የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ወረራ እና ህገ ወጥ ግንባታን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው

የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ወረራ እና ህገ ወጥ ግንባታን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ወረራ እና ህገ ወጥ ግንባታን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ በመሬት፣ በፀጥታ እና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ወረራ እና ህገ ወጥ ግንባታን የተመለከቱ የተለያዩ መነሻ ፅሁፎች ቀርበዋል፡፡

በዚህም በየዓመቱ በተለያዩ አካላት በከተማው በከፍተኛ ሁኔታ የመሬት ወረራ እና ህገ ወጥ ግንባታ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ ህገ ወጥ ስራ እንዳይቆምም የመሬት ወረራን ለመከላከል ኃላፊነት የተሰጣቸው ተቋማት ተቀናጅተው አለመስራታቸው ምክንያት መሆኑ ተነስቷል።

ሌላው ወረራውን ማስቀረት ያልተቻለበት ምክንያት ተብሎ የቀረበው ከከፍተኛ አመራሩ ጀምሮ በየደረጃው ያለው የዘርፉ አስፈጻሚ አካል በሰነድ የተደገፈ ትዕዛዝ በመስጠትም ጭምር ለህገ ወጦች ከለላ ሲሆን መቆየቱ ተጠቅሷል።

በትዝታ ደሳለኝ

The post የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ወረራ እና ህገ ወጥ ግንባታን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply