የከረዩ አባገዳ ከድር ሀዋስ ቦሩ በአሸባሪው ሸኔ መገደላቸውን የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ገለጸ፡፡

በከረዩ አባገዳ ላይ በአሸባሪው ሸኔ በተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡

ሸኔ በየጊዜው በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈጽመው ግድያ አሸባሪው ቡድኑ ሕዝባዊ ዓላማ እንደሌለው ማረጋገጫ መሆኑን የክልሉን ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ዋቢ አድርጎ ኢብኮ ዘግቧል፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ህዳር 24 ቀን 2014 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

This Post Has One Comment

  1. Tesfa

    እጅግ ያሳዝናል። የሃገር ሽማግሌዎችን የሚገሉ እነዚህ የወያኔ ተላላኪዎች መቼ ይሆን ሃገርንና ህዝብን ከማወክ ተመልሰው ሰላምን ወዳድ በሆነው የኦሮሞ ህብረተሰብ ውስጥ በሰላም የሚኖሩት? ችግሩ የተላላኪዎች ባህሪ የታዘዙትን መፈጸም በመሆኑ በራሳቸው አስበው ለመኖር አይፈቀድላቸውም። ሁሌ እየገደሉና እየተገደሉ መኖር ምን የሚሉት ስልጣኔ ነው? ይህ ግድያ የተፈጸመው የኦነግን ክፋት ለመግታት ወጣቱን በመምከርና ተው አይበጅም በማለታቸው እንደሆነ ግልጽ ነው። የኦሮሚያ ክልል መንግስት በሥራቸው የተሰገሰጉትን እነዚህን ተላላኪዎች ካልመነጠሩ ብዙም ሳይቆይ ችግሩ በራሳቸውም ላይ የሚፈጸም ነው የሚሆነው። በማያሻማ መረጃና የክትትል ስራ ላይ ተደግፎ ገዳይን መግደል፤ አሸባሪን እንዲሸበር ማደረግ ተገቢ ይመስለኛል። ሲጀመር ኦነግ ሸኔ አፍጫንችሁ ሥር ነው ያለው። ጋዜጠኞችና ለኦነግ እሳት የሚያቀብሉ ሰዎች ኦነግ ሸኔ ባለበት ሥፍራ ድረስ በመሄድ የሰሩትን ዘገባ ተመልክተናል። ታዲያ የሃገሩ መንግስት እንዴት በስለላ መረቡ የትና ወዴት እንዳሉ ፈልጎ የሚደረገውን ለማድረግ ተሳነው? ግራ ያጋባል። በዚህስ ግድያና ዝርፊያ አሁን ማን ይሙት የኦሮሞ ህዝብ ያተርፋል? ብቻ የሃበሻው ሂሳብ ማወራረድ በወገኑና አብሮ አፈር በሚገፋው ድሃ ገበሬና ከእጅ ወደ አፍ በሚለው ላይ በመሆኑ ቱሩፋት የለሽና የበሽተኞች የፓለቲካ እይታ እንደሆነ አሁን በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የሚደረገው ፍትጊያ ያመላክታል። እብደታችን የሚቆምበት ጊዜና ህዝባችን እፎይ የሚልበት ጊዜ ለማየት ይናፍቀኛል። ይሆን ይሆን? አላውቅም።

Leave a Reply