የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እና የመንግሥት ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ከ750 ሚሊየን ብር በላይ ለመስጠት ቃል ገቡ

የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እና የመንግሥት ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ከ750 ሚሊየን ብር በላይ ለመስጠት ቃል ገቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እና የመንግሥት ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት የሚሆን ከወር ደመወዛቸው የሚቆርጥ ከ750 ሚሊየን ብር በላይ ለመስጠት ቃል መግባታቸው ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በጀግናው መከላከያ ሠራዊት የህወሓት የጥፋት ቡድን ላይ እየተወሰደ ባለው ህግን የማስከበር ስራ ለመደገፍ በየደረጃው ካሉ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በእስካሁኑ የሀብት ማሰባሰብ ስራ በከተማ አስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ፣ የመንግሥት ሰራተኞች እና ፖሊሶች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚሆን ከወር ደመወዛቸውን የሚቆረጥ ከ750 ሚሊየን ብር በላይ ለመስጠት ቃል መግባታቸው ተገልጿል።

ለመከላከያ ሰራዊቱ፣ የአጎራባች ክልሎች ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አባላትን ለማበረታታት እና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የሀብት ማሰባሰብ ስራው በተደራጀ እና ግልጽነት በተሞላበት መንገድ ሊሆን እንደሚገባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በውይይቱ ወቅት ገልጸዋል።

አያይዘውም ከወቅታዊ ሁኔታው ጎን ለጎን በመደበኛው የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና የፕሮጀክቶች ግንባታ እንዲሁም የኑሮ ውድነት ላይ የሚደረጉ የክትትል እና የቁጥጥር ስራዎች በአግባቡ እንዲሰሩም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የመንግሥት ሰራተኞች በዚህ የኑሮ ውድነት እና ሌሎች ችግሮች ለሠራዊቱ የሰጡት ድጋፍ እና ያሳየው መነሳሳት የአንድነት ማሳያ መሆኑንም አመላክተዋል።

 

የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሃንስን ጫላ በበኩላቸው እርሳቸውን ጨምሮ ከ15 የጤና ባለሙያዎች ሙያዊ ድጋፍ ለመስጠት ቃል መግባታቸውን ነው የጠቀሱት።

በነዋሪው ዘንድ የታየውን የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ እና ድጋፍ ለማድረግ ያሳየውን መነሳሳት ውጤታማ እንዲሆንም በየደረጃው ያሉ አመራሮች በልዩ ትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም አመራሮቹ መናገራቸውን የአዲስ አበባ ሴክሬታሪያት ቢሮ ያገነኘው መረጃ ያመለክታል።

 

 

 

 

The post የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እና የመንግሥት ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ከ750 ሚሊየን ብር በላይ ለመስጠት ቃል ገቡ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply