የካሊፎኒያው ሰው ሌላ ሁለተኛ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት

እኤአ በ2019 ደቡብ ካሊፎርኒያ በሚገኘው የአይሁድ ቤተ-እምነት ውስጥ አንዲት ሴትን በመግደልና ሦስት ሰዎችን በማቁሰል የተከሰሰው የ22 ዓመቱ ነጭ ወጣት ሌላ ሁለተኛ የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት መሆኑን ተገለጸ፡፡

በፌዴራሉ ፍርድ ቤት የተሰጠው የአሁኑ ውሳኔ ከሦስት ወር በፊት በክፍለ ግዛቱ ፍርድ ቤተ ከተፈረደበት የዕድሜ ልክ እስራት ጋር ሁለተኛው መሆኑን ተመልክቷል፡፡

“የነጭ የበላይነት ተከታይ ነው” የተባለው ጆን ቲ ኧርነስት የሟች ቤተሰቦችና የእምነቱ አባላት በተገኙበት ችሎት ስለተወሰነበት ፍርድ ምንም ያለው ነገር አለመኖሩ ተገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ ጠበቃው ጆን ቲ ኧርነስት በክፍለ ግዛቱ ፍርድ ቤት

“መናገር የሚፈልገው ነገር የነበረው ቢሆንም ዳኛው የከለከሉት በመሆኑ መናገር አልቻለም” ብለዋል፡፡ 

ዳኛው ስለከለከሉበትም ምክንያት ጠበቃው ሲገልጹ “ለሚያራምደው ጥላቻው ስብከት መድረክ አልሰጠውም” በሚል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በውሳኔ መሰረት የፌዴራሉ ዕድሜ ልክ እስራት ከጨረሰ በኋላ በክፍለ ግዛቱ የተሰጠውን ሌላ የዕድሜ ልክ እስራት ደግሞ የሚጀምር መሆኑን ተመልክቷል፡፡

በተወንጃዩ ላይ የተላለፈበት የዕድሜ ልክ ውሳኔ በፌዴራሉና በክፍለ ግዛቱ የሚፈጸመው አንዱ አንደኛውን ተከትሎ በየተራ መሆኑንም የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ አንተኒ ባታግሊያ ተናግረዋል፡፡

ይህ ማለት ጠንካራ መልዕክት ለማስተላለፍ ያህ ልነው እንጂ ሁሉቱ ዕድሜ ልክ እስራቶች ተከታትለው ይመጣሉ ማለት አለመሆኑ በዘገባው ተመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply