የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአሶሳ እና መቅደላ ዓምባ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ ትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቀዋል፡፡
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ከማል አብዱራሂም ዩኒቨርሲቲው 2 ሺህ 182 ተማሪዎችን ለ7ኛ ጊዜ ማስመረቁን ጠቁመው ከተመራቂዎቹ መካከል በመደበኛ መርሃ-ግብር ውስጥ 1 ሺህ 636 ተማሪዎች፣ በቅዳሜ እሁድ 401 ተማሪዎች፣ 145 ተማሪዎች ደግሞ የድህረ-ምረቃ ምሩቃን መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል 33 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው ዶክተር ከማል አመልክተዋል፡፡
የእለቱ የክብር እንግዳ የዩኒቨርስቲው ቦርድ ሰብሳቢ እና የትራንስፖርት ሚንስትር ዴኤታ አቶ አወል ወግሪስ፣ በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ዕውቀት አግኝተው የተመረቁ ተማሪዎች ሀገሪቱን ከድህነትና ኋላ ቀርነት ለማላቀቅ ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ኃላፊነት ይዘው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በተጨማሪም ተመራቂዎች ያገኙትን ክህሎት በመጠቀም ከስሜታዊነትና በጸዳ መልኩ አሁን ላለው ሀገራዊ ሁኔታ የመፍትሔ አካል መሆን እንደሚጠበቅባቸውም አቶ አወል ማሳሰባቸውን ከቤኒሻንጉን ኩሙዝ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ የመቅደላ ዓምባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በመካነሰላም በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ግቢው 344 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 137ቱ ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡
ዩኒቨርስቲው በትናትናው ዕለትም በተፈጥሮ ሳይንስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 480 ተማሪዎችን ማስመረቁ ይታወሳል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply