የካቡል መስጊድ የቦምብ ጥቃት

https://gdb.voanews.com/019e0000-0aff-0242-f0d4-08da80f1dbc3_w800_h450.jpg

አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ በአንድ መስጊድ ላይ ሌሊቱን በተጣለ የቦምብ ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር በትንሹ ሃያ አንድ መድረሱን የታሊባን ባለሥልጣናት ገለፁ።

ሌሎች ሰላሣ ሦስት ሰዎች መቁሰላቸውን የካቡል ፖሊስ ቃል አቀባይ ለቪኦኤ ገልፀዋል። 

ኃይለኛው የቦምብ ፍንዳታ የደረሰው የምሽት ፀሎት እየተካሄደ ሳለ እንደነበረና የዐይን ምስክሮችና ፖሊስ ያመለከቱ ሲሆን ከተገደሉት መካከል ፀሎቱን ይመሩ የነበሩት ታዋቂ የሱፊ እስልምና ሊቅ አሚር መሐመድ ካቡሊ እንደሚገኙበት ተጠቁሟል።

የታሊባን መሪዎች የሽብር ጥቃቶችን ለመከላከል ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስዱና ተጠያቂዎቹን ህግ ፊት እንዲያቀርቡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍጋኒስታን ድጋፍ ተልዕኮ ጠይቋል።

እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊ ነኝ ያለ የለም። ይሁን እንጂ ወትሮም የሱፊ አስተሳሰብን የሚያወግዘው ራሱን ‘የእስልምና መንግሥት ብሎ የሚጠራው ቡድን ድርጊት ሳይሆን አይቀርም’ ተብሎ መጠርጠሩ ተዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply