አርብ ሰኔ 30 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ)
በከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ምርምር ተቋማት እና በኢንዱሰትሪው መካከል ምቹ የእርስ በእርስ ትርስስር በመፍጠር፤ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ያስችላል የተባለለት ረቂቅ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል።
አዋጁ የኢንዱስትሪውን መስረታዊ ችግር በመፍታት በቂ እና ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት የትስስር ሥራዎችን ለመስራት ያለመ ነው ተብሏል።
የትስስር ሥራዎች አገራዊ የልማት አጀንዳን ባገናዘበ መልኩ በቅንጅት፣ በወጥነት፣ በተጠያቂነት እና በብቃት እንዲተገበሩ እና ውጤታማነትን፣ የጋራ ተጠቃሚነትን፣ አገራዊ እና ዓለማቀፋዊ ተወዳዳሪነትን የሚጨምር መሆኑም ተመላክቷል።
ረቂቅ አዋጁ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በየደረጃው ሲወያዩበት ቆይተው በቂ ግብዓት እና ማሻሻያ ተደርጎበት በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት መጽደቁን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
Source: Link to the Post