You are currently viewing “የከተማዋ ማህበረሰብ በመደራጀት ከጸጥታ አካሉ ጋር በመሆን የከተማችንን ቁልፋ እና መለስተኛ በሮች በመዝጋት የጠላት ሰርጎ ገቦች እንዳይገቡ እንከላከል።”  አቶ አበበ ገብረመስቀል_የደሴ ከተ…

“የከተማዋ ማህበረሰብ በመደራጀት ከጸጥታ አካሉ ጋር በመሆን የከተማችንን ቁልፋ እና መለስተኛ በሮች በመዝጋት የጠላት ሰርጎ ገቦች እንዳይገቡ እንከላከል።” አቶ አበበ ገብረመስቀል_የደሴ ከተ…

“የከተማዋ ማህበረሰብ በመደራጀት ከጸጥታ አካሉ ጋር በመሆን የከተማችንን ቁልፋ እና መለስተኛ በሮች በመዝጋት የጠላት ሰርጎ ገቦች እንዳይገቡ እንከላከል።” አቶ አበበ ገብረመስቀል_የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ለደሴ ከተማ ህዝብ ያስተላለፉት መልእክት! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 14 ቀን 2014 ዓ. ም አዲስ አበባ ሸዋ የተከበራች የደሴ ከተማ ማህበረሰብ የሚከተሉት ነጥቦች ላይ በትኩረት እንሰራ ዘንድ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ። 1) በየአካባቢያችን በንቃት በመጠበቅ ጸጉረ ልውጦችን ለጸጥታ ሀይሉ የማስረከብ ስራ ከምንግዜውም በላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ 2) ለሰራዊታችን የሚደረገው የምግብና የውሀ አቅርቦት በአደረጃጀት ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ 3) ወጣቱ ፣ አመራሩ፣ የመንግስት ሰራተኛው እና አጠቃላይ ህዝባችን የጀመረውን የግንባር ደጀንነት አጠናክሮ እንዲቀጥል፣ 4) የኬላ እና የውስጥ ከተማችንን ጥበቃ በማጠናከር የከተማችንን ሰላም ለማስጠበቅ ሁሉም ማህበረሰብ እርብርብ እንዲያደርግ፣ 5) የከተማዋ ማህበረሰብ በመደራጀት ከጸጥታ አካሉ ጋር በመሆን የከተማችንን ቁልፋ እና መለስተኛ በሮች በመዝጋት የጠላት ሰርጎ ገቦች እንዳይገቡ እንከላከል። 6) ከተለመደው የጠላት የሀሰት ወሬ እና ፕሮፖጋንዳ እራሳችንን በማራቅ ከተማችን ላይ ተረጋግተን መቀመጥ አለብን። 7) ጸጉረ ልውጦችን እንቅስቃሴ ለመግታት ያመች ዘንድ ከዛሬ ጀምሮ የሞተር እና የባጃጅ እንቅስቃሴ በከተማዋ ላይ እንዲቆም በጸጥታ ምክር ቤት ተወስኗል። 😎 የተዘጉ የተለያዮ የንግድ ቤቶች በተለይ መድሀኒት ቤቶች በአስቸኳይ ከፍታችሁ ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንድትጀምሩ። ይህን በማታደርጉ ላይ አስፈላጊውን የህግ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን ለማሳሰብ እወዳለሁ። አቶ አበበ ገብረመስቀል የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply