የከተራና የጥምቀት በዓል በሁሉም የአማራ ክልለ አከባቢዎች ያለምንም ችግር በሰላም መከበሩ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 11 ቀን 2013 ዓ.ም          አዲስ አበባ ሸ…

የከተራና የጥምቀት በዓል በሁሉም የአማራ ክልለ አከባቢዎች ያለምንም ችግር በሰላም መከበሩ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 11 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸ…

የከተራና የጥምቀት በዓል በሁሉም የአማራ ክልለ አከባቢዎች ያለምንም ችግር በሰላም መከበሩ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 11 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ እንደገለፁት በሁሉም የአማራ ክልል አከባቢዎች ከተራና ጥምቀት በዓል ያለምንም ችግር በደማቅ ሁኔታ ከነሙሉ ኃይማኖታዊ ክዋኔው በሰላም፣በፍቅር፣በደስታ ተከብሮ መጠናቀቁን ገልፀዋል። ከማይዳሰሱ ቅርሶች አንዱ የሆነው የጥምቀት ኃይማኖታዊ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበር ታላቅ በዓል ሲሆን በዓሉ ሌሎች የእምነት ተከታዮች፣ የውጭ አገር ቱሪስቶች፣ አርቲስቶች፣ ታላላቅ የእምነት አባቶች፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ከተለያዩ ክልሎችና አጎራባች አገራት ለአብነትም ከኤርትራ የተጋበዙ የሉካን አባላት በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብራ ሯል ብለዋል። ይህ በዓል ከኃይማኖታዊ በዓልነቱ በተጨማሪ ወንድማማችነትን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን፣ የጋራ ትስስርንና የጋራ ብልፅግናን ልንፈጥርበት በምንችልበት መንገድ በኃይማኖት አባቶችና በመንግስት የስራ ኃላፊዎች መልዕክቶችን በማስተላለፍ የተከበረ ነበር። በተለይም በጎንደር ፣ በምንጃርና በዋና ዋና የክልላችን ከተሞች እጅግ ብዙ ምዕመናንና የበዓሉ ታዳሚዎች በተገኙበት በተሳካ ሁኔታ ተከውኗል ሲሉም የኮሚኒኬሽን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል ። በዓሉ በሰላም በመጠናቀቁም እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን ይህ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፅዖ የነበራችሁ የፀጥታ አካላት፣ የክልላችን ወጣቶች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ሴቶች፣ ባለሀብቶቻችንና መላውን የክልላችን ህዝቦች ላደረጋችሁት መልካም ትብብርና ላሳያችሁት ጨዋነት የክልሉ መንግስት ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና ያቀርብላችኋልም ብለዋል። መላው የክልላችን ህዝቦች በዓሉ በሰላምና በተሳካ መንገድ እንዲጠናቀቅ ያሳያችሁት ትህናትና ፣ ጨዋነት፣ መልካምነት ፣ ቁርጠኝነትና አንድነት በሌሎች የክልላችን የሰላም፣ የልማትና የአብሮነት ስራዎቻች ላይ ሁሉ በመድገም የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ ጥሪውን ያቀርብላችኃል ብለዋል አቶ ግዛቸው። መጭው ጊዜም በርካታ በዓላት የሚከበሩበት ወቅት በመሆኑ ትብብራችሁ፣ አስተዋይነታችሁና ጨዋነታችሁ እንዳይለዬንና አብሮነታችንም ተጠናቅሮ እንዲቀጥል ሲሉም አሳስበዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply