላቸው የሕዝቡ መፃዒ ዕድል ምን ሊሆን እንደሚችል አመላካች አሰቃቂ ተግባር ነበር። በወያኔና በኦነግ የተፈፀመ የዘር ጭፍጨፋ ነበር፡፡ ወያኔ መሪ መለስ ዜናዊ፣ ሻብያው ኢሳያስ አፈወርቂና ኦነግ ሌንጮ ለታ በጆኖሳይዱ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡
 • በ1983ዓ/ም አራጆቹ ወያኔው መለስ ዜናዊ፣ የሻብያ ኢሳያስ አፈወርቂና የኦነግ ሌንጮ ለታ በአሜሪካው ህእር ማን ኮን አንጋሽነት ሥልጣን ተቆጣጠሩ፣ በመለስና ኢሳያስ የበድሜ ጦርነት መቶ ሽህ ወታደሮች ህይወታቸው ተቀጠፈ፡፡ በ1983 ዓ/ም በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት ኢህአዴግ በህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴን እና ደኢህዴን ተመሠረተ፡፡ ዋናዎቹ ወያኔና ኦነግ ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ ጅኦ-ፖለቲካ ካርታ ተነድፎ ተቀየረ፡፡ ትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ሃረሪ፣ ደቡብ ክልል የሚል ዘጠኝ ክልላዊ መንግሥቶች ተመሠረቱ፡፡ አዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተባሉ፡፡
 • በ1984/85 ዓ/ም በአርሲ ሃገረ-ስብከት አርባጉጉ አውራጃ በ680 ካህናትና ኦርቶዶክሳዊያን በአሰቃቂ አረመኔዊ ተግባር ታርደዋል፣ ተቃጥለዋል ከገደል ላይ ተወርውረዋል፡፡ቤተክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፣ ቅርሶች ተዘርፈዋል፣ አርባ ሦስት ሽህ ምዕመናን ተሰደዋል፡፡ በተመሳሳይ በ1984ዓ/ም በበደኖ፣ ጋራሙለታ፣ ጨለንቆና እንቁፍቱ ገደል ከ300 በላይ አማሮች ላይ የዘር ፍጅት አድርገዋል፡፡ የዘር ፍጅቱ ዋና ተዋናዬች ኦነግ ኦህዴድና ወያኔ ሠራዊት የመሩ ኮነሬል ኪዱና ኮነሬል ጥላሁን ነበሩ፡፡ አረንጎዴ መብራት አብርተው በማሳለፍ ብአዴን ታምራት ላይኔና ሰለሞን ኃይሉ ዋናዎቹ ነበሩ፡፡ ፊልሙን በዩቲዩብ ድር ገጽ ተመልቱ፡- “ESAT human right eyewitness testimony the massacre of Bedeno 1992 Ethiopia https://www.youtube.com/watch?v=E6uEc9wiZBs
 • በ1990ዓ/ም በደቡብ ክልል በጉራፈርዳ በደኢህዴን መሪ ሽፈራው ሽጉጤ መሪነት በአማራዎች ላይ የዘር ፍጅት ተደርጎል በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ሰዎች ከቀያቸው ተሰደዱ፡፡ መለስ ዜናዊ ድርጊቱን ‹‹የጎጃም ሞፈር ዘመት ገበሬዎች ደኑን በመጨፍጨፋቸው የተነሳ ግጭት›› አድርጎ ገልፆት ነበር፡፡
 • በ1990ዎቹ አይኤፍኤልኦ የጃራ አባገዳ የኦሮሞ እስልምና ግንባር በሐረር፣ በባሌና አርሲ አማራን ጨፍጭፎል፡፡ በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል በወለጋ የኦህዴድ የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ዩናታን ዲቢሶ በወለጋ አማሮችን በመግደልና አስር ሽህ አማራዎች ንብረታቸው ተቃጥሎ እንዲሠደዱ አስደርጎል፡
 • በምዕራብ ሐረርጌ ሃገረስብከት አሰቦት ገዳምና አቡነ ሣሙኤል ገዳም መነኮሳትና ምዕመናን በግፍ ታርደዋል፣ አብያተ ክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፡፡
 • በ1994 ዓ/ም የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዜዳንት ኦቦ አባዱላ ገመዳ በኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ አማሮች ምንም ውክልና አገልግሎት እንዳያገኙ በማድረግ አማሮች ተማረው ከኦሮሚያ ለቀው እንዲወጡ በማድረግ ስልት አማራ፣ ጉራጌዎች ወዘተ በናዝሬት ከተማ ግንብ ተራ ጉራጌዎች ሱቆችን  በማፍረስና ነጋዴዎች በመግደል አስለቅቀው ለኦሮሞ ነጋዴዎች ሠጡ፡፡ አማራን ከኦሮሚያ ማስወጣት ስልት በአባዱላ ገመዳ ተጀመረ፡፡
 • 1998 ዓ/ም በህዳር 8 እና 9 ቀን፣ በአርሲ ሃገረስብከት ኮፈሌ ቆሬ ከተማ አይሻ ሰበካ ስድስት ምዕመናን ተገለዋል፡፡ ከመቶ በላይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ተከታዬች ቤታቸው ተቃጥሎ ተሰደዋል፡፡ የማርያም ቤተከርስቲያን ተቃጥላለች፡፡
 • 1999 ዓ/ም ከመስከረም እስከ ጥቅምት አምስት፣ በሻሻ ዴዴሳና በሞናቶ  አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ተቃጥሎል፡፡ካህናትና ምዕመናን ታርደዋል፣ የምዕመናን መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡
 • በ2003 እኤአ በጋምቤላ ክልል አራት መቶ የአኝዋ ዜጎችን በዘር ማፅዳት ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል፡፡ በአኝዋክ የዘር ፍጅት ዋናዎቹ ተዋናዬች ሜጀር ፀጋዬ በየነ፣ አባይ ፀሐዬ እና ዶክተር ገብረአብ በርናባስ ይገኙበታል፡፡
 • በ2007 እኤአ በሱማሌ ክልል በኡጋዴን፣ ፊቅ፣ ደጋሃቡር፣ ቆሬ፣ ጎዴ፣ ዋርዴር በሱማሌ ዜጎች የዘር ማጥዳት ወንጀል በአብዲ ኢሌና በህወሓት የጦር አበጋዞች ተፈፅሞል፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=EcZJIfUKx9M
 • በ2010ዓ/ም መጋቢት ወር ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኑ፡፡ የኦነግ መሪዎች አዲስ አበባ ገቡ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አደስ ህግ ፀድቆለት ታከለ ኡማ፣ አዳነች አቤቤ፣ ወዘተ በማድረግ ‹‹ፊንፊኔ ኬኛ›› አማራን ከኦሮሚያ ክልል ብቻ ሳይሆን ከአዲስ አበባ ለማስወጣት ትልቅ የፖለቲካ ሴራ ተጀመረ፡ ከነትጥቁ የገባው ኦነግ ሸኔ በወለጋ ውስጥ ወጣቶች በወታደርነት በመመልመል ከፌዴራል መንግስቱ ቁጥጥር ስር ውጪ እንደሆነ በማውራት አማራን ዘር የማፅዳት ዘመቻ ጀመሩ፡፡  የኦሮሞ ክልል ፕሬዜዳንቶች ኦቦ ለማ መገርሳ፣ ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ አንደኛ አማራን ለማዳከም አማርኛ ቌንቌ የማዳከም ዘመቻ ጀመሩ፡፡ ሁለተኛ አማራን ትጥቅ ማስፈታት በግሉ የገዛውን መሣሪያ ጭምር ትጥቅ ማስፈታት በፌዴራልና በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ተደረገ፡፡ ሦስተኛ በኦሮሚያ ክልል አማራ በመሃበር እንዳይደራጅ ከለከሉ፡፡  
 • በ2011 ዓ/ም የጁዋር መሃመድ የተከብቢለሁ ጥሪ የ123 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ቢያንስ በ500 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል። በኦሮሚያ ክልል ከአንድ ሺህ በላይ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ላይ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱ ተነገረ። በመኖሪያእና በንግድ ቤቶች ላይ የደረሰ ጉዳት፤በአሮሚያ ክልል፤ 523 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። 499 (አራት መቶ ዘጠና ዘጠኝ) መኖሪያ ቤቶች ፈርሰዋል፡፡  195 (መቶ ዘጠና አምስት) ሆቴሎች መቃጠላቸውን እና ሌሎች 32 (ሠላሳ ሁለት) ሆቴሎች ደግሞ በንብረት ላይ የመሰባበር ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም 104 (መቶ አራት) የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቃጠሎ ውድመት እንደደረሰባቸው አመልክተዋል። ስድስት አነስተኛ እና ግዙፍ ፋብሪካዎች በሁከቱ መቃጠላቸውን፣  የተቃጠሉ አነስተኛ ንግድ ቤቶች ቁጥር ድግሞ 232 (ሁለት መቶ ሠላሳ ሁለት) እንዲሁም የተሰባበሩት አስተኛ ንግድ ቤቶች አሃዝ 219 (ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ) መሆኑ ታውቆል፡፡ 232 (ሁለትመቶ ሠላሳ ሁለት) የግል እንዲሁም 12 የመንግሥት ተሸከርካሪዎች በእሳት እንዲጋዩ ተደርገዋል። በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰው በምዕራብ አርሲ ሦስት ወራዳዎች  በተለይ በሻሸመኔ እና ባቱ ከተሞች እንዲሁም በባሌ ዞን ሮቤ እና አጋርፋ ከተሞች ገዳት ደርሶል።
 • በ2013 ዓ/ም በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች ውስጥ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ታውቆል፡፡ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን፣ 67 ሰዎች መሞታቸውን፣ 114 መቁሰላቸውን እና በወረዳው ስምንት ቀበሌዎች 815 ቤቶች መቃጠላቸውን ለማወቅ ተችሎል፡፡ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪውአቶ ታደሰ በበኩላቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ደብረብርሃን፣ አጣዬ፣ ኤፍራታ፣ ሸዋ ሮቢት ገንደ ውሃ፣ መሀል ሜዳ እና የተለያዩ ቦታዎች እንደሚገኙ ተናግረዋል።
 • በማክሰኞ መጋቢት 21/2013 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ ዓ.ም በዞኑ ውስጥ በሚገኘው በቦኔ ቀበሌ ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ላይ “አሰቃቂና ዘግናኝ” መፈፀሙን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስታውቋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የተገደሉት ሰዎች 28 መሆናቸውንና ጉዳት የደረሰባቸው 12 መሆኑን ገልጿል። የቦኔ ቀበሌ ነዋሪዎች ከእነዚህም በተጨማሪ በአካባቢው ከብቶቻቸውን በመያዝ ለግጦሽ በአቅራብያ ወደ ሚገኝ ቀበሌ ይዘው ሄደው የነበሩ 15 ታዳጊዎችም በታጣቂዎች መገደላቸውን ገልፀዋል።  ታጣቂዎቹ ግለሰቦቹን ከየቤቱ በማውጣት አንድ ቦታ በመሰብሰብ በጥይት መግደላቸውን ገልጸዋል።  በተመሳሳይ በምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ በሚገኝ ሌላ ስፍራ ላይ ታጣቂዎች ነዋሪውን በአንድ ቦታ ላይ በመሰብሰብ በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ሰዎችን መገደላቸው ይታወሳል።
 • በጥቅምት 24ቀን 2013ዓ/ም በተጀመረው የትግራይ ጦርነት ወቅት የተፈጸመ የዘር ፍጅት በማይ ካድራና በአክሱም  ወዘተ በገለልተኛ ዓለም አቀፍ አጣሪ ኮሚሲዮን ተመርምሮ እንዲጣራ እንጠይቃለን፡፡ ለትግራይ ህዝብ የረድኤት እህል፣ ህክምና ለህይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች እንዲቀርቡለት እንጠይቃለን፡፡

‹‹ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም!!!››  ኢህአዴግ በብልጽግና ቢለወጥ አስተዳደራቸው መንግሥታዊ ሽብር ነው፡፡

 • የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተቃጠለባቸው፣ ካህናትና ምዕመናን የተገደሉባቸው ስፍራዎች ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ አጣዬ ወዘተ በናሙናነት ይጠቀሳሉ፡፡
 • የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዕምነት ቦታዎች የመስቀል ማክበሪያ ቦታዎች በኦነግ/ ኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ በኦሮሞ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በሚገኙ የእምነት ቦታዎች ላይ በተደጋጋሚ የተፈፀመ የሃይማኖት እምነት መብት ጥሰት ተፈፅሞል፡፡ በአንፃሩ በኦሮሚያ መንግሥትና የአዲስ አበባ አስተዳደር ለእሬቻ ባህል ማክበሪያ ቦታ ሠጥተዋል፡፡
 • የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዕምነት ተከታዬች ካህናትና ምዕመናን ሰላማዊ ሠልፍ እንዳያደርጉ መታፈን ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ላይ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሦስት ድርጅቶች በመነጋገር ሰላማዊ የእንቢተኛነት ትግል፣ የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ቢጠሩ ህዝብ ተግባራዊ ያደርጋል እንላለን፡፡
 • ‹‹በሀገራችን ውስጥ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ግምባር ቀደም ተጠቂ ይሁኑ እንጂ፣ “መጤ”ና “ኗሪ” በሚል የጥላቻ ትርክት የተቀመረው ሕገ-መንግሥት ሌሎች ብሄረሰቦችንም ለጥቃት አጋልጧቸዋል። ጉራጌዎች፣ ስልጤዎች ጋሞዎች…ወዘተ ተጠቂዎች ሆነዋል። በሃይማኖትም ክርስቲያን ኦሮሞዎች የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት መካከል ይገኛሉ። በአብዲ ኢሌ የሥልጣን ዘመን ወደ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዜጎቻችን ከሶማልያ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ተፈናቅለዋል። በተመሳሳይ መልኩ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሌ ብሄረሰብ ዜጎቻችን ከኦሮሚያ ተፈናቅለው ለስቃይ ተዳርገዋል። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የጌዲዖ ዜጎቻችንም በኦሮሞ ፅንፈኞች ተፈናቅለው በብርድና በዝናብ በመጠለያ ሥፍራዎች እስከ አንድ ዓመት ድረስ ኖረዋል። የፈረደባቸው የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ከቤኒሻንጉል በተደጋጋሚ ተፈናቅለዋል፣ እስከዛሬም ያላቆመ ክስተት ነው።››3
 • የፌዴሬሽኑን ሕገ-መንግሥትና የክልል ሕገ-መንግሥቶችም፣ ተቀርፀው የተዋቀሩት አንዱን ‹ኖሪ/ባለቤት› የአንደኛ ደረጃ ዜጋ ሌላውን ‹መጤ/ ሠፋሪ› በሚል የሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ማዕከልነት ላይ የተመሠረቱ ናቸው።  በቡራዩ፣ በአርሲ፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በሻሸመኜ፣ በዝዋይና በባሌ እስከ ሦስት ጊዜ ድረስ የተካሄደው ጥቃት፣ ባመዛኙ የአማራና ሌሎችንም “መጤ” ተብለው የተሰየሙ ብሄረሰብ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ፣ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማኞችንና የዕምነት ቤቶችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት ነው። የዘመናችን የኦነግ አረመኔዊ ሽብርተኛነት፤-የዘመናዊ ሽብርተኛነት በፖለቲካ ድርጅቶችና ግለሰብ ደረጃ በስብዓናችን ላይ የሚከሰት ቀውስ እንደ (ሽመልስ አብዲሳ) የፖለቲካ ሥልጣን ጥማት ከፍተኛ ስሜት እንደ (ጅዋር መሓመድ)፣ የበታችነት ስሜት የሚንጸባረቅ የማንነት ጥያቄ እንደ (በቀለ ገርባ)፣ በራስን ማፍቀርና ማምለክ ስሜት ሁሉን አውቃለሁ ባይነት ስሜት መወጠር (ዶክተር ዐብይ አህመድ) አንዱን ሰማዕት አንግሶ ሌሎቹን ሰማዕታት አርክሶ፣ ዜጎችን እንደ ልጅና የእንጀራ ልጅ ለአንዱ ሃውልት ለአንዱ አመድ የሚሰጥ  መሪ በታልክ ተጠያቂ ነው፡፡
 • በኦኤምኤን የጅዋር መሃመድ የቴሌቪዝን ስርጭት ጣቢያው የተቃዋሚ ሽብርተኛነት ሚና ለብዙ አመታት ተጫውቶል፡፡ በተቃሚዎች የሚመራ ሽብርተኛነት ቡድን ሲሆን ኢላማውም የኦሮሞ በአማራና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዬች ላይ እርምጃ እንዲወስድ የመንግሥት  ባለሥልጣኖችና መንግስታዊ ተቆማት ላይ ጥቃት እንዲፈፅም ቀስቅሰዋል፡፡  እነዚህ ሽብርተኞች የፖለቲካና የኃይማኖት ዓላማዎችን በኃይል ማሳካት ነው፡፡
 • የኦሮሞ ፊዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ በቀለ ገርባና ጅዋር መሃመድ  የፖለቲካ ርዕተ ዓለም ፍልስፍና አንዴ የግራ ፖለቲካ ሽብርተኛነትንና አንዴ ደግሞ የቀኝ ፖለቲካ ሽብርተኛ በማጣቀስ  የዘርና ኃይማኖት ፍጅት ሲያደርሱ ኦፌኮ ምንም መግለጫ አላወጣም፡፡
 • ህወሓትና ኦነግ ሸኔ በመናበብ በሃገሪቱ ውስጥ የኃይማኖታዊ ሽብርተኛነት፡-ዋልታ ረገጥ ወይም ፅንፈኛ ኃይማኖታዊ ሽብርተኛ ቡድን በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና በሙስሊም የእምነት ተከታዬች ላይ ሽብር ፈፅመዋል፡፡
 • በሃገራችን የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር በተለይ ኦነግ ሸኔ በወለጋ ውስጥ የሚፈጽመው የወንጀል ሽብርተኛነት የሰዎች ገደላና አፈና የሃያ ሦስት ባንኮች ዘረፋ ለአብነት ይጠቀሳል፡፡ ኦነግና ኦነግ ሸኔ ወንጀለኛ ሽብርተኞ ቡድኖች በወንጀል ድርጊት ኃብትና ንብረት የሚዘርፉ ቡድኖች ውስጥ ይካተታሉ፣ በዕፅ ንግድ፣ በመሳሪያ ሽያጭ፣ በሰዎች ዝውውር፣ በወሲብ ንግድ፣ በህጻናት ሽያጭና ህፃናትን በወታደርነት በመመልመል ፣ በገንዘብ ዝውውር በህገ ወጥ መንገድ የተሰማሩ ወንጀለኛ ሽብርተኛ ብድኖች ናቸው፡፡የህግ ሉዓላዊነት በኢትዮጵያ ይከበር!!!

የዘርና ኃይማኖት ፍጅት የሚቃወም፣ ሰላማዊ የእንቢተኛነት ትግል፣ የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ  ይጠራ!!! ነጻነትና መብት በልመና አይገኝም!!! በመሣሪያ የመጣ፣ በመሣያ ይወጣ!!!

 

ምንጭ

1-https://www.youtube.com/watch?v=v8knP7MvFBc /ጉዳያችን – የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዘር ማጥፋት መከላከያ ድርጅትፕረስ ኮንፍረንስ -Abbay Media-Ethiopia (መታየት ያለበት ዩቲዩብ)

2-https://www.youtube.com/watch?v=14gADx9LyRg/Ethio 360 Special program “የዘር ማጥፋት ይቁም” ዘመቻ Tuesday September 22, 2020 (መታየት ያለበት ዩቲዩብ)

3-ዴሞክራሲያ ቅጽ 48 ፣ ቁጥር 3 ነሐሴ ፣ 2012 ዓ.ም/የኢሕ አፓ መግለማ ጥላቻ፣ አክራሪነትና ዘረኝነት አንድም ሦስትም ናቸው! /by ዘ-ሐበሻ/ August 27, 2020

Leave a Reply